Thursday, August 16, 2018

የአዊ (አገው ምድር) የፈረስ ጉግስ ባህል

ከ70 ዓመታት በላይ የሆነው የ‹‹አዊ የፈረስ ማህበር›› ባህሉን ጠብቆ በማቆየቱ በ‹‹ቅርስና ባህል ዘርፍ›› ለዘንድሮው የ‹በጎ ሰው ሽልማት› ከተመረጡ ሶስት ዕጩዎች አንዱ ሁኗል፡፡ የፈረስ ጉግስ ባህሉ ዝም ብሎ ለመዝናኛ የሚሆን ብቻ አይደለም፡፡ የማህበራዊ ስነ-ሰብ አጥኝዎች በአግባቡ ባያጠኑትም ቅሉ፣ የራሱ ታሪካዊ አመጣጥ አለው፡፡ ከታሪካዊ እውነታዎች እና አሁን የፈረስ ጉግስ ከሚዘወተርባቸው ሁነቶች ተነስቶ ሶስት መላምቶችን መገመት ይቻላል፡፡
1ኛ) አንደኛው ከመከረኛው ጦርነት ጋር የተያያዘ ነው፡፡
መኪና፣ አውሮፕላን እና ዘመናዊ የጦር መሳሪያ በሌለበት ዘመን አብዛኛው የእርስ በርስም ሆነ ከውጭ ጠላት ጋር ይደረጉ የነበሩ ውጊያዎች የሚከወኑት በጦር እና ጎራዴ በሚደረግ የጨበጣ ውጊያ ነው፡፡ የጨበጣ ውጊያን በድል ለማጠናቀቅ ደግሞ ፈረስ ትልቅ አስተዋፅኦ ነበረው፡፡ የአድዋ ጦርነት በፈረስ አጋዥነት ለድል እንደበቃ ብዙ ማሳያዎች አሉ፡፡ ለ‹‹ባንዳ እርግማን›› አፋችን የሾለውን ያህል ‹‹ፈረሶችን›› አመስግነናቸው አናውቅም፡፡ ለኢትዮጵያ ነፃነት ከ ‹‹ባንዳዎች›› እና ‹‹ከፈሪዎች›› ይልቅ ፈረስ የነበረው አስተዋፅኦ ታላቅ ነው፡፡ ፈረስ ለቀደሙ ነገስታት ባለውለታ፣ የህይወታቸው አለኝታ ነበር፡፡ ለዚህም ይመስላል ብዙ ነገስታት ከ አባታቸው ይልቅ የፈረሳቸው ስም ጎልቶ የሚወጣው፡፡ ለምሳሌ የአፄ ቴወድሮስን ብናነሳ፡
‹‹ታጠቅ ብሎ ፈረስ፣ ካሳ ብሎ ስም
አርብ አርብ ይሸበራል፣ ኢየሩሳሌም››……ተብሎ ተገጥሞላቸዋል፡፡

ከነፃው ፕሬስ ፋና-ዎጊዎች


(በቅዱስ ሃብት በላቸው)
ነሃሴ 9 ቀን በኢትዮጵያ የነፃ ፕሬስ ታሪክ ፋና-ወጊ ተብለው በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱት ጋዜጠኞች መካከል አንዱ የሆነው የመብሩክ/መብረቅ ጋዜጣ አሳታሚና አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ ወርቁ ዓለማየሁ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየበት ዕለት ነው። “ትንሿ ትግራይ!” በሚል ርዕስ በአንድ መንግስታዊ ተቋም ውስጥ ከላይ እስከታች የተሰገሰጉትን የአንድ ብሔር ሰዎች በማስረጃ ማጋለጡን ተከትሎ ድንገት ታፍኖ እስር ቤት ተጥሎ የነበረው ጋዜጠኛ ወርቁ፣ ከእስር ቤት እንደወጣ ነበር እስከወዲያኛው ከዚህ ዓለም በሞት የተለየን።

Monday, August 13, 2018

‹‹ፍቅር›› ወይስ ‹‹ፍትህ›› የትኛው ይቀድማል?



ሰልጥነናል፣ ደሞክርሰናል፣ አድገናል እንላለን እንጂ ቁልቁል እየተምዘገዘግን ነው፡፡ ለአንድ ማህበረሰብ የእድገትም ይሁን የስልጣኔ መሰረት ለዘመናት ያካበተው የአስተሳሰብ፣ የሀይማኖት፣ የባህል እና የሞራል እሴት ነው፡፡ ይህ እሴት በዘመን መንገድ ውስጥ ተናደ፡፡ የ60ዎች ትውልድ በማህበረሰቡ ውስጥ የነበሩ የመተማመን ድልድዮችን ሰብረው፣ የመጠራጠርን ግንብ ሰሩ፡፡ በ60ዎች ከተፈለፈሉት የመደብ ተጋዮች በህይወት ተርፎ በትረ መንግስቱን የጨበጠው ‹‹ትህነግ›› የተራረፉ ድልድዮችን ሰባበራቸው፡፡ አንዱ አንዱን በአይነቁራኛ መከታተል ጀመረ፡፡ አጥሩ እየጠነከረ ሂዶ ዘመን በሚሻገር የዘር አጥር ታጠረ፡፡ ትህነግ ‹‹ ንግበር በአርያነ…..›› ብሎ የፈጠራቸው የየብሔሩ ድርጅቶችም ድልድይ አፍርሶ ግድግዳ መጠገን ላይ ተጠመዱ፡፡

Saturday, August 11, 2018

የልጅነት ትዝታ


ይችን ልጅ ሳይ ልጅነቴ ትዝ አለኝ፡፡ ከልጅነቴ ውስጥ ደግሞ የአራተኛ ክፍል የሳይንስ መምህር ትዝ አሉኝ፡፡ አንድ ቀን የሳይንስ መምህር አዳፋ ካቦርታቸውን እና እንደ ምድር ወገብ መሃል ለመሃል የተሰነጠቀች ባርኔጣቸውን ለብሰው ወደ ክፍል ገቡ፡፡
‹እንደምን አደራችሁ ልጆች›
ሁላችንም ተነስተን ‹እንደምን አደሩ መምህር›
‹
ቁጭ በሉ›
‹
እሺ› ብለን ቁጭ!
ምን አለበት ‹እንደምን አደሩ› ስንላቸው ‹እግዚሃር ይመስገን› ወይም ‹ደህና ነኝ› ቢሉን!...አላሉንም..... ቀጥታ ገጣባ አህያ ወደ ሚመስለው ብላክ ቦርድ ሄደው ‹ሳይንስ› ብለው ጻፉ፡፡ ቀጥለውም የሰሌዳው ጠርዝ አካባቢ በዲያጎናል አስምረው ቀን ፃፉ፡፡