Friday, April 19, 2013

አዎን እኖራለሁ

ምላሴን ሲመረኝ በጨው እያጣፈጥሁ
ክፉውን ስሰማ በጎውን እያሰብሁ
ንዴት ሲያቃጥለኝ ሻወር እየወሰድሁ
ቀን ያለፋል እያልሁኝ ቀናት እየቆጠርሁ
        እንዲህ እጓዛለሁ
        እንዲህ እኖራለሁ
ህሊናየን ትቼ ለስጋ እያደላሁ
ነፃነቴን ትቸ ሆዴን እየሞላሁ
       እንዲህ እጓዛለሁ
       እንዲህ እኖራለሁ
አዎን አንኖራለሁ ሆዴን እየሞላሁ
     ህሊናን እያስራብሁ
     እነዲሁ ዝም እያልሁ
     አዎን አንኖራለሁ
ቢጨንቀኝ ነው እንጂ ሂጀስ የት እደርሳለሁ፡፡

No comments:

Post a Comment