Friday, September 4, 2015

የ “አሉ” ዘመን

አሉነው ዘንድሮ
እውነትማ ጠፋ በውሸት ተቀብሮ
....“አሉ”....
ጋዜጠኞችአሉ
በሸፈጠ አንደበት ቃላት እየቆሉ
.......“አሉ”.....
ነጋዴዎችአሉ
በለስላሳ አንደበት ህዝብ እያታለሉ
.....“አሉ”.....
ባለስልጣኑአሉ
የህልም እንጀራ ህዝብን እያበሉ
.....“አሉ”......
መምህራኑምአሉ
ሳይንስን እረሱ ኑሮን እያሰሉ
......“አሉ”.....
የትም ቦታአሉነው 
አሉድንበር አልባው
አሉነው ዘንድሮ 
አውነትም የትአል በዘመን ተቀብሮ
......“አሉ”.....
ቀሳውስቱምአሉ
ህግጋቱን ረስተው መሰለኝ እያሉ
ንግድ ጀምረዋል ቁማር በመስቀሉ
........“አሉ”.....
ሸሆችም ሸፈጡ ወደአሉዞሩ
ቁራንን ረስተው ገንዘብ እያስቀሩ
........“አሉ”.....
ትውልዱ ሸፍጠኛ አሉየሰከረ
በእናቱ የሚያሾፍ ሳይኖር የነበረ
......“አሉ”.....
አሉነው ህዝበ አዳም 
አሉብሎ ያድራል ቢሆንም ባይሆንም
......“አሉ”.....
የኔም ቃልአሉነው በዚህ አሉዘመን
አሉእየኖርን አሉእንሞታለን 
ነውነበር ህሊና ውስጥ ቀብረን
***********************************
ነሐሴ 27 2007 .
አሉየሚለው ቃል ላልቶ ይነበብ፡፡



No comments:

Post a Comment