Tuesday, December 20, 2016

‹‹ትዝብት….›››

 ሂደትላይሂደት
ቆርጠን ስንቀጣጥል~ቃላትን በቃላት
በጨለማ ግርዶሽ~ ትናንት ከሰመ
ዛሬም   ጭቅጭቅ~አቁሞን ተመመ
ሂደትሽንገላ
ወደፊትመላ
ነገ ነገ~እቅድ ስናሰላ
በማስመሰልና ስንፍና ጋሻ~እየተደገፈ
ያልኖርንበትነገ~ሳናየው አለፈ
(ምንጭ፡ ከታዛቢው  ማስታወሻ)

Friday, December 16, 2016

‹‹የማታ የማታ...››

ኢንሴኔ ኢሴራ ተታኤ - ማናሆ ጣጊሳኖ
ሳይኖሩ አለሁ ማለት - ባዶነት ዘግኖ 

እንደ በሬ ማግሳት - ትንኝን ሳይሆኑ 
እኩይ ጊዜ ታቅሮ - መራቅ ዘመኑ
ራሱ አያውቅ ነዳይ -ሚል ተረት ታቅፎ
ራስነት በላይ፣ ሰውነት መንፈስ አእምሮዬ ገዝፎ
መሰሪ ገመድ፤ ህሊና ችንካር እጄ ተቆልፎ 
ነገ እያልሁኝ ኖሬ - ከንቱ ይሉኝታ 
ዛሬዬን ገድዬ፣ ነገ እለያለሁ የማታ የማታ
.........( ዘላለም ጥላሁን)...............

Wednesday, December 14, 2016

ለካስ እድሜ ማለት...

እንደ ኤሊ ጉዞ~እንዲህ እንደዋዛ
ሴኮንድ ተደማምሮ~ደቂቃ እየበዛ
የሰዓታት ውህደት~በቀናት ሲሰላ
ሳምንትና ወራት~አመት እየሞላ
ሰው የሚባል ፍጡር~ይኖራል በመላ
ሲደምር ሲቀንስ~ ቁጥር ሲጣላ


በትናንት ትውስታ~ከልጅነት ማዶ
ዛሬ ገፄን ሳየው~ እርጅና ተዋዶ
"ለካስ እድሜ ማለት~ጅረት ነው ፏፏቴ
ሽው ብሎ የሚሮጥ~አንዱ በአንዱ ኮቴ"
(Thank You My God)