Tuesday, September 29, 2015

[["ጎርፍ"]]

በጋ ዘመን አልፎ
                        ሊተካ ሲል ክረምት
በደረቀው መሬት
ጠል ሊወርድበት
የመኸሩ በኩር
ሲገባ ግንቦት ወር
በጠራው ሰማይ ስር

Saturday, September 26, 2015

“ጴጥሮስ ያችን ሰዓት”

(ዛሬም ጀብራሬዎች በሐውልቱ እየሸኙ ነው)
ታላቁ ባለቅኔና ተውኔት አዘጋጅ ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ዘመን ተሻጋሪ የሆነችውን “ጴጥሮስ ያችን ሰዓት” የምትለዋን ግጥም የፃፈው፡ አንድ ቀን ምሽት ከማዘጋጃ ቤት ሲወጣ ባየው ትዕይንት ምክንያት ነው፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡ ፀጋዬ ገ/መድህን ከማዘጋጃ ቤት እንደወጣ ቁልቁል ወደ አቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ሲያመራ አንድ ጀብራሬ (በሎሬቱ አነጋገር) ከአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ላይ ሸንቱን ሲሸና ተመለከተ፡፡ ፀጋዬም በደም ፍላት ወደ ጀብራሬው ተንደረደረ፡፡ ጀብራሬው ግን “አንተ ድንጋይ እሸናብሃለሁ፡፡ ድንጋይ ነህ …. ድንጋይ ነህ ….” እያለ በሐውልቱ ላይ ይሸናል፡፡ በዚህ ሰዓት ነበር ሎሬቱ “ጴጥሮስ ድንጋይ አይደለም” ብሎ ጀብራሬውን በደም ፍላት ዘሎ ያነቀው፡፡ ከዚያም አብረውት የነበሩት ሰዎች ገላገሉትና እየተብሰከሰከ አራት ኪሎን ተሻግሮ ቀበና ገባ፡፡

Wednesday, September 23, 2015

“ለምን አለቅሳለሁ!”

እስከመቼ ለቅሶ
እስከመቼ እምባ
ዘመን ተቀይሮ
      የሳቅ ቀን ላይገባ
የሚያስለቀስ እንጂ
      ሀዘን የሚያጠፋ
ተስፋ ጨፍላቂ እንጂ
       ሚመፀውት ተስፋ፤
በሌለበት ሀገር
በግፍ በጥላቻ በቀለጠ መንደር
የዓለምን እርኩሰት ክፋቷን እያሰብሁ
በነጋ በጠባ ለምን አለቅሳለሁ?

Thursday, September 10, 2015

አስገራሚዋ ብላቴና (The Miracle Teenager)_ክፍል ፪

               በመጨረሻም ፌስቡክ ተጠቃሚዋ ስምረትና አሁን ያለችበት ሁኔታ !
ከአመታት በኋላ በቀጠሯችን መሰረት ከተወዳጇ ስምረት ጋር ተገናኘን፡፡ የተገናኘነው ከአመታት በፊት አውርተንበት የነበረው ቦታ መሆኑ ሁለታችንንም ትልቅ ትዝታ ላይ ጥሎናል!
ከቀጠሯችን ውጭ ይዛቸው የመጣቻቸው ሦስት ሴት ልጆች ትኩረቴን ስበውታል፡፡ በአንድ አይነት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሦስት ዕንቁዎች !! የስምረትን አስበልጬ ከሁሎችም ጋር ሞቅ ያለ ሰላምታ ከተለዋወጥኩ በኋላ ስራዬን ጀመርኩ፡፡
«ባለ ራዕይዋ ስምረት ይታይህእንኳን በድጋሜ ለመገናኘት/ለመተያዬት አበቃን»
«(
ሳቅ…) እግዚአብሄር የተመሰገነ ይሁንበድጋሜ ስላገኘሁህ እኔም በጣም ደስ ብሎኛል
«
እሽ ወይዘሪት ስምረትነው ወይንስ ወይዘሮ ይሆን ? በሚገርም ሁኔታ ተለውጠሻል፣ ትልቅ ሰው ሁነሻልሶስቱ አብረውሽ የማያቸው መንትያ ሴቶችስ ልጆችሽ ይሆኑ

Monday, September 7, 2015

"ና መስከረም ግባ"

ና መስከረም ግባ
  ና ሆድህ አይባባ    
ግባ ችግር የለም  
በአንተ አንጨክንም፤
መስከረም ለምለሙ የወራቶች በኩር
የሰላም የፍቅር የህዳሴ ሚስጢር
የዘመን ተምሳሌት የአንድነት ምልክት
የውጥን መባቻ የሐበሻ ኩራት
ኮተትህን ጥለህ መስከረም ሆይ ግባ
ጳጉሜ ላይ ቀብረኸው የጥላቻን ካባ፤

Friday, September 4, 2015

የ “አሉ” ዘመን

አሉነው ዘንድሮ
እውነትማ ጠፋ በውሸት ተቀብሮ
....“አሉ”....
ጋዜጠኞችአሉ
በሸፈጠ አንደበት ቃላት እየቆሉ
.......“አሉ”.....
ነጋዴዎችአሉ
በለስላሳ አንደበት ህዝብ እያታለሉ
.....“አሉ”.....
ባለስልጣኑአሉ
የህልም እንጀራ ህዝብን እያበሉ
.....“አሉ”......
መምህራኑምአሉ
ሳይንስን እረሱ ኑሮን እያሰሉ