Thursday, April 7, 2016

“ጊዜ በረርክ… በረርክ…”

ጊዜ እንዴት ይሮጣል፡፡ እነሆ ደርዘን አመታት ያለመታከት እንደዋዛ ነጎዱ፡፡ አንዳንዴ ቆም ብዬ ሳስበውየሰው ልጅ ዕድሜ እንደ ጥላ ያልፋል” የሚለው አገላለፅ እራሱ በቂ አይመስለኝም፡፡ ዞር ብለን የህፃንነት ዘመናችንን ስናስታውስ እጃችን የምነካው ያክል የትናንት ትዝታ በጣም ቅርብ መስሎ ይሰማናል፡፡ …..ነገር ግን በመሃከላችን በጊዜ መስፈርት ስናያቸው፡ 20 በላይ ድፍን ዓመታት ወይም …… 240 በላይ ወራት ወይም….. 624 በላይ ሳምታት …..ወይም 7300 በላይ ቀናት ….ወይም 175 200 በላይ ሰዓታት ….ወይም 10.5 ሚሊዮን በላይ ደቂቃዎች  …ወይም 630 ሚሊዮን በላይ ሰከንዶች  ….ወይም….
630 ትሪሊዮን በላይ ማይክሮ ሰከንዶች በልጅነታችንና በዛሬ መካከል እንደ ዘበት አልፈዋል፡፡ ላይመለሱ የውሃ ሽታ ሁነዋል…….ኧረ ውሃስ አንዳንዴ ይሸታል፡፡
 ገጣሚው፡
ካልተሳፈሩበት ቶሎ ተሽቀዳድሞ
ጊዜ ታክሲ አይደለም አይጠብቅም ቁሞ
ያለው በትክክልም ያለፈን ጊዜ ማስታወስ እንጂ መመለስ እንደማይቻል ያሳያል፡፡ ቢሆንማ ኑሮ ስንቶቻችን እድሜያችንንፓውዝእናደርገው ነበር……በተለይ………….. በተለይ……..ኡኔ አላልሁም….እንዳታጣሉኝ!
ይሁን እንግዲህ ትናንት እንደዋዛ አለፈ…….ነገስ?......….ነገስ?.....
ድሮ ድሮ እያንዳንዱ ቀን አወፋፈሩና ስፋቱ አንድ ሙሰኛ ባለስልጣን ቦርጭ ይበልጥ ነበር፡፡ አሁን ጠባ ስትሉት ይመሻል፡፡ ሳተኙ ይነጋል፡፡ ቀኑን ምን ነካው???? ጊዜውን ምን ነካው??? እንደ ኑሯችን በረከት አጣ እንዴ??? ይርማል የተወለደ ልጅ ሳይጎረምስ ማርጀት ጀምሯል፡፡ …………ምን ይሻላል???
ይህን የተገነዘበ አንድ #ቀልደኛ ሙሾ አውራጅ ዘመኑን እንዲህ ይገልፀዋል፡
            “የተራበው ሳይጠግብ ያጣውም ሳይለብስ
                 ስምንተኛው መጣ ፈረስ
……በእርግጥ ይህ ግጥም በጥንት ኢትዮጵያ ዘመናዊ ትራንስፖርት ጋር ሳትተዋወቅ ገጠር ውስጥ የተገጠመ ነው፡፡………ይህ ሙሾ አውራጅ አሁን ቢኖር ኖሮፈረስ” የሚለውንባቡር” ወይምአውሮፕላን” በሚል ቀይሮ እንዲህ ብሎ ይገጥም ነበር፡
                  የተራበው ሳይጠግብ ያጣውም ሳይከብር
                    ስምንተኛው መጣ ባቡር” ……
ሴት ሙሾ አውራጆች አንድ ልመርቃችሁ፡፡ ባል በጊዜው ያላገባችና ልጆችን ወልዳ ማቀፍ ያልቻለች አንዲት ሴት ብሶቷን አደባባይ እንዲህ ስትል አዚማለች፡
                   “ያሰብሁትን ሳልሆን ያሻኝን ሳልበላ
                        በ ከንቱ አለፈ ዕድሜዬ እንደ ጥላ
መጨረሻም ጊዜን ተችቶ ያለ ጊዜው ያለፈውን “ተናዳፊው ገጣሚ” ደበበ ሰይፉን ግጥም በማንሳት እኛም ጊዜን ወርፈን እንሰነባበት፡፡
ጊዜ በረርክ በረርክ
ጊዜ በረርክ በረርክ
ጊዜ በረርክ በረርክ
ግና ምን አተረፍክ
ግና ምን አጎደልክ?
ሞትን አላሸነፍክ
ሕይወትን
አልገደልክ”
 ደበበ ሠይፉ, 1992


No comments:

Post a Comment