Monday, May 25, 2015

ምርጫ 2007

እለተ ሰንበት ግንቦት 16 2007 .ም፡፡ እናት ሀገሬ 5ኛውን አገር አቀፍ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ አጠናቃለች፡፡ምንም እንኳ የሀገራችንን ልማትና ዲሞክራሲ ለማደናቀፍ የሚፈልጉ ፀረ ልማት ኃይሎች ምርጫው ምርጫ ሳይሆን በገዢው ፓርቲ ፊታውራሪነት በአጋር ፓርቲዎች ግራአዝማችነት የተጠናቀቀ ቅርጫ ነው ቢሉም፡፡ “ውሾች ይጮሃሉ፤ ግመሎችም መጓዛቸውን ይቀጥላሉ ”፡፡ ጠንካራና ከመጮህ ያለፈ ራዕይ ያላቸው ውሾች እስካልተፈጠሩ ድረስ፡፡ በትናንቱ የምርጫ እለት የተፈጠረ አንድ ፈገግ የሚያሰኝ ክስተት ልንገራችሁ፡፡

Tuesday, May 19, 2015

አፍሪካዊው ሰይጣን

የሳጥናኤል ምንዝር የጥንተ ፍጡራን
በጠሊሃ ሀገር በአፍቅሮተ ስልጣን
በከፊሎተ ዘር ህዝብን በመጨቆን
የአፍሪካን መሪዎች የለከፍከው ሰይጣን
      አላማህ ምንድን ነው?
      መኖሪያህ ወዴት ነው?
     ዘመንህ ስንት ነው?
      እባክህ ንገርን፤

Wednesday, May 6, 2015

ኮሎኔል አብዲሳ አጋ

ኮሎኔል አብዲሳ አጋ የተወለደው በ፲፱፻፲፪(1912) . በኦሮሚያ ክልል፣ ወለጋ ዞን ነበር። በ፲፪(12) ዓመቱ አባቱ በንዴት ወንድማቸውን በመግደላቸው ሲታሰሩ አብዲሳ አባቱን ለማስፈታት የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ቢያደርግም ሳይሳካ በሞት ተቀጥተዋል። በኋላም በ፲፬(14)።፤ ዓመቱ የኢትዮጵያን ጦር በመቀላቀል ሀገሩን ማገልገል ጀመረ። አብዲሳ ጦሩን ከተቀላቀለ ከሁለት አመት በኋላ አድዋ ሽንፈት ለመበቀል የዛተው ፋሺስት ሙሶሎኒ በድጋሚ ኢትዮጵያን ሲወር ሀገሩን ለመከላከል በ፲፮(16) ዓመቱ ወራሪውን ጦር መዋጋት ጀመረ። ውጊያ ላይ ባጋጠመው የመቁሰል አደጋ ህክምና ላይ ከቆየ በኋላ አዲስ አበባ ውስጥ ፒያሳ አካባቢ በሚገኝ ቤት በቁም እስር ላይ ነበር። በኋላ ጣልያን ኢትዮጲያን እንዲያስተዳድር በሾመችው ግራዚያኒ ላይ የመግደል ሙከራ ከተደረገ በኋላ አብዲሳ አጋ እና ሌሎች 37 የሚሆኑ የቁም እስረኞች ተጠርጣሪ ተብለው በከባድ ስቃይ እስር ቤት ከቆዩ በኋላ በወቅቱ የጣልያን ግዛት በነበረችው በሶማሊያ በኩል ወደ ጣልያን ተወስዶ በሲሲሊ ደሴት በሚገኝ እስር ቤት እስረኛ ተደረገ።

ፍትህ

አንዱ ለአንዱ አለቃ
ሌላኛው ጠበቃ
አንደኛው ምስክር
በሀሰት ክርክር
ፈራጁ ቀማኛ
ህሊና አልባ ዳኛ፤
እንዲህ እየሆነ በሚገዛው አለም
ተበደልኩኝ ብለህ ወደላይ ብትከስም
ትደክማለህ እንጂ ከቶ አታሸንፍም
ፍትህ መንፈሱ እንጂ
               አካሉ እዚህ የለም

Saturday, May 2, 2015

መንግስቱ ንዋይ

መጋቢት 19 1953 . የሞት ፍርድ ከተወሰነባቸው በኋላ የተናገሩት ንግግር
                           ======================
እናንት ዳኞች የበየናችሁብኝን የሞት ፍርድ ያለ ይግባኝ ተቀብያለሁ፡፡ ይግባኝ ብየ ጉዳየን የሚመለከትልኝ የኢትዮጵያ ህዝብ ቢሆን ኖሮ ይግባኝ ማለት በፈለግሁ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ እንደማይሆን አውቃለውና በይግባኝ የአፄ /ስላሴን ፊት ማየት አልፈቅድም፡፡ በእግዚያብሄር ስም ተሰይማችሁ ከተቀመጣችሁበት የፍርድ ወንበር ላይ ከመቀመጣችሁ በፊት በእኔ ላይ የምትሰጡትን የዛሬውን ፍርድ ታውቁት እንደነበር ሳስብና ፍርድ እስከዚህ መርከሱን ስታዘብ ሀዘኔ ይበዛል፡፡ለኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት፣ ነፃነትና እርምጃ የተነሳሁ ወዳጅ ነኝ እንጅ ለማፋጀት የተነሳሁ ወንበዴ አይደለሁም፡፡ ይህንን ማድረግ ፈልጌ ቢሆን ኖሮ ማንም የማይወዳደረው ሰራዊትና መሳሪያ ሳላጣ ዛሬ እዚህ ከእናንተ ፊት ለመቆም ባልበቃሁ ነበር፡፡