Thursday, April 2, 2015

ተስፋ


 
ሁሌም ይታየኛል አንዳች ሩቅ ተስፋ
የዛሬ ያልሆነ የነገ ያልሆነ በጊዜ ሚገፋ
እንደ ህልም ያለ እውነት የመሰለ
ከመሬት ከፍ ያለ ከሰማይ ዝቅ ያለ
የህሊና ምስል ሰዓሊ ያልሳለው
ደራሲ በምናብ በብዕር ያልከተበው
ምሁር በምርምር ደርሶ ያልጨበጠው
ግብር ማልከፍልበት መንግስት ያላወቀው
ከእኔ ጋራ ያለ ተስፋዬ ብቻ ነው፡፡
             ዘላለም፤ ሰኔ 2006 ዓ.ም፣አዲስ አበባ

No comments:

Post a Comment