እንደምን አላችሁ፡ እስኪ ወጋችንን እንጠርቅ፡፡ ወጋችንን ያቆምነው ከ45 ዓመቱ ጓደኛዬ ላይ ነው፡፡ ልቀጥል……
ምነው ጋሸ ያ ነገር እምቢ አለህ እንዴ?
“ኧረ!…..አንተ!……እሱማ…………ጥዋት ጥዋት የአባቴን ጎራዴ እየመሰለ እያስቸገረኝ ነው” አለ ደስ በሚል ፈገግታ፡፡ ደሃ ፈገግ ሲል እንዴት ደስ ይላል መሰላችሁ፡፡
ቀላል አልሳቅሁም፡፡ ምንም እንኳ “ጥዋት ጥዋት” የሚሉት ቃላት ባይዋጡልኝም፤ ሌላ ጊዜስ ብዬ ለመጠየቅ ግን ድፍረቱን አጣሁ፡፡
ያም ሆነ ይህ ጎራዴ መምሰሉ የስሜት ይሁን የሽንት ባይታወቅም፤ የጓደኛዬ መልስ ወንዶቹ እስከ 45 ዓመት ድረስ ጥሩ ተስፋ እንዳላቸው የሚያበስር ነው፡፡
ታዲያ ለምን አታገባም፣ እንዴት ለአንተ የምትሆን ሴት ታጣለህ?
“ኧረ እሱስ አላጣሁም፡ እኔ ምመጥናት ሴት አትገኝም ነው እንጂ?”
ምን ማለት ነው እሰኪ አብራራልኝ?





