ባለቤታቸው ወ/ሮ ጥሩወርቅ ልባቸው ፈራ፡፡ ንጉሱ ለእንግሊዞች እጁን ከሚሰጥ፣ እራሱን ማጥፋት እንደሚመርጥ ውስጣቸው ያውቃል፡፡ ከዚያም ወደ መቅደላ አምባ መልዕክት ላኩ፡፡ ምን ብለው? ‹‹ እባክህ በልዑል አለማየሁ ይሁንብህ፣ በራስህ ምንም እንዳታደርግ›› ብለው፡፡ የአለማየሁ ነገር እንደማይሆንላቸው ያውቃሉ፡፡ ቴዲ ግን በአለማየሁ እንኳን ጨከነ፡፡ ህልመኛው ተስፋ ቆረጠ፡፡ ዞር ሲል ሊያቆመው የሞከረውን ምሰሶ የሚገፉ፣ ግርግዳውን ለማፍረስ የሚለፉ ሰዎችን አዬ፣ አስተዋለ፡፡ ከሰው መሃል ሁኖ ብቻውን ሆነ፡፡
‹‹ተስፋ ባጣ ምድረ በዳ
ያንድ እምነት ይሆናል ዕዳ››……እንዳለው ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ከገብርዬ ሞት በኋላ ከቅርቡ ያለው አንድ ነገር ብቻ ነው፡፡ ሽጉጥ፡፡
ያንድ እምነት ይሆናል ዕዳ››……እንዳለው ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ከገብርዬ ሞት በኋላ ከቅርቡ ያለው አንድ ነገር ብቻ ነው፡፡ ሽጉጥ፡፡