Sunday, April 26, 2015

የመንገደኛ ነፍሶች ዋይታ

             ከ ጦቢያው አለም
ከወሎ ከሀረር፣ ከወለጋ ከወላይታ….ወጥተን
የደንበልን ሸለቆ የሱዳንን ጥሻዎች አቆራርጠን
በቀይ ባህር አዞዎች በየመን ግርዶሾች ተውጠን
ሞተን ተርፈን ሳውዲ አረቢያ ገብተን
ጉልበታችንን ሽጠን በልተን
በእንባችን ልብስ እያጠብን
ወዛችን ሽቶ ሆኖን ለራሳችን የነጻን ሲመስለን ለሌሎች ከርፍተን
በረሀ የበላው ጸጉራችንን ነጭተን ማግደን ሳት አንድደን ሞቀን
ነደን አብስለን በልተን አብልተን ሁሌ ሞት ሲፈረድብን

Wednesday, April 8, 2015

መልካም በዓል

እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቆሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን 
                                (ኢሳ. 535 1ጴጥ. 225)

Thursday, April 2, 2015

ተስፋ


 
ሁሌም ይታየኛል አንዳች ሩቅ ተስፋ
የዛሬ ያልሆነ የነገ ያልሆነ በጊዜ ሚገፋ
እንደ ህልም ያለ እውነት የመሰለ
ከመሬት ከፍ ያለ ከሰማይ ዝቅ ያለ
የህሊና ምስል ሰዓሊ ያልሳለው
ደራሲ በምናብ በብዕር ያልከተበው
ምሁር በምርምር ደርሶ ያልጨበጠው
ግብር ማልከፍልበት መንግስት ያላወቀው
ከእኔ ጋራ ያለ ተስፋዬ ብቻ ነው፡፡
             ዘላለም፤ ሰኔ 2006 ዓ.ም፣አዲስ አበባ