Friday, July 10, 2015

ህሊና ብቻ ነው!

ጥላቻ ከፍቅር
መኖር ካለመኖር
ፅድቅና ኩነኔ
ፍርሀትና ወኔ
እውነትና ሐሰት
መውደድና መጥላት
ጤና ከበሽታ
ሀዘን ከደስታ
መማር ካለመማር
እብደትም ከስካር፤
 ተቀላቅለውብኝ
ድንበሩ ጠፍቶብኝ
ለመክፈል ስዳክር
ስዳክር
       ስዳክር
                        ስዳክር…         
መሃል ላይ ሳሰምር
እንደገን አጥፍቼ
ግራ ቀኝ ጎትቼ
ሚዛን ላይ አውጥቼ
      ሳሰምር
            ሳሰምር
                 ሳሰምር
ድንበሩን አጣሁት
ደከመኝ አቆምኩት፤
ለካስ በትክክል
ሳያንስ ከፍ ሳይል
እኩል የሚከፍለው
        የሰው ልጆች ሚዛን
ህሊና ብቻ ነው!

 / Zelalem T/
      ሐምሌ 2 2007 .

No comments:

Post a Comment