Saturday, April 30, 2016

እንኳን አደረሳችሁ


[እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቆሰለ፣ ስለ በደላችንም ደቀቀ። ኢሳ 535]

ክርስትና እምነት ተከታይ የሆናችሁ፤ ውድ የድህረ ገፅ ወንድሞቼና እህቶቼ፡ 
እንኳን ለትንሳኤ በዓል ሰላም አደረሳችሁ፡፡ 
በዓሉ የሰላምና የደስታ ይሁንላችሁ፡፡ 

አሜን!


Tuesday, April 26, 2016

"የተስፋዋን ምድር…"

እንደ ሲና ምድር ቢሆንም በረሃ
የሚቀመስ ባይኖር የሚጠጣ ውሃ
እጅግ አስቸጋሪ ቢሆንም መንገዱ
ድካም ቢፈትነኝ እግሮቼ
                                     ያ
                                         ረ
                                             ግ
                                                 ዱ
ከጉዞዬ አልቆምም ኋላም አልመለስ
የተ
     ስ
          ፋ 
              ዋ
                  ን ምድር እስካገኛት ድረስ!

Tuesday, April 19, 2016

ነጭ አምላኪነትና የወገን ፍቅር (White worship & Fellowship’ Love)

“ሳንርቅ እንጠይቅ…..” 
(ከ ዘላለም ጥላሁን)
 ##በቅድሚያ መንግስት ያወጣውን ብሔራዊ የሐዘን ቀን መሰረት አድርጌ የንፁሃንን ነፍስ አምላክ እንዲምር ዝቅ ብዬ የህሊና ፀሎት አድርሻለሁ፡፡ ከዚህ ቀጥሎ ግን አንዳንድ ትዝብቶቼን ልተንፍስ፡፡
ከ ጥቁርና ከነጭ ሰው ማን ይበልጣል???
ይህን ጥያቄ ለመመለስ የሰው መጀመሪያ የነበሩት አዳምና ሔዋን መልካቸው ምን አይነት እንደነበር ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ለ አቤልና ቃዬል የጠብ መነሻ ተደርጋ የምትወሰደው እንስት እንኳ ስለ ውበቷ መልከ መልካምነት እንጂ ስለ ነጭና ጥቁርነቷ የሚገልፅ ማስረጃ የለም፡፡

ያም ሆነ ይህ ግን መች እደተጀመረ ባይታወቅም የነጭ የበላይነት በዓለም ላይ ለ ዘመናት ገኖ/ሰልጥኖ ቆይቷል፡፡ ምንም እንኳ የሰውን እኩልነት የሚያንፀባርቁ ለቁጥር የሚያታክቱ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ና ድንጋጌዎች በየጊዜው ቢወጡም የሰው ልጅ ግን አሁንም ድረስ ከ አካላዊ ባርነት ቢወጣም ከ አስተሳሰብ ባርነት ሊወጣ አልቻለም፡፡ ይህ ጉዳይ ደግሞ ወደ አፍሪካ ሲመጣ መረን የለቀቀ ችግር ሁኖ ይስተዋላል፡፡ ያን የሰቀቀን የቅኝ ግዛት ዘመን በግፍና በመከራ ያለፉ የአፍሪካ ሀገራት ዜጎች አሁንም ቢሆን ነጭን ከማምለክና ለነጭ ከማጎብደድ (ሮበርት ሙጋቤን አይጨምርም…..) እንዲሁም ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ከማዬት አስተሳሰብ አልወጡም፡፡

Monday, April 11, 2016

ስማኝ ያገሬ ሰው...

አንተ ያገሬ ሰው!
ስንዝር መቃብርህ~በቁም የተማሰው 
እባክህን ስማኝ 
አንድ ምክር አለኝ 
በነጋ በጠባ የሚወሰውሰኝ፤
አይሁዳውያን መሃል~ክርስቶስን ማግኘት
ልክ እንደ ጲላጦስ~ሰቃይ ፊት መዳኘት
እንደ አገሬ አርበኛ~ስለ እውነት መሞት
እንዲከብድ አውቃለሁ
ዘመኑን እያየሁ፤

Thursday, April 7, 2016

“ጊዜ በረርክ… በረርክ…”

ጊዜ እንዴት ይሮጣል፡፡ እነሆ ደርዘን አመታት ያለመታከት እንደዋዛ ነጎዱ፡፡ አንዳንዴ ቆም ብዬ ሳስበውየሰው ልጅ ዕድሜ እንደ ጥላ ያልፋል” የሚለው አገላለፅ እራሱ በቂ አይመስለኝም፡፡ ዞር ብለን የህፃንነት ዘመናችንን ስናስታውስ እጃችን የምነካው ያክል የትናንት ትዝታ በጣም ቅርብ መስሎ ይሰማናል፡፡ …..ነገር ግን በመሃከላችን በጊዜ መስፈርት ስናያቸው፡ 20 በላይ ድፍን ዓመታት ወይም …… 240 በላይ ወራት ወይም….. 624 በላይ ሳምታት …..ወይም 7300 በላይ ቀናት ….ወይም 175 200 በላይ ሰዓታት ….ወይም 10.5 ሚሊዮን በላይ ደቂቃዎች  …ወይም 630 ሚሊዮን በላይ ሰከንዶች  ….ወይም….