Monday, July 18, 2016

"ወረድን......."

ቁልቁል ተራመድን~ከስልጣኔ ጓዳ 
ተራራውን ለቀን~ወረድን ወደ ሜዳ፤
ወረድን እምነት
ወደ 'ሸት ማንነት 
ወጣን ሰውነት

.....

.........

..............
......

.......

............

..................
.....
አንድ ሁለት እያልን


.....

.........

..............
......

.......

............

..................
....
መንገዱ እስኪጠፋን....
በጭንቅ በመከራ~ሜዳ ላይ ደረስን!
ሜዳው ላይ ሳናተርፍ
ደረስ' ገደል አፋፍ
አቃተን መሻገር
ዞርን ወደ ኋላ~ወደ ትናንት መስመር
ሞከርን ልንመለስ
ተራራውን ወጠን~ትናንትን ልንዳብስ፤
ሽቅብ ወደ እምነት
ሽቅብ ወደ እውነት
ማቅናት ግን አቃተን
ከተራራ ወርደን~ገደል ስናይ አድገን
!


2 comments:

  1. ዋው ዘላለም!
    መራራ እውነት!
    ዘመናዊነት ይሄን ትውልድ (እኛን ማለቴ ነው) ከእውነትና ከህሊና ድባብ አውጥቶ ለምንም የማይበጅ ቀሽም አድርጎናል
    ውበትን በተላበሰ መልካም አንደበት ወቀርከን!
    በሁሉም ስለሁሉም ከልብ እናመሰግናለን!!

    ReplyDelete
  2. ዋው ዘላለም!
    መራራ እውነት!
    ዘመናዊነት ይሄን ትውልድ (እኛን ማለቴ ነው) ከእውነትና ከህሊና ድባብ አውጥቶ ለምንም የማይበጅ ቀሽም አድርጎናል
    ውበትን በተላበሰ መልካም አንደበት ወቀርከን!
    በሁሉም ስለሁሉም ከልብ እናመሰግናለን!!

    ReplyDelete