Monday, April 11, 2016

ስማኝ ያገሬ ሰው...

አንተ ያገሬ ሰው!
ስንዝር መቃብርህ~በቁም የተማሰው 
እባክህን ስማኝ 
አንድ ምክር አለኝ 
በነጋ በጠባ የሚወሰውሰኝ፤
አይሁዳውያን መሃል~ክርስቶስን ማግኘት
ልክ እንደ ጲላጦስ~ሰቃይ ፊት መዳኘት
እንደ አገሬ አርበኛ~ስለ እውነት መሞት
እንዲከብድ አውቃለሁ
ዘመኑን እያየሁ፤

ግን ደግሞ ወገኔ፡
አእምሮ ስላለህ
አንተም አንደሌላው~ስጋ ስለለበስህ
የሁሉን ቻይ ጀርባ~በገራፊዎች ግፍ
እንደ አቫዬ በሬ~ሳይደማ ጅራፍ 
ምስኪን ክርስቶስን~ከመስቀልህ በፊት 
ግዴለም አትቸኩል~ደግመህ አስብበት

No comments:

Post a Comment