Wednesday, July 15, 2015

“ አንድ ሰው ለአንድ ወገን! ”

Click here for PDF
       (ወገን አልባ ወገኖች)
ፒያሳ፡ ሐምሌ 8፣2007 ዓ.ም ማለዳ 3፡00 ሰዓት፡፡ ፒያሳ ከፀሐይ በተለቀቁት ጨረሮች ፈካ ለማለት እየሞከረች ነው፡፡ ሰው የማያጣት ፒያሳ በሰው ትርመሰመሳለች፡፡ ወደ አስኮ፣ አውቶብስ ተራ፣ አራት ኪሎ፣ ካዛንቺስ ፣ መገናኛ ፣ስድሰት ኪሎ፣ ሽሮሜዳ፣ አዲሱ ገባያ ለመሄድ በሚርመሰመስ ሰው፡፡ መሃል ፒያሳ ከወደ አውቶብስ መያዣ አካባቢ አውቶብስ ጠባቂዎች የሚያርፉበት መቀመጫ እንደድሮው አውቶብስ በሚጠብቁ ሰዎች አልተያዘም፡፡ በምትኩ በቤት አልባ ብላቴናዎች ተጨናንቋል፡፡ ቀኑ ሐሩሩና ረሃቡ፣ ሌሊት ደግሞ ቁሩ የተፈራረቀባቸው ብላቴናዎች በጥዋቷ ፀሐይ ሙቀት እንቅልፍ አሸልቧቸዋል፡፡ አንዲት ቤት አልባ የሆነች ውሻም ከቤት አልባ ብላቴናዎች ጋር ጉርብትናን ፈጥራ አብራ ተኝታለች፡፡ ለብላቴናዎች ሙቀትንና ፍቅርን ትለግሳለች፡፡ እነሱም በአጠፋው ፍቅርንና ሙቀትን ብቻ ሳይሆን ከሚበሉትም ያጋሯታል፡፡ ውሻዋ ለብላቴናዎች ምግብ ማጋራቷን ግን እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ነገር ግን በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ውሻና ሰው ተጋርቶ አንድ ላይ ሲበላ ማየት የተለመደ ነው፡፡ በእርግጥ የዚችን ውሻ ያክል ፍቅር እንኳ ማን ሰጣቸው፡፡ ከውሻ የባስን መሆናችንን ሳስበው ዘገነነኝ፡፡

Monday, July 13, 2015

“ጠብሰው አንገረገቡኝ”








(ከአባቴ ተረቶች-፩)፡ ተረት ተረት...
በአንድ ወቅት አንድ ባልና ሚስት አንዲት ትንሽ የገጠር መንደር ውስጥ ይኖሩ ነበር፡፡ ባል ሁልጊዜም ራቅ ካለ ቦታ ስንቅ ቋጥሮ፣ ውሃ በኮዳ አንጠልጥሎ ጥዋት ለእርሻ የወጣ ማታ ይመለሳል፡፡ሚስት ከቤቱ ስራ በተጨማሪ አንዳንድ ጊዜ ባልንም በጉልጓሎና በአረም ታግዛለች፡፡ ባል ብዙ ጊዜ  በስራና በመንገዱ እርቀት ደክሞት ይመጣል፡፡ በዚህም ምክንያት የወንድነት ስራውን መዘንጋት ጀመረ፡፡ በዚህ ክፍተት ስሜቷን ለባል መናገር ያፈረች ሚስት ቤት ለቤት ሲያውደለድል የሚውል አንድ ወስላታ የሰፈር ሰው አሽኮረመመችና ወሸመች (ጠበሰች)፡፡ ውሽምየ የባልን ወደ ስራ መሄድ ሰልሎ ቤት ይመጣና ሲያስደግስ ይውላል፡፡ የልቧንም አድርሷት ይሄዳል፡፡ ምስኪን ባል ከውሽምየ የተረፈውን ቀማምሶ እንደለመደበት ድብን ብሎ ይተኛል፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ ሚስት ለባል ያላት ፍቅር እየቀነሰና የሚዘጋጅለት ምግብም በአይነትና በመጠን እየወረደ ሲመጣ ባልዬም መጠርጠር ጀመረ፡፡ ጎረቤት መጠየቅ አልፈለገም፡፡ እራሱ አንድ ቀን በአሳቻ ለመያዝ አሰበ፡፡

Friday, July 10, 2015

ህሊና ብቻ ነው!

ጥላቻ ከፍቅር
መኖር ካለመኖር
ፅድቅና ኩነኔ
ፍርሀትና ወኔ
እውነትና ሐሰት
መውደድና መጥላት
ጤና ከበሽታ
ሀዘን ከደስታ
መማር ካለመማር
እብደትም ከስካር፤
 ተቀላቅለውብኝ
ድንበሩ ጠፍቶብኝ

Monday, July 6, 2015

ግብረ ሰዶም ወ አሜሪካ



የሰዶምና ገሞራ የጥጋብ ኃጢያት፣ የምዕራባውያን የስልጣኔ ዝቅጠት፣ የዓለማችን ታላቁ የተፈጥሮ ክህደት የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ “ሌዝቢያን፣ ጋይ፣ ባይሴክሽዋል እና ትራንስጀንደር” (LGBT)፡፡ እነሆ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ እ.ኤ.አ ሰኔ 29፣ 2015 ግብረሰዶምን የሚፈቅድ አዋጅ በይፋ በሁሉም የአሜሪካ ግዛቶች ማፅደቃቸውን ተከትሎ ምዕራባውያን የደስታ ሲቃ ተናንቋቸው ሰንብቷል፡፡1 ናይጀሪያን በመሳሰሉ አንዳንድ የአፍሪካ አገሮች የሚገኙ ዜጎችም ይህንን ዜና ወደ ሀገራቸው ማስተጋባት ጀምረዋል፡፡ በሌላ በኩል የዙምባቡዌው ፕሬዘዳንት ሮበርት ሙጋቤ ግብረሰዶምን በመቃወም ከምዕራባውያን ጋር ቀዝቃዛ ጦርነት ከፍተው የዓለም መነጋገሪያ ሁነው ሰንብተዋል፡፡ በአገራችን ኢትዮጵያም ደስታውን መስቀል አደባባይ ወጦ የገለጠ ወራዳ ባይኖረም በማህበራዊ ሚዲያ አደባባይ ግን ኢትዮጵያዊና ሀበሻዊ ባልሆነ ቃና ይህንን እርኩስ ተግባር ደግፈው የውስጣቸውን የተነፈሱ አልጠፉም፡፡

Thursday, July 2, 2015

የመምህራን ቀልዶችና ምሳሌዎች

መምህራን አንዳንዴ ተማሪ ለጠየቀው ጥያቄ መልስ መስጠት ሲያቅታቸው ወይም ሲደብራቸው ቀልድ አዘል የሆነ መልስ ይመልሳሉ፡፡
ቀልድ አንድ፡ እስኪ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የሂሳብ መምህር ከነበሩትና ተማሪው ትዕቢተኛ ናቸው ከሚላቸው ከጋሽ _______እንጀምር፡፡
ተማሪ፡ ጋሸ
መምህር፡ አቤት
ተማሪ፡ የሜትርና የኪሎ ሜትር ዝምድናቸው ምንድን ነው፡፡
መምህር፡ አታውቀውም እንዴ፣ የአክስትና የአጎት ልጆች ናቸው፡፡

Saturday, June 27, 2015

MADIBA_LONG WALK TO FREEDOM

 Click to get the book in PDF
Nelson Mandela (Madiba), one of the great democratic leaders in the world had said many things about his stay in Ethiopia. His started the appreciation with the black Ethiopian pilot:
“We put down briefly in Khartoum, where we changed to an Ethiopian Airways flight to Addis. Here I experienced a rather strange sensation. As I was boarding the plane, I saw that the pilot was black. I had never seen a black pilot before, and the instant I did I had to quell my panic. How could a black man fly an airplane? But a moment later I caught myself: I had fallen into the apartheid mind-set, thinking Africans were inferior and that flying was a white man’s job. I sat back in my seat, and chided myself for such thoughts. Once we were in the air, I lost my nervousness and studied the geography of Ethiopia, thinking how guerrilla forces hid in these very forests to fight the Italian imperialists.”

Sunday, June 21, 2015

የአስመሳዮች ዘመን

                   አስመሳይ ካልሆንህ አታንበው? ከጀመርኸው ጨርሰው!
አንድ ታሪክ ልንገራችሁ፡፡ እውነተኛ ታሪክ፡፡ በአንድ ወቅት በሰሜን ኢትዮጵያ ከሚገኙ ገዳማት ወደ አንዱ ብቅ ብየ ነበር፡፡ አንድ አባት የማግኘት ዕድሉ ገጥሞኝ ነበር፡፡ አባ ገ/ሕይወት ይባላሉ፡፡ በመንፈስ የበቁ፣ ለፀሎት የነቁ አባት፡፡ አባ አንድ ታሪክ ነገሩኝ፡፡ መግቢያውን ላለማገመድ ወደ ታሪኩ ልጋባ፡፡ አባ እንዲህ ሲሉ ጀመሩ፡፡
“አንድ ደግ ገበሬ ነበረ፡፡ እንደ ደጉ አብርሃም እንግዳ ተቀባይ ነበር፡፡ እንግዳ ይቀበላል፣ ያበላል፣ ያጠጣል፣ ያሳድራል፣ መንገድ አሳይቶ ይሸኛል፡፡ አንድ ቀን ግን ያልተጠበቀ ነገር ገጠመው፡፡ እንደተለመደው ሶስት ወጣቶች ከሩቅ ሀገር እንደመጡ ለዚህ ደግ ገበሬ አስረድተው “ የእግዜር እንግዳ” ነን አሳድሩን ሲሉ ተማጠኑ፡፡ "  አባ ድምፃቸውን ጠራርገው ትረካቸውን ቀጠሉ፡፡

Sunday, June 14, 2015

ዳማካሴ

                 click here for PDF
የኢትዮጵያ የባህል ህክምና ታሪክ ሲነሳ በፈዋሽነቱና በተደራሽነቱ በቀዳሚነት ብቅ የሚለው ዳማካሴ ነው፡፡የኢትዮጵያውያን ፈውስ፣ የረጅም ዘመን የጤና ወዳጅ-ዳመካሴ፡፡ታሪክ ጠቅስን መረጃ ተንተርስን መናገር ባንችልም ኢትዮጵያ ውስጥ በባህል ህክምና ባለሙያዎች ለፈውስ ከተገኙት ቀዳሚ ቅጠሎች አንዱ ዳማካሴ መሆኑን መገመት አያዳግትም፡፡አንድ ሰው የህመም  ስሜት ሲሰማው የሰፈር አዛውንቶች የሚሰጡት የመጀመሪያው ምክር ዳማካሴ ውሰድበት ነው፡፡ በመሆኑም ዳማካሴ፤ ጤና አዳምን፣ ፌጦንና ነጭ ሽንኩርትን አስከትሎ በኢትዮጵያውያን ዘንድ በፈዋሽነቱና በተደራሽነቱ በቀዳሚነት ይታወቃል፤ ምንም እንኳ የቅጠሉ ዝርያና አበቃቀል ከቦታ ቦታ ቢለያያም፡፡ ታላቁ ገጣሚና የወግ ቀማሪ በውቀቱ ስዩም “ኢትዮጵያዊ ነኝ” በተሰኘ ግጥሙ እንዲህ ሲል ተቀኝቷል፡፡
                                               ……………..                     
“ግትር ጠላቴን በአጭር አንካሴ
ራስ ምታቴን በዳማካሴ
ነቅዬ ምጥል
አገር በነገር የማብጠለጥል
ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡”
……………….
ዳማካሴ ከሌሎች የመድሀኒትነት ባህርይ ካላቸው ዕፅዋት ለየት ይላል፡፡ 

Sunday, June 7, 2015

›››የሐበሻ ጀብዶ›››የኢትዮጵያውን የነፃነት ተጋድሎ›››


                                        ለፒዲኤፍ ይህንን ይጫኑ
ኢትዮጵያዊ ነህ? ሐበሻ ነህ? ሐበሻ ከሆንክ መጀመሪያ የሐበሻ ጀብዶንና ቀይ አንበሳን አንብብ፡፡ የቅድመ አያትህ፣ የአያትህና የአባትህ ታሪክ ነው፡፡ ዘመን የማይሽረው የሀበሻ ወኔ፣ ችግር ማይበግረው ጀግንነት፣ ሀገር ወዳድነትና ዘላለማዊ የሆነ የወገን ፍቅር በቀይ ቀለም የተከተቡበት ድንቅ መፅሐፍ፡፡ ስለማንነትህና ስለ ዘርህ አትጨነቅ ብቻ ሀባሻ ሁን፡፡ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ፣ ወላይታ፣ትግሬ የትኛውንም የኢትዮጵያ ዘር ብትሆንም ይህ ያንተ የሀበሻው ታሪክ ነው፡፡ ቅድመ አያትህ፣ አያትህ፣ አባትህ ወይም ከወገኖችህ አንዱ አድዋ ነበር፤ ማይጨው ነበር፣ አቢ አዲ ነበር፣ መቀሌ ነበር፣ ኮረም ነበር፣ ተከዜ በረሃ ነበር፤ ኢትዮጵያን ከጠላት ሊታደግና ያልተበረዘ ማንነት ሊያወርስህ፡፡ አንተ የነዚያ ጀግኖች ውጤት ነህ፡፡ አጥንታቸውን ከስክሰው፣ ደማቸውን አፍሰው በከፈሉልህ መስዋትነት ቀና ብለህ የምትጓዝ ነፃ ትውልድ! አንበው ቢያንስ ማንነትህና ታሪክህ ነው! ማንነቱን በትክክል የተረዳና ታሪኩን የሚያውቅ ትውልድ ማንም በደነፋ ቁጥር አይበረግግም፤ ታሪክ ጠቅሶ መፅሐፍ አስደጉሶ ስለማንነቱ ይከራከራል እንጂ፡፡

የአሲምባ ፍቅር


ከውስጥ በገነፈለ ስሜት፣ በተመረጡ ውብ ቃላት፤ የተፃፈ ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ የፍቅርና የትግል ታሪክ፡፡ ባለታሪኩ እንዲህ ብሎ ይጀምራል፡

“ከልብ በመነጨ ፍቅርና ቁርጠኝነት በለጋ እድሜየ የጀመርኩት ጉዞ አቅጣጫውን የቀየረው ባላሰብኩት ሁኔታና ወቅት ነበረ፡፡ ማንኛውም ሰው በሁኔታዎች አስገዳጅነት ያላሰበበትንና አልሞ ያልመረጠውን ሕይወት እንደሚቀበል ሁሉ እኔም እጣ ፈንታዬን ከተቀበልኩና በመራኝ ጎዳና መንገድ ከጀመርኩ በርካታ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡”