Saturday, May 27, 2017

...ግንቦት 20 ሺ ዘጠኝ ሞቶ…

ሁሉም መንገዶች ግንቦት 20 አድርገው ወደ ህዳሴ ያመራሉ አንድ ወቅት በውቀቱ ስዩም እንዲህ የምትል ክሽን ቀልድ ቀልዶ ነበር፤
‹‹ ቀበሌው ሊቀመንበር አካባቢው ፈለቁ ሶስት ምንጮችን እየመረቁ ነበር፡፡ ከዚያ ምረቃው ስነ ስርዓት ለተገኘው ህዝብ እንዲህ የሚል ንግግር አሰሙ፤ ‹‹ ውድ ቀበሌያችን ህዝቦች እነዚህ ምንጮች መፍለቅ ዲሞክራሲያችንና መልካም አስተዳደራችን ውጤት ነው አሉ፡፡ ከዚያም ጭብጨባ ተቸራቸው››. አጨብጭበህ ሙት ያለው ህዝብ!

ወደ የት መሄድ እንደፈለግሁ ግልፅ ነው፡፡ ንጉሱ ዘመን መልካም ነገሮች ሁሉ ንጉሱ ችሮታ ተደርገው ይታሰቡ ነበር፡፡ ደርግ ዘመን ደግሞ ሁሉም መልካም ነገር አብዮቱ ውጤት፣ መጥፎው ነገር ደግሞ አድሃሪያኑ ሴራ ተደርጎ ይወሰድ ነበር፡፡

Thursday, May 18, 2017

‹‹የ ወንድ ልጅ ልቅሶ››

መች ጠገብሁሽና እንዴት ይድላኝ አልጋዬ
ፍቅርሽ ፀንቶብኛል እኔ አልተኛም ጨርሶ፣
……………
ማታ ማታ ማልቀስ ነው ስራዬ
…..እንዲህ እንዲህ እያለ ገርማሞ ልጅ ብሶቱንና እውነታውን አደባባይ አንጎራጉሮ እኛንም ሆድ አስባሰን፡፡ እኛ ማህበረሰብ ሴት ልጅ ብቻ አልቃሻ ተደርጋ ትወሰዳለች፡፡ ነገር ግን የወንድ ልጅ አልቃሻምነት ይብሳል፡፡……………ሴት ልጅ እምባ ዘለላዎችን አፍሳ የውስጧን እሳት ከፊልም ቢሆን ታበርዳለች፡፡ ወንድ ልጅ ግን ውስጡ እያነባ እምባ ዘለላዎቹን ጥርሱን ነክሶ ይታገላቸዋል፡፡ 

Monday, May 15, 2017

አንድ አፍታ_ስለ በላይ ዘለቀ

‹‹ያን ጀግና ሰቀሉት ቁልቁል አንጠልጥለው
በላይ ዶሮ አይደለ ጭርታውን አይተው››
********************************************
“ይድረስ ለኢጣሊያ መንግሥት፤ ሰላም ለአንተ ይሁን፤ የላክልኝን እንግዶች እነ ቀኛዝማች እጅጉ ለማን በአክብሮት ተቀብዬ በማስተናገድ ሥፍራ ወይም ቦታ ሰጥቻቸዋለሁ። ላንተ ግን ትርጁማን (አስተርጓሚ) ብለህ የላከውን ሌላ ቦታ ስትልክ እንዳይቸግርህ ልኬልሃለሁ። ልጅህን እመልስልሃለሁ ለምትለው ለአንድ ልጅ ብዬ እናት ሀገሬን ኢትዮጵያን ከድቼ ከአንተ ጋር በእርቅ መልክ አልደራደርም። ከዛሬ ጀምረህ በእኔ በኩል ያለውን ምኞትህን አንሳ። እኔን ፈልገህ ማጥፋት እንጂ አንዲት ልጅ ወስዶ ማስጨነቅና ማጉላላት ደስ የሚልህ ከሆነ እንደፈለክ አድርጋት። ሲሆን ለሷም የፈጠራት አምላክ እግዚአብሔር ፍቃዱ ከሆነ ከአንተው እጅ ላመጣት እችል ይሆናል። ጐጃምን በእንደራሴነት ልስጥህ ለምትለው አንተ የሰው ሀገር ሰው ከምትሰጠኝ እኔው ሀገሬን በሥሬ አድርጌ አስተዳድረው የለም ወይ?”
ይህ ወኔና እልህ የተሞላበት ግብረ መልስ ያፃፈው ጀግናው አርበኛ በላይ ዘለቀ እንደሆነ አያጠራጥርም፡፡ በ 5 ዓመቱ የኢትዮጵያ አርበኝነት ታሪክ ውስጥ ለ ሃገሩ ነፃነት ሲል ቤተሰቡን እንደ ፋሲካ በግ ለጣሊያን ሶላቶዎች የሰዋ እልኸኛና አስደማሚ አርበኛ በላይ ዘለቀ ነው፡፡
ለመሆኑ በላይ ዘለቀ ማን ነው?

Saturday, May 13, 2017

ቃል_አልባ_ስሜቶች

ደብልቅልቅ ሃሳቦች
ቃል አልባ ስሜቶች
እንደ ገጠር ሕፃን በ ጀርባዬ ታዝለው
እንደ ጨቋኝ ገዢ ከ ላዬ ተቀምጠው
ስሄድ ሲመልሱኝ ከ ፊቴ እያለፉ
ስመለስ ሲንጡኝ ከ ኋላ እየገፉ
ወዴት ብዬ ልሂድ ወደ የት ልራመድ
በ ምድር በ ሰማይ በ ታጠረ መንገድ፤

Wednesday, May 10, 2017

ለ መቶ ሺ ሰዎች...ምስጋና!

አራት ዓመት ጉዞ ውስጥ 116 ተለያዩ መጣጥፎችን አንባብያን ጀባ ብለናል፡፡ እነዚህ ውስጥ አራት አካባቢ ፅሁፎች በሌሎች ጓዶች የተሰናዱ ሲሆኑ ሌሎች ግን እኔ በራሴ የተሞነጫጨሩ ናቸው፡፡ እንግዲህ ‹‹ያለውን የወረወረ ፈሪ አይባልም›› በሚለው አባባል መሰረት ስድና ግጥም ካወቅነው እየጨልፍን ሃሳባችንን ስናካፍል ቆይተናል፡፡ መጣጥፎች ብዛት ተፃፉበት ዘርፍ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

Monday, May 8, 2017

የ አርበኛውና የ ደራሲው ጉዞ

(ጎዛመን-ደብረ ኤልያስ-አዲስ አበባ-ዳንግላ-ሽሬ-ወለጋ-ጅማ-ከፋ-ሱዳን-ኢጣሊያ-ኢየሩሳሌም-ኒውጀርሲ-ኒዮርክ-ጄኔቫ-እንግሊዝ-ሆላንድ-ኢትዮጵያ)
(ጥንቅር_ዘላለም ጥላሁን)
ነፃነት ቀንዲልን ለመቀዳጀት፣   ጨለማውን ዘመን ለመግፈፍ፣ ጭሰኞችን ቀንበር ለማራገፍ፣ ርትዕት የሆነች ፍትህን ለማስፈን፣ ሀገራቸውን ለማዘመን ሲሉ፤ ጠመኔያቸውን አስቀምጠው በረሃ ለበረሃ፣ ጫካ ጫካ ተንከራተዋል፡፡ ጠላት እጂ 7 ዓመት ግዞት ታስረዋል፡፡ ሾለ ብዕራቸውን አፎት ከፍተው ወረቀት ሰሌዳ ላይ አንብተዋል፡፡ ቀን ቀን ሀገራቸውን ቅንነት ሲያገለግሉ ውለው፤ ማታ ማታ ደግሞ ጭንቀታቸውንና ራዕያቸውን፣ ብሶታቸውንና ተስፋቸውን ብዕራቸው ሲተነፍሱ ያድራሉ፡፡ ሀገራቸውን መምህርነት፣ ርዕሰ መምህርነት፣ አርበኝት፣ ዲጵሎማትነት፣ ሚንስትርነትና ደረሲነት  ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ቅንነት አገልግለዋል፡፡ ኢትዮጵያ የዘመናዊ ስነ ፅሁፍ ታሪክ ( በተለይም ልቦለድ አፃፃፍ) ታለቅ ብርሃን  ፈንጥቀዋል፣ ዘመን አይሽሬው ፍቅር እስከ መቃብር ፀሀፊ--ክቡር ዶክተር አምባሳደር ሐዲስ አለማየሁ፡፡

Friday, May 5, 2017

‹‹የ አርበኞቹ ልጆች….››


አያቶቻችን፤
በ ሀገር ፍቅር የሰከሩ
አንበሳ ያሰገሩ
ጥሊያንን የገሩ
ሰንደቋን አንግበው
ረሃብ መከራን ታግሰው
ስለ ወገን  የሞቱ~ድንበር ያስከበሩ
እውነትም ጀግኖች ነበሩ!
እውነትም ፃድቆች ነበሩ!
አባቶቻችን ፤
በ እንጥፍጣፊ ፍቅር
ተዋድቀዋል ለ ሀገር!