እስራኤል ዘነፍስን~ ከኃጥያቱ ቀንበር
እስራኤል ዘስጋን~ ከ ምድር ቸነፈር
ያዳንሃቸው መሲዕ~አንተ ብላቴና
እኛንም አድነን~እባክህ ቶሎ ና
አየህ ብላቴናው፡
እስራኤል ዘስጋን~ ከ ምድር ቸነፈር
ያዳንሃቸው መሲዕ~አንተ ብላቴና
እኛንም አድነን~እባክህ ቶሎ ና
አየህ ብላቴናው፡
ሰማይ ተለጉሞ
ምድር ሆዷ ታሞ
በደረቀ ማሳ~በደረቀ ተስፋምድር ሆዷ ታሞ
ሺ ወይፈን~ተኝቶ ቀኑን እየገፋ
ምነው ምን በደልንህ~ድምፅህ ሁሉ ጠፋ
…………
አየህ ብላቴናው፡
የረሃብ ሰቀቀኑ
የችግር ዲደኑ
አብሮን ቢራመድም~እኩል ከዘመኑ
አራሽ ገበሬ ግን~አልተወም መጥመዱን
በደከመ በሬ~በደከመ ወይፈን፤
…..
እኒያም ምስኪን በሬዎች፡
ሳይፈቅዱ ተወልደው
ሳይወዱ ተጠምደው
ከማሳው ተኝተው~ይኸው ስራ ፈቱ
የሚላስ ልመና~ወደ አንተ ቃተቱ
……..
እንዲህ እየሆነ
እንዲያም እየሆነ
የትናንት ማንነት እየመነመነ
በሬዎች ደከሙ~ቀንበሩ ከበደ
በኮሩ መሳሳት~ጫንቃቸው ነደደ
በገራፊው ጉልበት~ጀርባቸው ተላጠ
በመንበርከክ ብዛት~እግራቸው ጎበጠ
…..
እናም አንተ መሲህ
ስማን ከወዴት ነህ?
እንዴት ዝም ትላለህ?
ይሄን ሁሉ እያህ፤
የችግር ዲደኑ
አብሮን ቢራመድም~እኩል ከዘመኑ
አራሽ ገበሬ ግን~አልተወም መጥመዱን
በደከመ በሬ~በደከመ ወይፈን፤
…..
እኒያም ምስኪን በሬዎች፡
ሳይፈቅዱ ተወልደው
ሳይወዱ ተጠምደው
ከማሳው ተኝተው~ይኸው ስራ ፈቱ
የሚላስ ልመና~ወደ አንተ ቃተቱ
……..
እንዲህ እየሆነ
እንዲያም እየሆነ
የትናንት ማንነት እየመነመነ
በሬዎች ደከሙ~ቀንበሩ ከበደ
በኮሩ መሳሳት~ጫንቃቸው ነደደ
በገራፊው ጉልበት~ጀርባቸው ተላጠ
በመንበርከክ ብዛት~እግራቸው ጎበጠ
…..
እናም አንተ መሲህ
ስማን ከወዴት ነህ?
እንዴት ዝም ትላለህ?
ይሄን ሁሉ እያህ፤
የዘገየህ ምነው?
አራሹን ተው በለው~ወይ በሬውን ፍታው
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
አራሹን ተው በለው~ወይ በሬውን ፍታው
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
[ዘላለም☞የእናቱ ልጅ]; January 14, 2016
በገራፊው ጉልበት~ጀርባቸው ተላጠ
ReplyDeleteበመንበርከክ ብዛት~እግራቸው ጎበጠ
አራሹን ተው በለው~ወይ በሬውን ፍታው
ReplyDelete