Saturday, May 27, 2017

...ግንቦት 20 ሺ ዘጠኝ ሞቶ…

ሁሉም መንገዶች ግንቦት 20 አድርገው ወደ ህዳሴ ያመራሉ አንድ ወቅት በውቀቱ ስዩም እንዲህ የምትል ክሽን ቀልድ ቀልዶ ነበር፤
‹‹ ቀበሌው ሊቀመንበር አካባቢው ፈለቁ ሶስት ምንጮችን እየመረቁ ነበር፡፡ ከዚያ ምረቃው ስነ ስርዓት ለተገኘው ህዝብ እንዲህ የሚል ንግግር አሰሙ፤ ‹‹ ውድ ቀበሌያችን ህዝቦች እነዚህ ምንጮች መፍለቅ ዲሞክራሲያችንና መልካም አስተዳደራችን ውጤት ነው አሉ፡፡ ከዚያም ጭብጨባ ተቸራቸው››. አጨብጭበህ ሙት ያለው ህዝብ!

ወደ የት መሄድ እንደፈለግሁ ግልፅ ነው፡፡ ንጉሱ ዘመን መልካም ነገሮች ሁሉ ንጉሱ ችሮታ ተደርገው ይታሰቡ ነበር፡፡ ደርግ ዘመን ደግሞ ሁሉም መልካም ነገር አብዮቱ ውጤት፣ መጥፎው ነገር ደግሞ አድሃሪያኑ ሴራ ተደርጎ ይወሰድ ነበር፡፡

ጊዜ ሚዛን ነውና፣ ርእሰ ብሔር የነበረው ደርግ ‹‹ ብሶት የወለደው ጀግናው………….ግንቦት 20 ዘጠኝ ሞቶ…..›› ምትለዋ ብስራተ ዜና ድባቅ ተመቶ አንድ ጊዜ መሪነት ወደ አድሃሪነት ተቀየረ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የሙዚቃው ቃና…. ‹‹እድገት በህብረትና አብዮት›› ቀጥታ …‹‹ ሁሉ ታለፈ ብሔር ብሔረሰቦች፣ ግንቦት 20 ህዳሴ›› ተሰኙ ህብረ ዜማዎች ተቀየረ፡፡

ከዚህ የምንረዳው አመዛኙም ቢሆን መንግስታት የሰሩትን መልካም ነገር የማሞገስ፣ የደረሰውን ጉዳትና መጥፎ ነገር አለባብሶ የማለፍ ተለመደ ባህሪ አንዳላቸው መገንዘብ አይከብድም፡፡ ይህ ድርጊት ግንቦት ሃያ ፍሬዎች ጎልቶ የሚታይ እውነታ መሆኑን ከላይ ያነሳሁት ቀልድ በቂ ማስረጃ ነው፡፡
ምሳሌ ተለያዩ ሚዲያዎች የምንሰማቸውን ግንቦት ሃያ ውጤቶች እንመልከት፤
1)    ብሔር ብሔረሰቦች መብትና እኩልነት
2)    11 መቶ እድገት
3)    ህዳሴው ግድብ
4)    / ቴድሮስ ምርጫ
5)    ኢንቨስተሮች መብዛት….እያለ ይቀጥላል፡፡
በዚሁ አጋጣሚ የግንቦት ሃያ ፍሬዎች እንኳን ግንቦት 20 አደረሳችሁ! ነገርግን ከላይ የጠቀስናቸው የግንቦት 20 ፍሬዎች ናቸው ብለን ካመንን፣ ባለፉት ሁለት አሰርት አመታት ያየናቸው ሚከተሉት የምን ፍሬዎች ናቸው? ወይስ ሌላ የማናውቀው ዛፍ ይኖር ይሆን???

1)    ከፍተኛ የሆነ የኑሮ ግሽበት
2)    ከፍተኛ የሆነ የሙስና መንሰራፋትና አገልግሎት ብልሹነት
3)    መሰረታዊ የሆኑ ሰው ልጅ ፍላጎቶች እጥረት (ምግብ፣ መጠለያ፣ ልብስ……ወዘተ)
4)    ዘርንና ጎሳን መሰረት ያደረገ አድሎ፣ መገለልና ግጭት
5)    ስደትና እስራት……….እያሉ መቀጠል ይቻላል ግን ዘርዝሮ መጨረስ አይቻልም፡፡
አንድ ስሙን የማላውቀው ፈላስፋ እንዲህ የሚል ጥሩ ጥቅስ አለው፡ ‹‹Do not speak your success day and night, the success speaks by itself; instead please speak loudly about your failure and request others to get you up››

ቁርስ ሳይበሉ ትምህርት ቤት ለሄዱ ህፃናት፣ ጎዳና ዳር ቁጭ ብለው ዘመን ለሚረግሙ አዛውንቶች፣ ኑሮ ግሽበትና የገቢ አለመመጣጠን እንዲሁም የመጠለያ እጦት እንደ እግር እሳት ላቃጠለው ማህበረሰብ እድገት ምንድን ነው???…..ወይስ እድg ትርጉም ሃበሻ      አይገባውም?

‹‹ዌል አንግዲ!››……ወይስ በተደጋጋሚ እንደምነሰማው መልስ  ‹‹ይህን ችግር ኢኮኖሚ እድገቱ ያመጣው መገፋፋት ነው›› በሚል አረፍተ ነገር ዘግተነው እንለፍ….ግን እስከመቼ?….  እስከመቼ ነው ገመናችን ላይ ነጭ ሸራ ዘርግተን በላዩ ላይ የፅጌረዳ አበባ ነስንሰን አሼሸ ገዳሜ የምንጨፍረው?  

ስለዚህ ቆም ብሎ መንገዶቹ ግንቦት ሃያ ወደ የት እየሄዱ መሆኑን መመርመር ወሳኝ ይመስኛል፡፡ ወደ ህዳሴ ያቀኑትን መንገዶች ብቻ መዘመር ውጤቱ እምባ የተቀላቀለበት እስክስታ መሆን አያልፍም!
ጊዜ ኩሉ!
 © Zelalem Tilahun @ 2009



No comments:

Post a Comment