Labels
- ሐይማኖት (Religion) (8)
- ማህበራዊ ጉዳይ (Social Affair) (42)
- ሳይንስና ቴክኖሎጂ (Science and Technology) (4)
- ባህል (Culture) (11)
- ታሪክ (History) (20)
- ከመፅሐፍት ዓለም (from books) (6)
- የጉዞ ማስታወሻ (Journey’s log) (4)
- ግጥም (Poam) (44)
- ጤና (Health) (3)
Saturday, February 25, 2017
Thursday, February 23, 2017
"አክሚኝ...፩"
አመመኝ
አልችል ስል ተኛሁኝ
.
.
ተኝቼም ሲብሰኝ~በሽታዬ ሲከር
ሄድሁኝ ወደ ሃኪም~ህመሜን ላማክር
.
.
.
ሆስፒታል ገብቼ~ደሜን መረመሩኝ
ትዝታሽ ነበረ~እኔን ያሳመመኝ
.
.
ተኝቼም ሲብሰኝ~በሽታዬ ሲከር
ሄድሁኝ ወደ ሃኪም~ህመሜን ላማክር
.
.
.
ሆስፒታል ገብቼ~ደሜን መረመሩኝ
ትዝታሽ ነበረ~እኔን ያሳመመኝ
Monday, February 20, 2017
ከ ቢሾፍቱ ሐይቅ አፋፍ ላይ
(ከ ፕሮፌሰሩ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ)
ቢሾፍቱ ነፍስን የሚገዙ ትንንሽ ሀይቆችን በተፈጥሮ የተቸረች ምርጥ ከተማ ናት፡፡ በተደጋጋሚ ጎብኝቻታለሁ፡፡
ግን አልጠግባትም፡፡ ሐይቆቿ ነፍሴን ይገዙታል፡፡ ከ እራሴ ጋር እንዳወራ እድል ይሰጡኛል፡፡ ከ ዓለም ጫጫታ ወጥቼ ከ ማዕበሉ ጉዞ
ጋር ነፍሴን አስማምቼ በምናብ እንድመጥቅ፣ ከ ሀሳቤ ህመሜ ለ አፍታም ቢሆን እንድላቀቅ ይረዱኛል፡፡ ሐይቅ እወዳለሁ፡፡ ጣና፣ ደብረዘይት፣
ዝዋይ፣ ሐዋሳ፣ ዘንገና፣ አለማያ……በተጋጋሚ ባያቸውም አልጠግባቸውም፡፡ ሁሌም ከጉያቸው ቁጭ ብዬ የሚተነፍሱትን አየር ወደ ውስጤ
መማግ ያረካኛል፡፡ ንፁህ አየራቸውን ስስብ፣ አዲስ ተስፋና አዲስ ህይወት ይታየኛል፡፡ ከ ጀርባዬ ያለ ሸክም የተራገፈ ያክል ነፃነት ይሰማኛል፡፡ ጥሎብኝ ሐይቅ ብቻ ሳይሆን ተፈጥሮን
አደንቃለሁ፡፡
ከ ቢሾፍቱ ፈርጦች ውስጥ በ ርዕሰ ከተማዋ ስም የተሰየመችው ቢሾፍቱ
ሐይቅ አፋፍ ላይ ቁጭ ብዬ ከማዕበሉ ጋር በመጫወት ላይ ሳለሁ እርዳታዬን ፈልጎ አንድ አሮጌ ፈረንጂ ወደ ተቀመጥሁበት ወንበር መጣ፡፡
(እዚህ ጋ ያዝ ላድርገውና ስለ ቢሾፍቱ ሐይቅ ትንሽ ልበል፡፡)
Wednesday, February 15, 2017
በ እንተ ቫላንታይን_ ፪
(እለትና
ማግስት)
“የማይጠቅም መሬት ያበቅላል ደደሆ
የፈራሁት ነገር መጣ ድሆ ድሆ”
……..እንዲሉ……..ሁላችንም ፈረንጂ ካመጣው የባህል ወረራ በምንም መንገድ ማምለጥ እንደማንችል ገባኝ፡
ከሃላፊዎች ቀጭን ትዕዛዝ የተቀበሉ የአልጋ
ከፍል ሰራተኞች ያለ የሌለ ጥበባቸውን ተጠቅመው የቫላንታይን ቀን እንዴት ከጥበብ ጋር እንደሚገናኝ አልጋው ላይ በሰሩት ዲኮሬሽን
ሊያሳዩን ሞክረዋል፡፡…………..አራት ማዕዘን፣ ልብ ቅርፅ፣ዲያጎናል…..ምን አለፋችሁ የሌለ የለም፡፡….ምን አልባት ከ አገልግሎቱ
በተጨማሪ ሆቴሉ የዲይዛይን ትምህርት ይሰጣል መሰለኝ፡፡…………ክፍሉ በፅጌረዳ አበባ መዓዛ ታውዷል፡፡ ከ እብድ መሃከል የተቀመጠ
ሰው ጤነኛ ነኝ ቢል ማንም አያምነውም፡፡………..የተረዳሁት ነገር ሁላችንም ታመናል፡፡………ጨዋታው የ 6 እና የ 9 ቁጥር ነው፤
ሰዎች በራሳቸው ዕይታ ያያሉ፣ ያዩትንም ያምናሉ፡፡……. ያመኑትን ግን ሌሎችን ካልተቀበላችሁ ብሎ በግድ መጫን ትክክል አይደለም፤
ይህን ለማድረግ መጀመሪያ በሌሎች ቦታ ሁኖ ማየት ግድ ይላል፡፡……ውድ አድማጮች አስተውሉ፣ እኔ በዓሉን አልነቅፍም……..የበዓሉን
አንድምታ እንጅ! ተከተሉኝ!
በ እንተ ቫላንታይን
(ለቀይ አምላኪዎች-ከ ዘይት ተራራ
እስከ ቀይ ፓርቲ)
የተዘጋጃችሁ፣ ሩጫ የጀመራችሁ፣ በዝግጅት ላይ ያላችሁ፣ የተደናገራችሁና ግራ የገባችሁ…አንድ ቀኝ
መላ ልንገራችሁ፡፡ በቅድሚያ ለቫላንታይን (ቅድመ ቃለ አመጣጥ=አማርኛ፤ ትርጉም=ባለን ታዬን……ዝርዝሩን በሌላ ጊዜ) ዋዜማ እንኳን
አደረሳችሁ፡፡ ከ ደም ውጭ ቀይ የሆነ ነገር ለምሸጡ ሁሉ ይሄን ቀን እሺ ያድርግላችሁ፡፡ አሜን
በሉ! (ሀሌ ሉያ እንዳትሉ!....ኢየሱስ ደም ሰጠ እንጂ ቀይ ልብስ አልሰጠም፣አልሸጠም)……
የአዲስ አበባ ህዝብ ከሰኞ እስከ አርብ ወጥሮ አዲስ አበባ ውስጥ ይሰራል፡፡ ቅዳሜና እሁድ ደግሞ
ደብረ ዘይት ውስጥ ወጥሮ ይሰ’ራል! (ሳቅ)……………………………..(ይህ አረፍተነገር በደምና በወዝ የሚኖሩ ና ከስኳር በሽታ ነፃ
የሆኑ የህዝብ አገልጋዮችን አያካትትም፡፡)
Thursday, January 26, 2017
ሶስቱ_ወፎች...
ቀኑ ጥቁር ነበር~ደመና ያዘለ
ተጓዥን የሚያደርስ~ከታች መንገድ አለ
እንደ እየሱስ መስቀል~የተመሳቀለ፤
በ ረጅም ጉዞዬ~ስሄድ በመንገዴ
አእዋፍትን ዛፍ ላይ~አያለሁ አንዳንዴ
ከነዚህ መካከል~በውበት የሚያምሩ
ቀልቤን የወሰዱ~3 ወፎች ነበሩ፤
ከዛፉ ወጥቼ~ትንሽ ስረጋጋ
ከዛፉ ወጥቼ~ትንሽ ስረጋጋ
ክንፋቸውን ልይዝ~እጄን ስዘረጋ
አንድ ሲሉ.....
.......አንድ ሲሉ
ሁሉም በየተራ~ጥለውኝ በረሩ፤
ቁጭትና ንዴት~ከ እልህ ተደምሮ
እንቅልፍ ቢጤ ጣለኝ~በድካም አስክሮ፤
ከ
ግንባሬ በታች~አንዲት ፍሬ ወድቃ
ዘራፍ ወንዱ ብዬ~ከ እንቅልፌ ስነቃ
በህይወቴ ዛፍ ላይ~ብዙ አእዋፋት ሰፈሩ
ቀልቤንም ላይስቡት~አብረውም ላይኖሩ፤
በዚህ ሁሉ ሂደት~አውቃለሁ አንድ ሃቅ
በ
እውነተኛ ብዕር~የፃፍሁት በደማቅ
➊
"ለማዳም ፍጥረታት ክንፍ ያላቸው ሁሉ
ጊዜውን ጠብቀው ሁሉም ይበራሉ"
➋
"በዚህ ግዑዝ ዓለም~የለም ትልቅ ቅጣት
እንደ መካ`ድ እና~ፈልጎ እንደ ማጣት!"
Tuesday, December 20, 2016
‹‹ትዝብት….›››
በ “ሂደት” ላይ “ሂደት”
ቆርጠን ስንቀጣጥል~ቃላትን
በቃላት
በጨለማ ግርዶሽ~ያ
ትናንት
ከሰመ
ዛሬም በ ጭቅጭቅ~አቁሞን
ተመመ
በ“ሂደት” ሽንገላ
በ “ወደፊት”መላ
የ “ነገ” ን ለ “ነገ”~እቅድ
ስናሰላ
በማስመሰልና በ ስንፍና ጋሻ~እየተደገፈ
ያልኖርንበት “ነገ”~ሳናየው
አለፈ
(ምንጭ፡
ከታዛቢው ማስታወሻ)
Friday, December 16, 2016
Wednesday, December 14, 2016
Thursday, September 29, 2016
ሁሌ_ጥቁር_መርዶ...
"ከ ቀይ ባህር ማዶ~እሺ ሰው ሰመጠ
በሳውዲ አደባባይ~አንገት ተቆረጠ
በሰሜን በ ደቡብ~እልፍ ሰው ታሰረ
መሪና ተመሪ~ሁሉም አመረረ፤
አምሳ ተገደለ
እቤት ተቃጠለ"
.
.
ነው መሪ ዜናችን~ከ አገር ቤት ከማዶ
ሰላም ማውራት ቀረ~ሁሌ ጥቁር መርዶ፤
በሰሜን በ ደቡብ~እልፍ ሰው ታሰረ
መሪና ተመሪ~ሁሉም አመረረ፤
አምሳ ተገደለ
እቤት ተቃጠለ"
.
.
ነው መሪ ዜናችን~ከ አገር ቤት ከማዶ
ሰላም ማውራት ቀረ~ሁሌ ጥቁር መርዶ፤
Subscribe to:
Posts (Atom)






