Saturday, January 12, 2013

ይቅደም ሰብአዊነት

በህንፃ ላይ ህንፃ ድንጋይ ስንደረድር

ከመንገድ ላይ ወድቆ የስላሴ ፍጡር
የሚቀምሰው አጥቶ ለመሞት ሲጣጣር
አያየን ማለፉ አንደ ቀላል ነገር

         ምነው መኖር ተስፋው ምንድን ነው ትርጉሙ
         የራበውን ደሃ ቀርበው ካልደጎሙ
         እናም ወገኔ ሆይ ይቅደም ሰብአዊነት
         ነገ ዛሬ ሳትል በሃብትህ ስራበት
         አንተም ወደ መሬት ከመግባትህ በፊት


 ከዚህ በታች ያለውን የአንድ ህንዳዊን ሰብአዊ ተሞክሮ የሚያሳይ ድምፅ ወምስል ሁላችንም ማየት ያስፈልጋል፡፡


Tuesday, January 1, 2013

ፓተንቱ ይሰጠው


 
የትኛውነው እብድ የትኛው ነው ደህና
መለየት አቃተን ግሎባላይዜሽን ባመጣው ፈተና
እብድ አሳጥሮ ቀዶ ሲለብስ አይተው
እራቁት ይሄዳሉ ዝመና ነው ብለው
        ዝመና ከሆነ እራቁትን መሄድ አጭር ታይት መልበስ
        በነፃ መደብደብ ለ ፀሐይ ለ ነፋስ
        አለም ሳያስበው ቀድሞን ለዘመነው
        ለሀገሬ ገበሬ ፓተንቱ ይሰጠው