Thursday, May 18, 2017

‹‹የ ወንድ ልጅ ልቅሶ››

መች ጠገብሁሽና እንዴት ይድላኝ አልጋዬ
ፍቅርሽ ፀንቶብኛል እኔ አልተኛም ጨርሶ፣
……………
ማታ ማታ ማልቀስ ነው ስራዬ
…..እንዲህ እንዲህ እያለ ገርማሞ ልጅ ብሶቱንና እውነታውን አደባባይ አንጎራጉሮ እኛንም ሆድ አስባሰን፡፡ እኛ ማህበረሰብ ሴት ልጅ ብቻ አልቃሻ ተደርጋ ትወሰዳለች፡፡ ነገር ግን የወንድ ልጅ አልቃሻምነት ይብሳል፡፡……………ሴት ልጅ እምባ ዘለላዎችን አፍሳ የውስጧን እሳት ከፊልም ቢሆን ታበርዳለች፡፡ ወንድ ልጅ ግን ውስጡ እያነባ እምባ ዘለላዎቹን ጥርሱን ነክሶ ይታገላቸዋል፡፡ 
...................ለምን ቢሉ አንድም ሽንፍት ምልክት አድርጎ ስለሚቆጥረው፣ ወይም……..‹‹‹ደግሞ እንደ ሴት እንዴት ታለቅሳህ???›› የሚለውን የማበረሰብ ትችት መፍራት፡፡
ሚገርመው ግን ይህን አደባባይ አምቆ የያዘውን እምባ፣ ማታ ወደ ቤቱ ሲገባ ጨለማን ተገን አደርጎ ይዘረግፈዋል፡፡ እንደ ሳት በሚያቃጥሉ እምባ ዘለላዎች የታቀፋቸውን ትራሶች ሲያርሳቸው ያድራል፡፡ ወንድ ልጅ ትራስ ብዙ ጊዜ ቶሎ የሚቆሽሸው በዚህ ምክንያት ይመስለኛል፡፡ ይህ ውሽት ከሆነ ወንዶች ይመስክሩ፡፡ አልቃሻም ብቻ!-ውሸት ነው???
እናንተ ብትዋሹም ቴዎድሮስ ግን ሌሊት ሌሊት እምባ ዘለላዎቹን ሲያፈስ ማደሩን በዜማ አንጎራጉሯል፡፡ ይህ የሆነበትንም ምክንያት በሰጠው ቃለ መጠይቅ ሲያስረዳ እንዲህ ብሎ ነበር:
‹‹ ባለቤቴ (አምለሰት) ሰውነቷ ጋር ተፈጠረ መድሃኒት ታቃርኖ ምክንያት ወደ ውጭ ሄዳ እንድትታከም ተወስኖ ለማሳከም ይጃት ስሄድ …. አገር እንዳልወጣ ተወስኖብኝ ወደ ቤቴ ተመለስሁ፡፡ አንድ ወር ያህል እሷ ተለይቼ ዛሬ ያዜምሁትን ህይወት አሳለፍሁ፡፡ ወንድ ልጅ ጨለማ ለብሶ ያልቅሳል እንዲሉ-እኔንም ማታ ማታ ይሞክረኝ ነበር››
ይህንን እውነታ ነው ብላቴናው ‹‹ማራኪዬ›› ላይ፡
‹‹ ናፍቆትሽ አምባ እየራሰ አልጋዬ
ካላንቺ አቅቶኛል ማደር ለብቻዬ››………………..ሲል ስሜቱን በዜማ ያንቆረቆረው፡፡
ምክንያታችን ይለያይ እንጂ ሁላችንም ጨለማ ጋርደን፣ ትራስ ስር ተወሽቀን እምባ ዘላለዎችን ማፍሰስ ወደ ኋላ አንልም፡፡
የሰው ልጅ አምስት ነገሮች ያለቅሳል፡ ፍቅር፣ ቁጭት፣ ብሶት፣ ፀፀትና ሃዘን፡፡
ሰውነት ከፍ ያለ መላካዊ ልዕልና ያለው ሰው ካልሆነ በቀር ሁሉም ሰው እነዚህ አንዱን ይቀምሳል፡፡ ቀመሰው መጠን ህሊናው ያነባል፣ ውስጡ ይብሰለሰላል፡፡ ከፍ ሲል ደግሞ እምባ ዘለላዎቹ እራሱን ይፈውሳል፡፡ ለጊዜውም ቢሆን እራሱን ይፈውሳል፡፡ …..ይህን ሳስብ ሴት ልጅ መሆን እድለኛነት ነው፣ ህመማቸው ፈውስ አይኖቻቸው ጫፍ ነው፡፡
እዚህ ጋር አንድ ነገር ልጨምር፡ 
ቴዲ አፍሮ ዘፈን ግጥሞች ዘርፈ ብዙ የሆነ ትርጉም እንዳላቸው፡፡ እሱ ስለ ባለቤቱ ፍቅር የዘፈነውን፣ ብዙዎች ስለ ሃገር፣ ስለ እናት፣ ስለ ልጅና ስለ አህት እየቀየሩ ሊያዳምጡት ይችላሉ-ልክ እንደ አኔ!
ከሁሉም በላይ በዚህ ምድር ሰላም መኖር ትልቁ ነገር ይቅር ባይነት ነው፡፡ ሰው ልጅ መጀመሪያ ለራሱ ይቅርታ ማድረግ አለበት፡፡ ፈውስ መጀመሪያው ይቅርታ ነው፡፡ ሰው ልጅ ለራሱ ህሊና ይቅርታ ሳያደርግ ለሌላ ሰው ይቅርታ ሊያደርግ አይችልም፡፡ ይቅርታንም ምላሱ ሳይሆን በልቡ መቀበል አለበት፡፡ ቂም ይዞ ፀሎት እንዲሉ ….ሁሌም ቢሆን ጥላቻና ቂምን ልብ ይቅር ብሎ መኖር ጥቅሙ ለራስ ነው- ብሩህ ቀን፣ ንፁህ ህሊናና ሰላማዊ አንቅልፍ ሲባል!...
ይህንንም እውነታ ብላቴናው‹‹መማፀኔውስጥ ሚከተሉት ይቅርታ ስንኞች ይማፀናል!
‹‹በደለኛ ሰው ይቅር ብሎ አምኖ ሰው ካሰ
ይኖር ወይ ልቡን ያልመለሰ››
………
‹‹ሳይገባኝ እኔ የቱ እንደሆን እንኳን ማስቀየሜ
ተይ ብያት ነበር ባለኝ አቅሜ››
ሻሎም!!!
ፈጣሪ ይቅር ባይ ልብ ይስጠን!
© 2009 ዓ.ምTop of Form

No comments:

Post a Comment