እንደ ዘበት ወርደን~ከ ትናንት አቀበት
ለመውጣት ስንጀምር~የዛሬን ቁልቁለት
ነገን መዳረሻ~መንታ መንገዱ ላይ
አንዲት እርጉዝ አለች~ከርቀት የምትታይ
ከመንታ ተወልዳ~መንታ በማርገዟ
መንታ መንገዱ ላይ~የበዛ መዘዟ፤
እነዚያም ልጆቿ፡
በማይታይ ህልም~በሰነቁት ተስፋ
ሰፊ ማህፀን ውስጥ~አንዱ አንዱን ሲገፋ
መቻቻል ተረግጦ~ጥላቻ ሲፋፋ
በመን’ቶ’ች ሽኩቻ~ነጠፈ ሰላሟ
በቃር በሲቃ ድምፅ~በረታ ህመሟ፤
እንዲህ እየሆነች
የስቃይን ፅዋ~በግፍ እየጠጣች
መንታ መንገዱ ላይ~ትውልድ ታምጣለች
በ ዘላለም ጥላሁን (የእናቱ ልጅ)
ጥር 09/ 2008 ዓ.ም
"«ሰፊ ማህፀን ውስጥ~አንዱ አንዱን ሲገፋ»" Dark, True, and touching.
ReplyDelete