በቤተክርስቲያኗ ህግ መሰረት ማህበረ ቅዱሳን ከ ተፈቀደለት መስመር ከወጣ፤ መስተካከል ያለባቸውን ጉዳዮች በዝርዝር አውጥቶ ማየትና የእርምት እርምጃ መውሰድ የሲኖዱሱ ጉባኤ ስልጣን ነው፡፡ ይህ ከሆነ ማኅበረ
ቅዱሳን ለቤተክርስቲያኗ ስጋት የሚሆንበት አንዳችም መንገድ አይታየኝም፡፡ ከዚህ ባለፈ ከ ሲኖዶሱ እውቅና ውጭ በተለያዩ አካላት
“ሾላ በድፍን” የሚደረጉ ዘመቻዎች የምዕመናንን ሰላም ከማወክ ያለፈ የረባ ፋይዳ ይኖራቸዋል ብዬ አላስብም፡፡ በሌላ በኩል ግን “ጥንታዊ የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ለማደስ” በሚል ተልዕኮ በየቀኑ ለሚፈለፈሉ ምዕራብ ወለድ ሃይማኖቶች ከሆነ አሁንም ቢሆን ማኅበረ ቅዱሳን ስጋት ነው፡፡
Labels
- ሐይማኖት (Religion) (8)
- ማህበራዊ ጉዳይ (Social Affair) (42)
- ሳይንስና ቴክኖሎጂ (Science and Technology) (4)
- ባህል (Culture) (11)
- ታሪክ (History) (20)
- ከመፅሐፍት ዓለም (from books) (6)
- የጉዞ ማስታወሻ (Journey’s log) (4)
- ግጥም (Poam) (44)
- ጤና (Health) (3)
Wednesday, March 30, 2016
Monday, March 28, 2016
በ እንተ “ማኅበረ ቅዱሳን”: ክፍል_1
(ትዝብትና ነፃ አስተያየት)
ማኅበረ ቅዱሳን ማን ነው? መች ተመሰረተ? ዓላማው ምንድን ነው? ለ ቤተክርስቲያን ምን አበረከተ? ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ለምን ጠሉት? የሁሉም ቀስትስ ለምን ወደ ማኅበረ ቅዱሳን አነጣጠረ? እውን ማኅበረ ቅዱሳን ለቤተክርሰቲያን ስጋት ወይስ አቃቤ?
(የውጭ አካላትን ጣልቃ ገብነት ለጊዜው ተወት አድርገን እስኪ መረጃ እያጣቀስን ወደ ውስጥ እንመልከት)
ቅድመ ታሪክ (ማኅበረ ቅዱሳን ማን ነው?): የ መተከልና ጋምቤላ መንደር ምስረታ፣ የ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች የፅዋ ማኅበራትና የብላቴ ዘመቻ ለ ማኅበረ ቅዱሳን መመስረት ትልቅ ድርሻ ቢኖራቸውም ብፁዕ አቡነ ጎርጎሪዎስ ካልዕ እና ብፁዕ ዶ/ር አቡነ ገብርኤል ወጣቶችን ሰብስቦ ከማስተማር ወደ አንድ የማኅበር ስያሜ እስከ ማምጣት ድረስ ያደረጉት ተጋድሎ ለማኅበሩ ቀጥ ብሎ መቆም መሰረት መሆኑን በጊዜው የነበሩ አባላት ሁሌም የሚናገሩት ሃቅ ነው1፡፡ በተለይ እምነቱን በእነ ሌሊንና እስታሊን ፍልስፍና ቀይሮ በ ሶሻሊስት አብዮት ጨርቁን ጥሎ በከነፈው ትውልድ መሃከል ስለ አብያተ እምነት የሚቆረቆር ትውልድ መኖሩ ነበር እኒህን አባቶች “ኑ ልጆቼ እኛ እናንተን መፈለግ ሲገባን እናንተ እኛን ፈልጋችሁ መጣችሁ፣ ንፍሮ ቀቅለን፣ አዳራሽ ባይኖረንም ድንኳን ጥለን እናስተምራችኋለን”1,2,3,4 ብለው እንዲቀበሏቸው ያደረጋቸው፡፡
Friday, March 25, 2016
ለ "አንቺ ያለኝ ፍቅር"
ለፍቅርሽ ጥልቀት
ለ ሰብዕናሽ ምጥቀት፤
ብራና ዳምጬ
ቃላትን መርጬ
ብዕሬን ጨብጬ፤
በሰከነ መንፈስ~ልፅፍ
አስብና
ፈዝዠ እቀራለሁ~ሐሳብ
ሁሉ
መና
ማይጨበጥ ነፋስ~የቅዠት
ደመና
Friday, March 18, 2016
Sunday, January 24, 2016
“ከ አሜን ባሻገር”
በእውቀቱ ስዩም ትክክለኛው የጥበብ ሰይጣን ከለከፋቸው ጥቂት ኢትዮጵያውያን
መካከል አንዱና የወቅቱ ፈርጥ ነው፡፡ ክቡር ዶ/ር ሐዲስ አለማየሁ (በዕውቀቱ እንደሚለው ‘አዲስ ህልም አየሁ’) ምን አልባት ፍቅር
እስከ መቃብርን ሲፅፉ የመቼታቸው መነሻ የሆነውን ማንኩሳን ከአንዴም ሁለት ሶስቴ መጎብኘታቸው አይቀርም፡፡ በእርግጥ ማንኩሳ ከትውልድ
ቦታቸው ከእንዶደም ኪ/ምህረት በእግር ጉዞ ቀናትን የሚፈጅ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ግን በመኪና የ ሰዓት ጉዞ በቂ ነው፡፡ ወደ መላምቴ
ልምጣና፣ ክቡር ዶ/ር ሐዲስ አለማየሁ በወቅቱ ማንኩሳን ሲጎበኙ ከቤተክርስቲያኑ ጎን ቁጭ ብለው ስለ ቦጋለ መብራቱ፣ ውድነሽ በጣሙ
እና ስለበዛብህ ሲያሰላስሉ ከዚያ ቦታ ወደፊት አንድ የጥበብ ሰው እንዲነሳ አምጠዋል (ወይም በዩኒቨርስ ህግ ሃይል አጋርተዋል
(energy sharing)::
Monday, January 18, 2016
+መንታ መንገዱ ላይ...+
እንደ ዘበት ወርደን~ከ ትናንት አቀበት
ለመውጣት ስንጀምር~የዛሬን ቁልቁለት
ነገን መዳረሻ~መንታ መንገዱ ላይ
አንዲት እርጉዝ አለች~ከርቀት የምትታይ
ከመንታ ተወልዳ~መንታ በማርገዟ
መንታ መንገዱ ላይ~የበዛ መዘዟ፤
እነዚያም ልጆቿ፡
በማይታይ ህልም~በሰነቁት ተስፋ
ሰፊ ማህፀን ውስጥ~አንዱ አንዱን ሲገፋ
መቻቻል ተረግጦ~ጥላቻ ሲፋፋ
በመን’ቶ’ች ሽኩቻ~ነጠፈ ሰላሟ
በቃር በሲቃ ድምፅ~በረታ ህመሟ፤
እንዲህ እየሆነች
የስቃይን ፅዋ~በግፍ እየጠጣች
መንታ መንገዱ ላይ~ትውልድ ታምጣለች
በ ዘላለም ጥላሁን (የእናቱ ልጅ)
ጥር 09/ 2008 ዓ.ም
Friday, January 15, 2016
Wednesday, January 13, 2016
Thursday, December 31, 2015
“ትርጉሙን የማላውቀው ህይወት በ___ብር”
የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል
ማግስት ምሽት የባቡሩን መንገድ ተከትዬ ከሜክሲኮ ወደ ቡናና ሻይ እያዘገምሁ ነው፡፡ በአካባቢው የመኪና፣ የሰውና የባቡር ድምፅ
ነግሷል፡፡ ቡናና ሻይ አካባቢ ስደርስ አንድ ተባራሪ መፅሐፍ ነጋዴ….
“ትርጉሙን የማላውቀው መፅሃፍ በ
20 ብር….”
“ትርጉሙን የማላውቀው መፅሃፍ በ
20 ብር…..”
እያለ አልፎ ሂያጁን ይጣራል፡፡
ወደ ቦሌና ወደ አራ ኪሎ የሚሄድ ታክሲ ፈላጊ ልጁን ገረፍ አድርጎት ፈገግ ብሎ ያልፋል፡፡
እኔ ትንሽ ቆም ብዬ መፅሀፎችን
ገረፍኋቸው፡፡ ነገር ግን ከፅሁፋቸው መብዛት የተነሳ ርዕሳቸውን በደንብ ማስታወስ አልቻልኩም፡፡ የተፃፉት ግን በእንግሊዝኛ ነው፡፡
የማንበብም የመግዛትም ሙድ ውስጥ
ስላልነበርሁ እኔም ገረፍ አድርጌው ሄድሁ፡፡
Monday, December 28, 2015
“ቱቦ አትሁኑ…ቱቦ አትሁኑ…”
“ልጆቼ ቱቦ አትሁኑ፡፡ ቱቦ ባዶ ነው፡፡ የሚይዘው ነገር የለም፡፡ ማስተላለፍ
እንጂ መያዝ አይችልም፡፡ ቱቦ ካልሰጡት በራሱ የሚያመነጨውና የሚያስተላልፈው ነገር የለም፡፡ ቱቦ ሁሌም ጥገኛ ነው፡፡ ልጆቼ ቱቦ
አትሁኑ፡፡ቱቦ አትሁኑ፡፡ ልጆቼ መተላለፊያ አትሁኑ፡፡”
ይህ ንግግር በአንድ ወቅት አንድ
አባት የተናገሩት ነው፡፡ በወቅቱ ንግግራቸውን ከቁብ አልቆጠርሁትም፡፡ ሌሎቹም እንደዚሁ፡፡ ምክንያቱም ሰው እራሱ ቱቦ ነው፤ በአፉ
አስገብቶ በ ‘እንትኑ’ የሚተፋ የምግብና የውሃ ማስተላለፊያ ቱቦ፡፡ ከዚህ ያለፈ ሰውን ከቱቦ ጋር ሊያመሳስለው የሚችል አንዳች
ነገር በጊዜው አልታየኝም፡፡ ይህ ደግሞ ተፈጥሮአዊ ነው፡፡ ስለዚህ በጊዜው ሀሳባቸውን ውድቅ አደረግሁት፡፡ መብቴ ነው መቀበልም
አለመቀብልም (አንቀፅ---)፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)








