Friday, June 29, 2018

ይድረስ ለባህርዳር የድጋፍ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ

(ጥብቅ ጥንቃቄ ስለማድረግና መፍትሄዎችን ስለመጠቆም (ምሳሌ የ 5-ለ5 አደረጃጀት)
በሩቁ ሁኖ የፍርሃት ድባብ መልቀቁ ብቻ መፍትሔ አልመሰለኝም፡፡ ሰልፉ እውን መሆኑ ካልቀረ ጥንቃቄው ላይ መነጋገር መልካም ይመስለኛል፡፡ ስለዚህ ከአዲስ አበባው የድጋፍ ሰልፍ ላይ ያየኋቸው ክፍተቶች ባህርዳር ላይ እንዳይደገሙ ቅድመ ጥንቃቄ እንዲደረግ በትህትና አመለክታለሁ፡፡
1) ከተማ አስተዳደሩ ሃላፊነት አልወስድም ቢልም ዞሮ ዞሮ የክልሉ ልዩ ሃይልና የክልሉ ፖሊስ መሳተፉቸው ስለማይቀር ከእነሱ ጋር በቅርበት መስራት፤
2) ሰልፉ የሚካሔድበትን ቦታ ከሰልፉ አንድ ቀን ቀድሞ፣ አንድ በአንድ ማየትና ማፅዳት (ገደሎችን፣ ሽንት ቤት፣ ድንጋይ ማስቀመጫዎች……) እና ሲጠበቅ እንዲያድር ማድረግ፡፡ የአዲስ አበባው አንዱ መላምት ይሄ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡
3) የፀጥታ አካላት እርስ በርስ ፍተሸ ተደርጎላቸው፣ የተፈቀደላቸውን መሳሪያ ብቻ ይዘው እንዲገቡ ማድረግ፡፡የአዲስ አበባው አንዱ መላምት ይሄ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡
4)  የተሳታፊዎችን ፍተሻን በተመለከተ፡
አዲስ አበባ የነበረው አንዱ ችግር ብዙ ሰዎች ሳይፈተሹ/በቀላል ፍተሻ ወደ ውስጥ ይገቡ ነበር፡፡ ፍተሻው ሶስት ቦታ በሶስት የተለያዩ አካላት ቢደረግ እመክራለሁ (ተሳታፊዎች እርስ በእራሳቸው፣ በተመረጡ ወጣቶች፣ በፀጥታ አካላት)፡፡
ሀ) የመጀመሪያው መግቢያ በር፡ የተወሰኑ አስተባባሪ ወጣቶችን በመመደብ ወደዚህ በር የሚመጡ ሰዎች አምስት /5/ አምስት/5/ እየሆኑ እንዲመጡ ማድረግ፡፡ ከዚያ እያንዳንዳቸው ከሌላኛው ቡድን አንድ አንድ ሰው ጋር እርስ በርስ እንዲፈታተሹ ማድረግ፡፡ ይህ አደረጃጀት ወደፊት ለሌላ ስራም እንደሚጠቅም በዚሁ ማሰብ!
ለ) ሁለተኛው መግቢያ በር፡ የፀጥታ አካላት እየፈተሹ እንዲያስገቡ ማድረግ
ሐ) ሶስተኛው መግቢያ በር፡ በአስተባባሪ ኮሚቴው የተመረጡ ወጣቶች እየፈተሹ እንዲያስገቡ ቢደረግ፤
  

ከዚህ በተጨማሪ ሁሉም ሰው ከጎኑ ያለውን ሰው በጥብቅ መከታተል አለበት፡፡ ‹‹ኤጭ ፍርሃት አትልቀቅብን›› የሚል ሰው አይጠፋም፡፡ ጎበዝ ‹‹ከስህተት የማይማር ፈንጂ አምካኝ ብቻ ነው›› ይላሉ፡፡ እያየንና እየሰማን ያለው ነገር ከዚህ በላይ እንዳስብ ያደርገኛል፡፡ መጠንቀቅ ክፋት የለውም፡፡ በተረፈ የግዮን አምላክ ይጠብቃችሁ!


(መልዕክቱን ለሚመለከታቸው ሁሉ አድርሱልኝ)







No comments:

Post a Comment