Thursday, September 10, 2015

አስገራሚዋ ብላቴና (The Miracle Teenager)_ክፍል ፪

               በመጨረሻም ፌስቡክ ተጠቃሚዋ ስምረትና አሁን ያለችበት ሁኔታ !
ከአመታት በኋላ በቀጠሯችን መሰረት ከተወዳጇ ስምረት ጋር ተገናኘን፡፡ የተገናኘነው ከአመታት በፊት አውርተንበት የነበረው ቦታ መሆኑ ሁለታችንንም ትልቅ ትዝታ ላይ ጥሎናል!
ከቀጠሯችን ውጭ ይዛቸው የመጣቻቸው ሦስት ሴት ልጆች ትኩረቴን ስበውታል፡፡ በአንድ አይነት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሦስት ዕንቁዎች !! የስምረትን አስበልጬ ከሁሎችም ጋር ሞቅ ያለ ሰላምታ ከተለዋወጥኩ በኋላ ስራዬን ጀመርኩ፡፡
«ባለ ራዕይዋ ስምረት ይታይህእንኳን በድጋሜ ለመገናኘት/ለመተያዬት አበቃን»
«(
ሳቅ…) እግዚአብሄር የተመሰገነ ይሁንበድጋሜ ስላገኘሁህ እኔም በጣም ደስ ብሎኛል
«
እሽ ወይዘሪት ስምረትነው ወይንስ ወይዘሮ ይሆን ? በሚገርም ሁኔታ ተለውጠሻል፣ ትልቅ ሰው ሁነሻልሶስቱ አብረውሽ የማያቸው መንትያ ሴቶችስ ልጆችሽ ይሆኑ

«ወይዘሪት በለኝ እባክህወይዘሮ እያልክ አቁመህ እንዳታስቀረኝ… (ፈገግታ…) ልክ ነህአድጊያለሁ። እነዚህ ልጆች አዎ ያው በሌላ እናት ተምጠው የተወለዱ ልጆቼ ናቸው…!!»
«
ማለትአንቺ ጋር ነው የሚኖሩት…?»
«አዎ
«ግቢ ውስጥ በነበርሽባቸው ጊዜያቶች አንዳንድ እንቅስቃሴዎች ታደርጊ እንደነበር በተደዋወልንባቸው ሰዓታቶች አጫውተሽኛልእስኪ አጠቃላይ ሁኔታው ምን ይመስል እንደነበር አጫውችኝ።»
«ጓደኞቼ ጋር በመሆን አንዳንድ ነገሮችን እናደርግ ነበር… «ካንድል ናይት» የሚባል ምሽት ላይ 1:30 ያህል ጊዜ የሚቆይ ፕሮግራም አዘጋጅተን አሪፍ አሪፍ መጣጥፎች፣ ግጥምና ወጎች እናቀርብ ነበር…»
«ከጥበብነቱ በላይ የፕሮግራሙ አላማ ምንድነው ? ማለትየምታገኙበት ጥቅም አለ
«
አዎዋና አላማውም እሱ ነበርፕሮግራሙን ለመታደም የሚፈልግ እያንዳንዱ ተማሪ ሁለት/ሁለት ብር ይከፍላልበሳምንት ሶስት ቀን ነው የምናቀርበው፣ በእያንዳንዱ ቀን እስከ አምስት መቶ (500) ብር እናገኝበት ነበር…»
«በሳምንት ሶስት ቀን አሪፍ እራት ትበላላችሁ ማለት ነው»
«(ሳቅ…) በፍፁም !! አጠቃላይ የሰበሰብነውን ገንዘብ ግቢው ውስጥ ባሉ የተማሪ አለቆቻችን አማካኝነት ደጋፊ ለሌላቸው ወይንም እንደኔ ከደካማ ቤተሰብ ለተገኙ ተማሪዎች ነበር ከመፅሐፍት እስከ አልባሳት ግዥ የምናውለው።»
«ብዙ ጊዜ ነገሮችሽ ሁሉ ከአምሳያዎችሽ ጋር የተሳሰሩ ናቸውእና እንዴት ነው ይሄ መዋጮ ደካማ ወንዶችንም ያካትት ይሆን
(ሳቅ…) ይሄን ያህል ለወንዶች ጨካኝ ነኝ ብዬ አላስብምያው ሴት እንደመሆኔ የሴት ልጅ ችግር ሳይነግሩኝ ይገባኛል። ኑሬበታለሁለዛ ነው። እንጂ ግቢ ውስጥ አብዛኛውን የሚደገፉ ልጆች ወንዶች ናቸው…»
«ለምን ይሆን
«ምክኒያቱምበሃገራችን ውስጥ ሴት ልጆች ምንም ያህል የትምርት ፍላጎት፣ ብቃት ቢኖራቸው ቤተሰቦቻቸው ደካሞች ከሆኑ ወደዩኒቨርሲቲ የመምጣት ዕድላቸው ጠባብ ነው። ከመጡም በኋላ በተለያዩ ችግሮች አማካኝነት ሊያቋርጡት ይገደዳሉበቀላሉ የኔን ታሪክ እንኳን መለስ ብለህ ብታይ ለማለት የፈለኩት ይገባሃል።»
«እንደምትይው ከሆነወንድ ሆኜ ቢሆን ኑሮ ትምህርቴን አላቋርጥም ነበር ነው…»
«
አዎእንደዛ ልልህ እችላለሁ። ወንድ ሆኜ ቢሆንያኔ በናቴ ችግር ምክንያት ትምርቴን ለማቋረጥ ባሰብኩበት ወቅት እናቴ እንዲህ ልትለኝ ትችላለች… «ልጄአንተ መጠህ ልብሴን አታጥብ፣ እንጀራ አትጋግርሃሳብህ ነው የሚብሰኝ፣ እንደምንም ብለህ ትምርትህን ጨርስልኝየኔ ነገር ያኔ ይደርሳል… (ፈገግታ
(ስምረት ይሄን ስትል ሳቄን መቆጣጠር አልቻልኩምከነገሩ በላይ ለማስረዳት የተጠቀመችው ቋንቋ ረዥም ሰዓት ስላሳቀኝንግግራችንን የቀጠልነው ሻይ ቡና እያልን ብዙ ከተጨዋወትን በኋላ ነበርስምረት ጨዋታዋ የማይጠገብ፣ ሁሌም አዲስ እየሆነች የምትመጣ ቀለል ያለች ሴት ናትበጨዋታችን መሃል «አካሄድ» የሚባል ነገር እንዳለየመጣላትን ሁሉ በፈለገችው ቋንቋ መጠቀም ያለባት ቤቷ ውስጥ እንጂ እዚህ «ቃለ መጠይቅ» ላይ «ስርዓት» መያዝ እንዳለባት ነግሪያት ነበር… «መስሚያዬ ጥጥ ነውአለች…!!)
«እሽ ስምረትያው ዛሬ ቃለመጠይቅ ያደረኩልሽ ባጋጣሚ ነውከአመታት በፊት ካንቺ ጋር ያወራነውን ያስነበብኳቸው ጓደኞቼ «አሁን ያለችበት ሁኔታ ምን ይመስላልየሚል ተደጋጋሚ ጥያቄ ስለጠየቁኝ ነው። ሌላ ቀን በሰፊው እስከምናወራ ድረስ እስኪ አሁን ስላለሽበት ሁኔታ የሆነ ነገር በይንበተለይ ስለምትረጃቸው ልጆችእንዲሁም ደግሞ የምታመሰግኛቸው ሰዎችና መልዕክት ማስተላለፍ የምትፈልጊው ነገር ካለ መድረኩን ለቅቂያለሁ… »
«አመሰግናለሁአሁን አንድ ጥሩ ደሞዝ የሚከፈላት ትጉህ ሰራተኛ ነኝ። ያው ሁላችሁም እንደምታውቁት ከነ ታደለች ገብሩና ጓዴ ጥላሁን ጋር ፌስቡክ ላይ «ኸራ ለልጆች» የሚል ፔጅ ከፍተን እነዚህ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ህፃናት ተማሪዎችን ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ መልካም ሰዎችን እንጣራለን። ከልጆቹ ውስጥ ደግሞ በባሰ ሁኔታ እርዳታ የሚሹ አሉለምሳሌ እንደነዚህ ከኔ ጋር እንዳሉት ሦስት ልጆች ማለት ነው።
እነሱን ደግሞ የቻልነውን ያህል አንድም ሁለትም እያደረግን ከራሳችን ጋር እናኖራቸዋለን እናስተምራቸዋለን !!
ማመስገን የምፈልጋቸው እልፍ ሰዎች አሉስማቸው እንዲጠቀስ ባይፈልጉም ከራሳቸው፣ ከልጅ ከቤተሰቦቻቸው አልፈው እነዚህን ሚስኪን ህፃናት ወስደው የሚያሳድጉም፣ እዚሁ በብዙ ነገሮች ድጋፍ የሚያደርጉልንም ብዙ ሰዎች አሉ።
በተለይ ወጣቶች በሚገርም ሁኔታ የኃላፊነት ስሜት የሚሰማቸው፣ የሚያበረታቱን፣ በቻሏት መጠን እርዳታ የሚያደርጉልን አሉ። በዚህ «መስጠጥ» የሚለውን ቃል «መጃጃል» ብሎ በሚተረጉም ማህበረሰባችን መሃል እነዚህን አይነት ሰዎች ማግኘት መታደል ነው። እነሱን የማመሰግንበት ቃል የለኝምምስጋናችሁን ከምትረዷቸው ልጆች ደስታ ላይ ፈልጉት፣ ከምትረዷቸው ልጆች ግንባር ላይ አንብቡት ነው የምለው።
በትንሹ ከሃምሳ ብር ጀምሮ እስከቻላችሁት ድረስ ብትደግፏቸው ደስታው ከልጆቹ በላይ የናንተ ነው። እኔ የምፈራው «አንረዳም» የሚሉ ሰዎች ይኖራሉ ብዬ ሳይሆን… «ትንሽ ነገር አንረዳም» የሚሉትን ነው፣ ለምሳሌ አንተ መቶ ብር ብትሰጥ ለነዚህ ልጆች ሃምሳ እስክርቢቶ ገዛህ ማለት ነው።
ከዚህ በላይ «አንጥፎ መለመን» እንዳይሆንብኝ ንግግሬን ልቋጭሰላም !!
(ከስምረት ጋር ወደፊት በሰፊው የምትገናኙበት እድል እንደሚፈጠር እምነት አለኝ። እዚህ ግን ለነበረን ቆይታ በናንተው ስም እያመሰገንኳትአንድ ሃሳቧን የሚደግፍ ታሪክ ላጫውታችሁነብዩ ሙሀመድ 23 አመታት የእስልምና ትምህርት ካስተማሩ በኋላ ከዚህ አለም በሞት ተለዩበሰዓቱ በነብዩ ስነምግባር ብቻ ተማርከው የእስልምናን ሃይማኖት የተቀበሉ ሰዎች ሃይማኖቱን ለቀው መውጣት ጀመሩ። ይሄኔ ኸሊፋ (ተወካይ) የነበረው አቡበክር አስሲዲቅ ህዝቡን ሰብስቦ… «ሙሀመድን የምትገዙ ሙሀመድ ሙቷል፣ አላህን የምትገዙ እርሱ ህያውና የማይሞት ነው !!» የሚል መልዕክት አስተላለፈ።
በስምረት ችግር አዝናችሁ «እንርዳት አድራሻዋን ስጠን» ያላችሁኝ ወገኖቼና ወገኖቿ ሆይስምረት ዛሬ ከራሷ አልፋ የተቸገሩ ህፃናትን እየረዳች ነውና እናመሰግናለንእንደሷ ችግር ውስጥ ያሉ ህፃናትን መርዳት የምትፈልጉ ግን እነሱ አሁንም የናንተን እጅ እያዩ ነውና «አለንላችሁ !!» እንበላቸው።
(25% በታደለች ገብሩ እና 75% በተረጂ ልጆች ገፀባህሪነት የተፃፈ እውነተኛ ታሪክ!)

                                 ሰላም!  መልካምነት ለራስ ነው!
ፀሐፊውን ለማግኘት በሚከተለው የፌስቡክ አድራሻ ይፃፉለት፡ https://www.facebook.com/remzee.abissinia.1




No comments:

Post a Comment