የተከበራችሁ የሀገራችን ህዝቦች ሆይ!
ምስጋና ከሚቀበል ሰው ይልቅ ምስጋና የሚሰጥ ታላቅ ነው! ያለ ጥርጥር ይህንን እንረዳለን፡፡ ባለፉት ሶስት ወራት በሀገራችን እየታየ ያለው የለውጥ ጭላንጭል፣ አሁን የሀገራችን ህዝብ እየሰጠን ካለው ወሰን አልባ ድጋፍ እና ፍቅር ጋር የሚወዳደር እንዳልሆነ ብንገነዘብም መንግስት ይሄንን ድጋፍ ፣ ፍቅር ፣ ክብር እና አለኝታነት ለተሰሩ ስራዎች እንደተሰጠ ምስጋና ብቻ ሳይሆን በቀጣይ እንሰራቸው ዘንድ ለሚገቡን በርካታ ስራዎች ተግባራዊነት የተላለፈ የአደራ መልእክት እንዲሁም የአጋርነት ማሳያ አድርጎ በመቁጠር ከምን ጊዜውም በላይ በፍጹም ቁርጠኝነት እና ትጋት ለማገልገል በጽናት ይሰራል፡፡









