Friday, November 15, 2013

ህይወቴ



 
ህይወቴ ሜዳ  ናት

የጠገበ ሁሉ- ኳስ ሚጫወትባት

ህይወቴ መንገድ ናት

ባለጊዜው ሁሉ የሚደፈጥጣት

ህይወቴ መሬት ናት

ባለጊዜው ቱጃር ቤት የሚሰራባት

ሕይወቴ ባዶ ናት

የምትመካበት መጠጊያ የሌላት



እኔም ችላ ያልኋት ሰዎችም የናቋት

አንድ እግዜሩ ብቻ ጨክኖ ያልተዋት

የረፋዷ ፀሐይ ህይወቴ ይች ነች

በዘር በሃይማኖት በ ደም የጨቀየች

በነገ በዛሬ እኔም የምኖረው

የህይወቴ ድርሻ 'ጣው እስኪወጣ ነው
        ህዳር 2006 ዓ.ም (በስደት ሀገር በግፍ ለተገደሉት መታሰቢያ)

No comments:

Post a Comment