Wednesday, September 23, 2015

“ለምን አለቅሳለሁ!”

እስከመቼ ለቅሶ
እስከመቼ እምባ
ዘመን ተቀይሮ
      የሳቅ ቀን ላይገባ
የሚያስለቀስ እንጂ
      ሀዘን የሚያጠፋ
ተስፋ ጨፍላቂ እንጂ
       ሚመፀውት ተስፋ፤
በሌለበት ሀገር
በግፍ በጥላቻ በቀለጠ መንደር
የዓለምን እርኩሰት ክፋቷን እያሰብሁ
በነጋ በጠባ ለምን አለቅሳለሁ?

.....................
እንባዬን ላቁመው
የእምባ ከረጢቴን ቦዬን ልገድበው
ብሶቴን አምቄ
ወገቤን አጥብቄ
እምባዬን ላድርቀው
በተስፋ መነፅር ፊቴን ልመልከተው፤
እንባዬን አብሸ ኑሮ እንኳን ባይሰምር
በፈገግታ ለዛ ልግባ ወደ ምድር!
*************************
 መስከረም 2፣ 2008 ዓ.ም

No comments:

Post a Comment