Wednesday, September 12, 2018

ሀሳብና ሰብዕና ቢለያዩስ?


ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም ለኢትዮጵያ ውለታ ከዋሉ አንጋፋ ምሁራን ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡ ከአፄው እስከ አሁኑ ስርዓት ድረስ የታሪክ ማጣቀሻ ሆነው በህይወት ካሉ ምሁራን ውስጥ አንዱ እኒህ ጎምቱ የታሪክ ምሁር ናቸው፡፡ በ1960ዎች ኢትዮጵያ በረሃብ አለንጋ ስትገረፍ ከፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ እና መሰል የወገን ተቆርቋሪዎች ጋር በመሆን ታላቅ ውለታ ውለዋል፡፡ እኒህ ምሁር ‹‹አማራ የሚባል ብሔር/ ነገድ የለም›› በሚል አቋማቸው አማራ ነህ ተብሎ እንደ ኑግ በየቦታው እየተሰለቀ በነበረው ወጣት ዘንድ ትልቅ ተቃውሞ ሲሰነዘርባቸው እንደቆዬ ሁላችንም የምናውቀው ነው፡፡ የአሁኑ ዘመን ትውልድ ከእሳቸው አቋም ጋር መስማማት ቢሳነው በማንም መፍረድ አይቻልም፡፡ ምክንያቱም በእሳቸው ትርክት እና በእኛ ትርክት መካከል ትልቅ የታሪክ መጋረጃ አለ፡፡ የታሪክ መጋረጃው ደግሞ ሰው በሰውነቱ ሳይሆን የደምና የአጥንቱን መሰረት ተከትሎ በዘውጌ ፖለቲካ እንዲተሳሰር ተደርጎ የተዘጋጀ መጥፎ መጋረጃ ነው፡፡ ፕ/ር መስፍን በሀሳባቸው ልክ ሆኑም አልሆኑም፣ ሰብዕናቸው መከበር አለበት፡፡ 

Monday, September 10, 2018

‹‹በደሃ እናቶች እምባና በወጣቶች ደም-የስልጣን ቁማር መጫወት ይብቃ!››

(የአዲስ ዓመት መልዕክት)
 
የፕ/ር ብርሃኑ እናት ልጃቸውን ቦሌ ተቀብለው ለመሳም ታደሉ፣ የሌሎችም እንዲሁ፡፡ ያም ሆኖ ግን ስስታቸውን ምስሉ ይገልፀዋል፡፡ እናት ምንም ቢሆን እናት ናት፡፡ ለሴኮንድም የልጇን መከራ መስማት አትፈልግም፡፡ ከጀርባ ግን ታላቅ የእምባ ጎርፍ ይታየኛል፡፡ ልጆቻቸውን በአደባባይ በአገዛዙ በግፍ የተነጠቁ እናቶች፣ መሰል ምስሎችን ሲያዩ የሚያነቡት እምባ!  ከአንጀት ተንሰቅስቆ የሚወርድ ትኩስ አምባ! በበቃሽ የማይቆም እምባ!

Saturday, August 18, 2018

‹‹የአገው ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት›› የአገው ህዝብ ወይስ የፖለቲካ ቁማርተኞች ጥያቄ?


                         (ሳይቃጠል በቅጠል፤ በዘላለም ጥላሁን) Must read!
እስኪ ልጻፍ፡፡ ዛሬ ካልጻፍሁ መቼ ልፅፍ ነው፡፡ እናቴ ጓዳውን፣ አባቴ ጋጣውን ተከፋፍለው እስኪለያዩ መጠበቅ የለብኝም፡፡ ምን ማለት እንደፈለግሁ አዊ ዞን የሚኖሩ ወጣቶች ይረዱኛል፡፡ ወደ ዋናው ነጥብ ከመግባቴ በፊት አንዴ ጠብቁኝ ‹‹የዘር ፖለቲካን ሰፈር ድረስ የዘራውን ሰው ሁሉ ልራገም››….‹‹ልጅ አይውጣላችሁ!›› ጨርሻለሁ!.....

እኔ ግን ይች ሀገር ታሳዝነኛለች፡፡ እንደ ዶሮ ብልት ተከፋፍላ ተከፋፍላ ማለቋ ነው፡፡ ይህን ጉዳይ ዛሬ ማንሳት የፈለግሁት ‹‹ጉዳዩ እየገፋ ስለመጣና የእዚህ ጉዳይ አራማጆች ዛሬ አዲስ አበባ ‹‹ራስ አምባ ሆቴል ›› ሲመክሩ ስለዋሉ ነው››

አሁን ‹‹አገው ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት›› የሚሆነው በየት በኩል ነው?……..ይህን ስል የአገውን ማህበረሰብ ማንነት ማሳነሴ አይደለም፡፡ ራሴን ማሳነስ ስለሚሆን፡፡ ሃቁ የአገው ህዝብ የራሱ ቋንቋ አለው፡፡ አብሮት ከሚኖረው አገውኛ ከማይናገረው ህዝብ የተለዬ ባህል እና ትውፊት ግን የለውም፡፡ ለጊዜው ትኩረቴን ‹‹የአዊ ዞን ህዝብ›› ላይ ላደርግ፡፡ ተከተሉኝ፡፡ ወደ ጉዳዩ ለመንደርደሪያ እንዲሆን እና ምሁራን ጉዳዩን በትኩረት እንዲያዩት ፍንጭ ለመስጠት ያህል እንዳንድ አሃዛዊ መረጃዎችን ማየቱ ጠቃሚ ነው፡፡

Thursday, August 16, 2018

የአዊ (አገው ምድር) የፈረስ ጉግስ ባህል

ከ70 ዓመታት በላይ የሆነው የ‹‹አዊ የፈረስ ማህበር›› ባህሉን ጠብቆ በማቆየቱ በ‹‹ቅርስና ባህል ዘርፍ›› ለዘንድሮው የ‹በጎ ሰው ሽልማት› ከተመረጡ ሶስት ዕጩዎች አንዱ ሁኗል፡፡ የፈረስ ጉግስ ባህሉ ዝም ብሎ ለመዝናኛ የሚሆን ብቻ አይደለም፡፡ የማህበራዊ ስነ-ሰብ አጥኝዎች በአግባቡ ባያጠኑትም ቅሉ፣ የራሱ ታሪካዊ አመጣጥ አለው፡፡ ከታሪካዊ እውነታዎች እና አሁን የፈረስ ጉግስ ከሚዘወተርባቸው ሁነቶች ተነስቶ ሶስት መላምቶችን መገመት ይቻላል፡፡
1ኛ) አንደኛው ከመከረኛው ጦርነት ጋር የተያያዘ ነው፡፡
መኪና፣ አውሮፕላን እና ዘመናዊ የጦር መሳሪያ በሌለበት ዘመን አብዛኛው የእርስ በርስም ሆነ ከውጭ ጠላት ጋር ይደረጉ የነበሩ ውጊያዎች የሚከወኑት በጦር እና ጎራዴ በሚደረግ የጨበጣ ውጊያ ነው፡፡ የጨበጣ ውጊያን በድል ለማጠናቀቅ ደግሞ ፈረስ ትልቅ አስተዋፅኦ ነበረው፡፡ የአድዋ ጦርነት በፈረስ አጋዥነት ለድል እንደበቃ ብዙ ማሳያዎች አሉ፡፡ ለ‹‹ባንዳ እርግማን›› አፋችን የሾለውን ያህል ‹‹ፈረሶችን›› አመስግነናቸው አናውቅም፡፡ ለኢትዮጵያ ነፃነት ከ ‹‹ባንዳዎች›› እና ‹‹ከፈሪዎች›› ይልቅ ፈረስ የነበረው አስተዋፅኦ ታላቅ ነው፡፡ ፈረስ ለቀደሙ ነገስታት ባለውለታ፣ የህይወታቸው አለኝታ ነበር፡፡ ለዚህም ይመስላል ብዙ ነገስታት ከ አባታቸው ይልቅ የፈረሳቸው ስም ጎልቶ የሚወጣው፡፡ ለምሳሌ የአፄ ቴወድሮስን ብናነሳ፡
‹‹ታጠቅ ብሎ ፈረስ፣ ካሳ ብሎ ስም
አርብ አርብ ይሸበራል፣ ኢየሩሳሌም››……ተብሎ ተገጥሞላቸዋል፡፡