Wednesday, January 13, 2016

"ለምን? ለምን? "

ለምን? ለምን? 
የአንድ ቃል ሰመመን
ከፊደሎች መክፋት
ደግሞ ከጎኑ ላይ ጥያቄ ምልክት?
የአንድምታው ግዝፈት 
እንደ ክፉ ደዌ አንጀት የሚጎትት
ለምን? ለምን? 
ለምን? መጠየቅ ከአፍ ላይ ቢቀልም
ለምን? ስትባል ግን ምላሽ አታገኝም
ቆይ ግን ለምን?
ይህ ሁሉ የሚሆን?
እኮ ለምን?
ቆይ ለምን?
....
አየህ! የለምን? ጋጋታ
ቤትም አይመታ
በለምን? ጥያቄ እውቀት ቢፈጠርም
አንተ ስጠይቅ ግን አንዳች መልስ የለውም
የሺ ለምን? ቃላት በአንድ ቢሰደሩ
በከንቱ ልፋት ነው መልስ የለም ባገሩ
......
ስለዚህ አንተ ሰው እህ.. ብለህ ከሰማህ
ለምን? ተውና መፍትሔውን ልንገርህ
.....
ለምን? ለምን? ብለህ-ለምን? ሳታበዛ
እሽ ብለህ እደር፣ ሆድህ እንዲሞላ-ፊትህ እንዲወዛ
[Zelalem T; January 12, 2016]

No comments:

Post a Comment