Saturday, October 24, 2015

“የእኔና የአንቺ ዓለም”

ለአንዱ ማግኘት ጣጣ 
ከውስኪ ሰገነት ስካር ላይ ሲወጣ
ለአንዱ ማጣት ዕዳ
ኑሮና ህይወቱ የቆሻሻ ገንዳ፤
አንዱ ጉልበተኛ የተጣላ ከእግዜር
ሰውን እንደ ሽንኩርት በስለት ሚመትር
ሌላው እረሃብተኛ
አገጩን ጭኑ ላይ ደግፎ የተኛ፤
አንዳንዱ ቄንጠኛ
በልዑል ሰገነት ልጁን የሚያስተኛ
ሌላው ዕድለቢስ
ከመላጣ እስፋልት ላይ በውርጭ የሚጠበስ፤
እዚያ ዲሞክራሲ 
ነፃነት በኬሻ ሁሉም ሰው ሃያሲ
እዚ አውቶክራሲ
ትንሽ ሰው ደራሲ፣ እራሱ ሃያሲ፤
ማዶ ቀዝቃዛ ብርድ 
የበረዶ ክምር ሰውነት የሚያርድ
ወዲህ የእሳት ምድር 
ጠብታ አልባ መሬት የሚያቃጥል ሐሩር፤
ይች ናት እንግዲህ…………
እግዜሩ ሲፈጥር መከራ ያየባት
በነጭ ወረቀት ላይ በ እርሳስ የነደፋት፤
ከእሱ ተቀብሎ ምድራዊው ፈላስፋ
የብዕሩን ቀለም ምራቅ እየተፋ፤
አጥፍቶ የሳላት በዥንጉርጉር ቀለም
ይች ናት እንግዲህ የእኔና የአንቺ ዓለም
!
          [ዘላለም☞የእናቱ ልጅ]

          ጥቅምት 11፣ 2007 ዓ.ም

Wednesday, October 21, 2015

'የሰንደቅዓላማ ቀን'ን…በበርጫ

(ከ'አጠቃ'ዎች አንደበት)

ከሆነ ሰፈር ወደ ፒያሳ እየሄድሁ ነው፡፡ አቤት እነዚህ እረዳቶች ደግሞ….ሳንቲም ጨምር….ጠጋ በል…የዕቃ ይህን ያክል ትከፍላለህ….ከዚይ ላይ አይቆምም! አሁን አሁን ታክሲ ውስጥ ያለው ጭቅጭቅ ስለመመረረኝ፤ ቅርብ ከሆነ በሁለት አግሬ ማቅጠን ጀምሬአለሁ፡፡ ራቅ ካለብኝ ደግሞ ጆሮዬ ውስጥ የምጨምረው ጥጥ ይዞ መግባት ጀመርሁ፡፡ ታዲያ ዛሬም እንደተለመደው እርዳቱ እንደ ሐምሌ መብረቅ ተሳፋሪ ላይ መጮህ ሲጀምር ቶሎ ብዬ መከላከያ ጋሻዬን ጆሮዬ ውሰጥ ሰካሁ፡፡ ምን ላድርግ ጆሮዬ ገና ብዙ ክፉ ደግ መስማት አለባት-ቢጠቅማትም ባይጠቅማትም፡፡ ታዲያ በዚህ መሃል ፀጉሩን እንደ ደረቀ ተክል ቅርንጫፍ ያንጨበረረ አንድ ወጣት ከጎኔ መጦ ቁጭ አለ፡፡ በአካል ጠጋ አልሁለት-ሶስተኛ መሆኑ ነው፡፡ በሃሳብ መጠጋጋት ግን በአካል እንደ መጠጋጋት ቀላል አይደልም፡፡ አይገርምም! በአካል እንደምንጠጋጋው በሃሳብም ብንጠጋጋ ምን አይነት ኢትዮጵያ ትፈጠር ነበር? ተውት በቃ፡፡ ይቅርታ ወደ ልጁ ልመለስ፡፡ ታክሲው በአንዴ ከህዝባዊ ሽታ ወደ ጫትና ሲጋራ ማዓዛ ተለወጠ፡፡ ደግሞ ጫትና ሲጋራ ሲቀላቀሉ እንዴት ነው የሚሸቱት!

Monday, October 19, 2015

ለምን አታገባም? (ክፍል-01)

ባለፉት ድፍን ሃያ አመታት በት/ቤት ህይወቴ ከተጠየቅኋቸው ጥያቄዎች ቀጥሎ በብዛት የተጠየቅሁት ጥያቄ “ለምን አታገባም?” የሚለውን ጥያቄ ነው፡፡ ጎበዝ ማግባት ግን “ለምን አታገባም?” የሚለውን ጥያቄ እንደመጠየቅ ቀላል አይደለም፡፡ የሂሳብን፣ የፊዚክስን፣ የኬሚስትሪን ጥያቄ ፎርሙላውን በመጠቀም መፍትሔ መፈለግ ወይም “ፕሩፍ” ማድረግ ይቻላል፡፡ “አግባ” የሚለውን ጥያቄ ግን ሚስት አግብቶ ለመመለስ ፎርሙላ አልባ የሆኑ ውስብስብ ጥያቄዎችን መመለስ ያስፈልጋል፡፡ ሰው “አግባ አግባ…..” ብሎ መስመር ውሰጥ ያስገባህና ነገ ግራ ስትጋባ “አይዞህ ቻለው” ብሎህ የፌዝ ሳቅ እየሳቀ ይሸሽሃል፡፡ ምሽት ላይ “ጉሮ ወሸባን” አስጨፍሮ በነጋታው ጥዋት ጫጉላ ሳይፈርስ የነገር ጦር ከመማዘዝ ዝግ ብሎ አስቦ፣ አጥንቶ ማግባት ይሻላል፡፡ ስንቶች ናቸው ተጋብተው አመት ሳይደፍኑ የሚፋቱት፤ ስለዚህ እኔ ረጋ ብዬ፣ በደንብ አጥንቼ ነው የማገባ ብየ እከራከራለሁ፡፡

አንድኛው መጦ ደግሞ “የአዲስ አበባ ልጅ እንዳታገባ” አለኝ፡፡
ኮስተር ብዬ ምነው አልኩት?

Monday, October 12, 2015

[ይድረስ ለአፍሪካ]


“እንዴት ነሽ ሀገሬ እንዴት ነሽ አፍሪካ
የምስኪኖች ቋጥኝ የክፉዎች ዋርካ”
የምትል ግጥም ፅፌ ልልክልሽ አስቤ ነበር፡፡ ነገር ግን አንዱ አድርባይ አጎብዳጅ ስም አጠፋህ ብሎ ጆካ እንዳይለይ ብዬ ስለፈራሁ ለስለስ ባለ አማርዚኛ የሰላምታ ደብዳቤየን ልልክልሽ አሰብሁ፡፡ አኔ ምለው አፍሪካ እንዴት ነሽ ባያሌው? ኑሮ፣ ጤና እንዴት ነው?…ይሄ ፈረንጆቹ “undefined word” የሚሉትን ቃል እንዳትጠቀሚ፡፡ ማለቴ “ምንም አይል”፣ “cool” ምናምን እንዳትይኝ፡፡ እናቴ እኛም “ምንም አይል!” እያልን ነው ኑሮ ምናምንቴ አድርጎን የሄደው፡፡ አሁንማ “ኑሮ” የሚለውን ቃል ሲሰማ ሁሉ የሚበረግግ ምስኪን አፈር ነው፡፡ ብዙ ነው ማለቴ ነው፡፡ እባክሽ ደግሞ ተረት እንዳታወሪ፡፡ ይሄ ምንድነው እሱ…… “ኑሮ ካሉት መቃብር ይሞቃል” ….ምናምን እንዳትይ፡፡

Thursday, October 8, 2015

[“የእንቅልፍ ዘመን”]









“ድሃ እንዳትሆን እንቅልፍህን አትውደድ” 
       መፅሐፈ ምሳሌ 20፡13



ጠቢቡ ሰለሞን በዚህ ዘመን ቢኖር ኖሮ ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ “የድሃ ድሃ እንዳትሆኑ እንቅልፋችሁን አትውደዱ” ብሎ ይናገር ነበር፡፡ እነሆ ይች ዓለም የበረዶ ዘመን፣ የነሃስ ዘመን፣የብረት ዘመን፣ የጨለማው ዘመን፣ የአብዮት ዘመን፣ የጦርነት ዘመን ፣ የሳይንስ ዘመን እያለች ብዙ አያሌ ዘመኖችን አሳልፋለች፡፡ እነሆ የእንቅልፍ ዘመን ደረሰ! እናት አህጉር አፍሪካ የ 50 ዓመት መፃኢ ራዕይዋን የምታሳካበት የስራ ዘመን ሳይሆን በድጋሜ ተኝተን ቅኝ የምንገዛበት የ "እንቅልፍ ዘመን" ውስጥ የገባች ይመስላል፡፡ ድህነት፣ ረሃብ፣ በሽታ፣ ጦርነት፣ ብጥብጥና ጥላቻ አፍሪካን ቅኝ የሚገዙበት የእንቅልፍ ዘመን!

Tuesday, September 29, 2015

[["ጎርፍ"]]

በጋ ዘመን አልፎ
                        ሊተካ ሲል ክረምት
በደረቀው መሬት
ጠል ሊወርድበት
የመኸሩ በኩር
ሲገባ ግንቦት ወር
በጠራው ሰማይ ስር፤

Saturday, September 26, 2015

“ጴጥሮስ ያችን ሰዓት”

(ዛሬም ጀብራሬዎች በሐውልቱ እየሸኙ ነው)
ታላቁ ባለቅኔና የተውኔት አዘጋጅ ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ዘመን ተሻጋሪ የሆነችውን “ጴጥሮስ ያችን ሰዓት” የምትለዋን ግጥም የፃፈው፡ አንድ ቀን ምሽት ከማዘጋጃ ቤት ሲወጣ ባየው ትዕይንት ምክንያት ነው፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡ ፀጋዬ ገ/መድህን ከማዘጋጃ ቤት እንደወጣ ቁልቁል ወደ አቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ሲያመራ አንድ ጀብራሬ (በሎሬቱ አነጋገር) ከአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ላይ ሸንቱን ሲሸና ተመለከተ፡፡ ፀጋዬም በደም ፍላት ወደ ጀብራሬው ተንደረደረ፡፡ ጀብራሬው ግን “አንተ ድንጋይ እሸናብሃለሁ፡፡ ድንጋይ ነህ …. ድንጋይ ነህ ….” እያለ በሐውልቱ ላይ ይሸናል፡፡ በዚህ ሰዓት ነበር ሎሬቱ “ጴጥሮስ ድንጋይ አይደለም” ብሎ ጀብራሬውን በደም ፍላት ዘሎ ያነቀው፡፡ ከዚያም አብረውት የነበሩት ሰዎች ገላገሉትና እየተብሰከሰከ አራት ኪሎን ተሻግሮ ቀበና ገባ፡፡

Wednesday, September 23, 2015

“ለምን አለቅሳለሁ!”

እስከመቼ ለቅሶ
እስከመቼ እምባ
ዘመን ተቀይሮ
      የሳቅ ቀን ላይገባ
የሚያስለቀስ እንጂ
      ሀዘን የሚያጠፋ
ተስፋ ጨፍላቂ እንጂ
       ሚመፀውት ተስፋ፤
በሌለበት ሀገር
በግፍ በጥላቻ በቀለጠ መንደር
የዓለምን እርኩሰት ክፋቷን እያሰብሁ
በነጋ በጠባ ለምን አለቅሳለሁ?

Thursday, September 10, 2015

አስገራሚዋ ብላቴና (The Miracle Teenager)_ክፍል ፪

               በመጨረሻም ፌስቡክ ተጠቃሚዋ ስምረትና አሁን ያለችበት ሁኔታ !
ከአመታት በኋላ በቀጠሯችን መሰረት ከተወዳጇ ስምረት ጋር ተገናኘን፡፡ የተገናኘነው ከአመታት በፊት አውርተንበት የነበረው ቦታ መሆኑ ሁለታችንንም ትልቅ ትዝታ ላይ ጥሎናል!
ከቀጠሯችን ውጭ ይዛቸው የመጣቻቸው ሦስት ሴት ልጆች ትኩረቴን ስበውታል፡፡ በአንድ አይነት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሦስት ዕንቁዎች !! የስምረትን አስበልጬ ከሁሎችም ጋር ሞቅ ያለ ሰላምታ ከተለዋወጥኩ በኋላ ስራዬን ጀመርኩ፡፡
«ባለ ራዕይዋ ስምረት ይታይህ፣ እንኳን በድጋሜ ለመገናኘት/ለመተያዬት አበቃን»
«(
ሳቅ…) እግዚአብሄር የተመሰገነ ይሁን… በድጋሜ ስላገኘሁህ እኔም በጣም ደስ ብሎኛል !»
«
እሽ ወይዘሪት ስምረት… ነው ወይንስ ወይዘሮ ይሆን ? በሚገርም ሁኔታ ተለውጠሻል፣ ትልቅ ሰው ሁነሻል…ሶስቱ አብረውሽ የማያቸው መንትያ ሴቶችስ ልጆችሽ ይሆኑ ?»