Thursday, September 29, 2016

ሁሌ_ጥቁር_መርዶ...

"ከ ቀይ ባህር ማዶ~እሺ ሰው ሰመጠ
በሳውዲ አደባባይ~አንገት ተቆረጠ
በሰሜን በ ደቡብ~እልፍ ሰው ታሰረ
መሪና ተመሪ~ሁሉም አመረረ፤
አምሳ ተገደለ
እቤት ተቃጠለ"
.
.
ነው መሪ ዜናችን~ከ አገር ቤት ከማዶ
ሰላም ማውራት ቀረ~ሁሌ ጥቁር መርዶ፤

ሰፊ መሬት ይዘን~ሳይጠበን አድባሩ
ሰኞና ማክሰኞ~መስመር አየሰሩ
መተማመን ጠፋ~መለያየት በዛ
ሰው ፈጣሪን ረስቶ~ለ 'አምልኮ' ተገዛ
ሰከን ብሎ ማሰብ~መደማመጥ ቀረ
ድንበሩን አቋርጦ~ትውልድ ተሻገረ፤
ከወተቷ ሳይጠግብ~የ እናቱን መዓዛ
እየወጣ ቀረ~ወጣት እንደ ዋዛ፤
ቀላያትን ሞልተን~ማዕበል ከ ምንፈጥር
አትንፈጊን እማ~ከ አፈርሽ መቃብር 
(ዘላለም ጥላሁን፣ መስከረም 2009 ዓ.ም)

(መታሰቢያነቱ፡ ሰሞኑን ሜድትራኒያን ለሰጠሙት ከ 600 በላይ ወገኖች (አፍሪካውያን) እና ሞት ለተፈረደባት እህታችን)

No comments:

Post a Comment