Thursday, August 31, 2017

የ ሲኦል ነፍሳት: ክፍል ፬

እየቀረበችኝ ስትመጣ የሰውነቷ ሙቀት እንደ በረሃ ቋያ ክፉኛ መጋረፍ ጀመረ፡፡ ምን እንደ ነካኝ አላውቅም ሰውነቴ እንደ በድን መንቀሳቀስ አቁሟል፡፡ 

አሁን ነፋስ ማሳለፍ በማይችል ክፍተት ተጠጋችኝ፡፡ አላመነታችም-እጆቿን ዘርግታ ወደ አንገቴ ጠመጠመቻቸው፡፡ እሳት የመሰለው ከንፈሯን ከከንፈሬ ጋር ለማዋሃድ ጠጋ ስትል እንደ ጦር የሾሉት ጡቶቿ ደረቴ ላይ አረፉ፡፡ ሰውነቴን አንዳች ሃይል አነዘረኝ፡፡ መላ ሰውነቴ እንደ ወንዝ ቄጠማ መራድ ጀመረ፡፡ 

ከንፈሯ ከከንፈሬ ከመዋሃዱ በፊት ነፍሴ ስጋዬን መግዛት አለባት፡፡ አሊያ እቅዴ ሁሉ ብልሽትሽቱ መውጣቱ ነው፡፡ በዚህ ሠዓት አደብ መግዛት በጣም ከባድ ነው፡፡ አእምሮዬ እኔ አይደለም፡፡ 

‹‹
ሰው ልጅ ትልልቅ ጥፋቶችን ከማጥፋት የሚድነው መላ ሰውነቱን ስሜት፣ ንዴትና ብስጭት በተቆጣጠረበት ወቅት አንጎሉ ምትላክ ‹‹ተው!……ረጋ ብለህ አስብ›› በምትል ትንሽ መልዕክት ምክንያት ነው››፡፡ በዚች መልዕክት ምክንያት የቀኑ ብዙ ሰዎች ጉዳትና ከሞት፣ ብዙ እንስቶች መደፈርና እንግልት ይድናሉ፡፡››……….ይች መልዕክት ድርጊቱን ፈፅመን የምናገኘውን እርካታ፣ ነገ ከሚደርስብን መንፈስ መረበሽና አእምሮ ፀፀት ጋር ‹‹ማይክሮ ሰከንድ›› ወይም ‹‹ሴኮንድ›› አስበን እንድንወስን ትረዳናለች፡፡ ይህ ሰውን ልጅ እንስሳት የሚለይበት አንዱ ፀጋ ነው-ሰከን ብሎ ማሰብ!፡፡

እኔ ግን አንጎሌ ፍርሃት እንጂ መልዕክት አልመጣም፡፡ ትክክለኛውን ከስህተቱ፣ ፅድቁን ከኃጢያቱ መለዬት ጊዜው አልፏል፡፡ በዚህ ሁኔታ ላይ ሁኖ ‹‹ይህ የነፍስ………..ይህ ደግሞ የስጋ ስራ ነው›› ብሎ መለየት እጅግ ይከብዳል፡፡ ጠቢቡ ሰለሞን እንዳለው ‹‹………እሳትና ጭድ አንድ ተገናኝተው…..እሳቱ ጭዱን ሳያነደው መለየት በጣም ከባድ ነው››፡፡ እነሆ እሳትና ጭድ ተገናኝተዋል፡፡ እሷ እሳት፣ እኔ ጭድ!

ማሪያናም ትንፋሸ እንደ አውሎ ንፋስ ይጋረፋል፡፡ ቁመት እሷ ትንሽ ረዘም ማለቴና ከንፈሮቿን ቀጥታ ወደ ከንፈሮቼ አለመላኳ ፋታ ሰጦኛል፡፡ አንገቷ ቀለስ ብላ ከንፈሮቿን ወደ አንገቴ ላከቻቸው፡፡ የትንፋሽዋ ሙቀት አንገቴን ሲያወረዛው ይሰማኛል፡፡ ሰውነቷ ይንቀጠቀጣል፡፡…….አሁን እኔም ሰውነት መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡ ሽባ የነበሩት ሁለቱ እጆቼ በፍጥነት ማሪያና ወገብ ተጠመጠሙ፡፡ ማሪያና አንገቷን ቀና አድርጋ አይኖቼ ላይ ማፍጠጥ ጀመረች፡፡ አይኖቿ መስለምለም ጀመሩ፡፡ እሳት የመሰሉ ከንፈሮቿን አይኖቿን ጨፍና ወደ እኔ ላከቻቸው፡፡ 

ግን እንዳሰበችው አልተሳካም፡፡ ከንፈሯ ከንፈሬ ከመዋሃዱ በፊት፣ አንዳች ልዩ ኃይል እጆቼን ወገቧ እንዳነሳ አዘዘኝ፡፡ በፍጥነትም…….ይቅርታ ብዬ አንገቴ የተጠመጠሙትን እጆቼን ፈንቅዬ አልጋው ላይ ሄጄ ቁጭ አልኩ፡፡ 
‹‹
ምን ሆነህ ነው?›› አለችኝ ማሪያና በተቆጣ ድምፅ

‹‹
….…….….……ማሪያና›› አፌ መንተባተብ ጀመረ፡፡

‹‹
የውልሽ ማሪያና አንቺን ከእኔ ጋር ይዤሽ የመጣሁት ዝሙት ልፈፅም አይደለም››፡፡

‹‹
እና ምን አስበህ ነው? እኔ ምንድን ነው የምትፈልገው? ማነህ አንተ?›› የጥያቄ መዓት ታዥጎደጉድብኝ ጀመር፡፡

‹‹
ምንም ምንም……..የተለዬ ሃሳብ የለኝምዝም ብለን አብረን እንድናድር…..እባክሽ ተረጋጊ››

‹‹
አረ ……….እሺ የእኛ ፃድቅ….ምን ልታደርገኝ ነው…….ንገረኝ! ….ነው ፊልም እየሰራህ ነው! ›› አለች ጮክ ብላ!…....ፊቷ እንደ ተቆጣች አራስ ነበር ያስፈራል፡፡

‹‹
እባክሽ ቁጭ በይና ላስረዳሽ›› አልኳት እጇን በእጄ እየሳብሁ፡፡

‹‹
ልቀቀኝ…….መረዳት አልፈልግም….ለእራት ያወጣኸውን አንድ ቀን እከፍልሃለሁደህና እደር›› ብላኝ እየተንደረደረች ልትወጣ ስትል በር ጋር እጆቿን ያዝኋት፡፡ ገፍትሬ አልጋው ላይ ካስቀመጥኋት በኋላ በሩን ቆልፌ ቁልፉን ኪሴ ከተትሁት፡፡

‹‹
ምን ልታደርገኝ ነው……ክፈትልኝ ልሂድ….ምን …..አሊያ እጮሃለሁ›› አለችኝ …. አይኖቿ ዘለላ እምባዎች መውረድ ጀምረዋል፡፡

‹‹
ማሪያና እመኝኝ ምወደው ነገር ሁሉ እምልልሻለሁ፣ አልጎዳሽም፡፡ አዳር ቃል የገባሁልሽንም ብር እሰጥሻለሁ፡፡ ግን ተረጋጊና እንነጋገር…..ከዚያ በኋላ ካልፈለግሽ መሄድ ትችያለሽ›› አልኋት ቁጢጥ ብዬ እጆቼን ጉልበቷ ላይ አድርጌ እየተለማመጥሁ፡፡

‹‹
አልፈልግም……ሁኔታህ አላማረኝም….. መሄድ እፈልጋለሁ›› አለችኝ ከተቀመጠችበት እየተነሳች በተጨነቀ ድምፅ፡፡

‹‹
እኔም ተበሳጨሁ፡፡ እኔ እኮ ሰው ነኝ፡፡ እንደ አንች ሴት እናትና እህት አለኝ፡፡ ይጎዳኛል ብለሽ ካሰብሽ ሂጅ፡፡ መሄድ ከፈለግሽ ሂጅ!.. ይኸው ተነሽ ሂጅ!›› …….300 ብርና የበሩን ቁልፍ ዘረጋሁላት፡፡ አመነታች፡፡

‹‹
እሺ ምን አስበህ ነው?›› አለችኝ እንደ ህፃን ልጅ ሆድ በሚያባባ ድምፅ

‹‹
የውልሽ ማሪያና ቁጭ በይና ላስረዳሽ…..መሄድ ከፈለግሽ ትሄጃለሽ…. እኔ እሸኝሻለሁ›› አልኳት፡፡

‹‹
እሺ›› ብላ አልጋው ጠርዝ ተቀመጠች፡፡
እኔም ጠጋ ብዬ ተቀመጥሁና በእጆቼ እምባዋን ጠረግሁላት፡፡ ተረጋጊ ብዬ ጫንቃዋን መታ መታ አደረግኋት፡፡ እንድትረጋጋ እጆቿን ጨበጥኋት፡፡ ሁሉ እንደ እሳት ይፋጅ የነበረ ሰውነታችን ሙቀት ውሃ ሽታ ሁኗል፡፡ ምትኩ ሰውነታችን ቀዝቅዟል፡፡ 

‹‹
ብዙ ጥፋቶች ስክነት ጉድለት ናቸው፡፡ ብዙ ዓለም ጥፋቶች ስሜት፣ ንዴት፣ በብስጭት፣ እልህ፣ ምርቃናና በስካር ምክንያት የመጡ ናቸው፡፡ ብዙ እንስቶች ሰቆቃና እንግልትም ደቂቃ ውስጥ ተኖ ሚጠፋ ስሜት ጊዜያዊ እስረኛ በመሆን የሚፈጠር ጥፋት ነው፡፡›› 

‹‹
እሺ…..ምን አስበህ ይዘኸኝ መጣህ ንገረኝ›› አለችኝ፡፡ አሁን አንፃራዊ መረጋጋት ይታይባታል፡፡ 

‹‹
ሴት ልጅ እንባዋን ከጠረግህላትና እጆቿን ጨብጠህ ጫንቃዋን መታ መታ ካደረግሃት ቶሎ የመፅናናት እድሏ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ አብረሃት ማልቀስ ጀመርህ ግን እንባዋ መቀበያ እቃ አዘጋጅ›› ሚል ነገር ያነበብኩ መሰለኝ፡፡…..ለዚህም ነው፣ እኔንም እምባ ቢተናነቀኝም ዋጥ አድርጌ የማፅናናት፡፡ እግዜር ማይጨክንባቸው ነገሮች አንዱ የሴት ልጅ እንባ ነው፡፡ አንዳንዴ ሳስበው እግዜሩ ‹‹አዳምን አፈር፣ ሔዋንን ደግሞ አዳም የግራ አጥንትና ውቅያኖስ ውሃ ቀላሎ የፈጠራቸው ይመስለኛል››

‹‹
አየሽ ማሪያና የሰው ልጅ የተለያዬ ነገር ያስደስተዋል፡፡ ግማሹን መብላት፣ ሌላውን መጠጣት፣ ሌላውን ዝሙት……..›› አላስጨረሰችኝም፡፡

‹‹
ቁስሌን አትንካው ወደ ገደለው ግባ›› አለችን ተቆጣ ድምፅ፡፡

‹‹
እሺ ይቅርታ እነግርሻለሁ፡፡ እኔ ወደ ባር የመጣሁት አብራኝ የምታድር እንስት ፍለጋ አይደለም፡፡ ብቸኝነቴን ለመርሳት ነበር፡፡ ከዚያ ግን ቤት ውስጥ ያየሁት ነገር አስደነገጠኝ፡፡ ብዙ እንስቶችን አየሁ፡፡ ሁሉም አራጃቸውን የሚጠብቁ ናቸው፡፡ ውስጤ በጣም አዘነ፡፡ ከዚያም በዚያ ሌሊት ቢያንስ አንዲት እንስት ነፍስ ለማሰረፍ ወሰንሁ፡፡ እንደ አጋጣሚ ፊት ለፊቴ ስለነበርሽ አንቺን ጠራሁሽ፡፡ እርግጥ ቅድም ስትቀርቢኝ አቅፌሽ ነበር፡፡ ስሜታዊ ሁኜ ነበር፡፡ አትፍረጅብኝ፣ ሰው ነኝ፡፡ ሰው ስለሆንኩ ስሜቴ ፈተነኝ፡፡ ስሜቴ በላይ የአንቺ ሁኔታና አቀራረብ ፈተነኝ፡፡ ግን ከራሴ ጋር ታግዬ ስሜቴን ለመቆጣጠር መኮርኩ፡፡ ከዚያም የሆነው ሁሉ ተፈጠረ፡፡ ይህ ነውአሁን ከፈለግሽ እደሪ……..…አሊያ የምትፈልጊው ቦታ አድርሸሽ እመለሳለሁ….›› ብዬ ብሩን ከእጇ ጎን አስቀምጬ ወደ መስኩቱ ሄጄ ማዶ ማዶ ማዬት ጀመርሁ፡፡

በመካከላችን ዝምታ ሰፈነ፡፡ ከዚያም ‹‹እእእ›› የሚል ድምፅ ዝምታውን ሰብሮ ወጣ፡፡ ዞር ስል ማሪያና እያለቀሰች ነው፡፡ 

‹‹
ይቅርታ ማሪያና እኔ መልካም ብዬ ያሰብኩትን ነገር ነበር ያደረግሁት፡፡ ካሳዘንሁሽ በጣም ይቅርታ አልኋት››

‹‹
አንተ አይደለም…..አንተ ራስህ መልካም ነህ፣ እኔን ግን ያመኛል››

‹‹
ለምን››…ኤጭ ይህን ቃል አሁንም ደገምሁት፡፡

‹‹
ምክንያቱም እኔ ወንድ ልጅ ስሜቱን ብቻ የሚከተል መደዴና ሴት ቁስል የማይራራ አውሬ እንደሆነ ነው የማምነው፡፡ አንተ ግን አምነቴን እየተፈታተንኸው ነው፡፡ እውነት ነው ብዬ እንዴት ልመን?››

‹‹
ይገባኛል ማሪያና!…ይገባኛል!....›› ብዬ እንደ በፊቱ መፅናናት ጀመርሁ፡፡ በፊቱ ሙከራ አሁንም ተሳክቶ በቶሎ ዝም አሰኘኋት፡፡ 

‹‹
አየሽ ማሪያና…….ትናንት ብዙ ቁስል ይኖርብሽ ይሆናል፡፡………ትናንት ግን ዛሬ የለም፡፡ ዛሬ ሌላ ቀን ነው፡፡ ነገም እንዲሁ ሌላ ቀን ነው፡፡ እያንዳንዱ ቀን የራሱ ክፋትና መልካም አጋጣሚ አለው፡፡ እኔም ሌላ ሰው ነኝ፡፡ ሁሉንም ሰው አንድ አይነት ነው ብሎ ማሰብ ይከብዳል፡፡ ክርስቶስን አይሁዳውያን አመኑት፣ አይሁዳውያን ተከተሉት፣ አይሁዳውያን ሰሱት፣ አይሁዳውያን ሰቅሉት፡፡ እነ ይሁዳ ተደራድረው ሲሸጡት፣ እነ ዮሐንስ መስቀሉን ተሸክመው አገዙት፡፡ እነ ሌንጌኒዎስ ጦር ሲወጉት፣ እነ ኒቆዲሞስ ቁስሉን አጥበው ቀበሩት፡፡ ሰውን በዘር፣ በፆታ፣ በሐይማኖትና በጎሳ ጠቅልሎ መልካም ነው፣ ክፉ ነው ማለት ስህተት ነው፡፡ የሁሉም ሰው ተግባር የእራሱ አእምሮና አስተሳሰብ ውጤት ነው፡፡ እሾኅ መድኃኒቱ እሾኅ ነው፡፡ እግር የገባ እሾኅ እሾህ ነው የሚወጣው፡፡ ይህ ሲባል ግን የማህበረሰብና የግለሰቦች ተፅዕኖ የለበትም ማለት አይደለም፡፡››

‹‹
ሊሆን ይችላል…..እኔ ግን እድሜ ዘመኔ የገጠመኝ ሁሉ የሚነግረኝ ወንዶችን አውሬነት እንጂ መልካምነት አይደለም››…አለችኝ…..ፊቷ ላይ ንዴትና እልህ በግልፅ እየተነበበ፡፡

‹‹
ይቅርታ ማሪያና…….ተረጋጊና እናወራለን፡፡ ሰውነትሽ በጣም ሞቋል፡፡ እያላበሽ ነው፡፡ እመኝኝ…….ሁሉም ያልፋል፡፡……….ሻወር ግቢና ተረጋግተን እናወራለን›› አልኳት፡፡ 

‹‹
እሺ›› አለች ሳታቅማማ፡፡ ስብከቴ ደንብ አሳምኗታል ማለት ነው፡፡ ዚያም ተነስታ ወደ ሻወር ቤት ሄደች፡፡

‹‹
እስከዚያ የሚጠጣ ምን ልዘዝልሽ›› አልኳት፡፡

‹‹
ወይን›› አለችኝና የጡት ማስያዣዋን ፊት ለፊቴ አውልቃው ወደ መታጠቢያ ክፍሉ ገባች፡፡ ‹‹አሁን እኔን እንደ ሴት ጓደኛ ማየት ጀምራለች ማለት ነው›› አልኩ ልቤ፡፡ እሷን አልኩ እንጂ የእኔም የወንድነት ስሜት በኖ ጠፍቷል፡፡ ጭኖቼ መካከል ዘራፍ ብሎ የተነሳው መደዴም ወደ ነበረበት ቦታ ተመልሷል፡፡ ብዙ መሰናክል የነበረው ቢሆንም እቅዴ መስመር እየያዘ መሆኑ ደስ አለኝ፡፡ ታጥባ እስክትወጣ ድረስ አስተናጋጁ ወይኑን ከሁለት ብርጭቆ ጋር ይዞት ከተፍ አለ፡፡ 

ግን ጭንቅላቴ መልሶ በጥያቄ ተወጠረ፡፡ ‹‹ምን ቢደርስባት ይሆን ይች ልጅ እንደዚህ ወንዶችን አምርራ የጠላቻቸው?…..ማናት…….ምን ደርሶባት ይሆን?››….ታሪኳን የማወቅ ጉጉቴ በጣም እየጨመረ መጣ፡፡ ማሪያና ውስጧ ብሶት የተሞላ መሆኑን ሁኔታዋ ተረድቻለሁ፡፡ ነገር ግን የት ጀምሬ እንደምጠይቃት ግራ ገባኝ፡፡ 

ዚህ መሃል ማሪያና…‹‹ወንድሜ ወንድሜ…›› ብላ ተጣራች፡፡ ‹‹እህቴ እህቴ›› ብትል ይሻላት ነበር፡፡

‹‹
አቤት ማሪያና›› አልኳት፡፡

‹‹
እባክህ ፎጣውን አቀብለኝ›› አለችኝ፡፡

ደነገጥሁኝ!…..ለምን እንደሆን አላውቅም ልቤ ‹‹ድጭ ድጭ›› አለ……….ሌላ ፈተና!
.
.
.
ይቀጥላል!

No comments:

Post a Comment