Wednesday, September 13, 2017

ዘመን ሲታወስ-መስከረም 2፣ 1967 ዓ.ም

(ኢትዮጵያ ትቅደም ያለምንም ደም)

ወደ ኋላ 43 ድፍን ዓመታትን እንደ ንስር በረን መስከረም 2 1967 .ምን እናስባት፡፡ ይች ቀን ታሪካዊ ቀን ናት-ያለምንም ደም ስልጣን አፄው ወደ ወታደራዊው መንግስት የተላለፈባት ቀን፡፡ ጅምሩ ተራማጅ ኃይሉን እየመሩ ከፍተኛ ተቀባይነትን እያገኙ በመጡት በአልጋወራሽ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ፣ ኢትዮጵያ በአፄ ሚኒሊክ የተጀመሩ ዘርፈ ብዙ የስልጣኔ እርምጃዎችን መራመድ ጀመረች፡፡

ጣሊያን 40 ዓመት ቂሙን ቋጥሮ ሲመጣ፣ ኢትዮጵያውያን አድዋ ላይ የተጠቀሙትን ጦርና ጎራዴ ይዘው መጠበቃቸው ብዙ ዋጋ ቢያስከፍላቸውም፣ በአርበኞቹ ወኔና ቁርጥ ተጋድሎ የማታ ማታ ኢትዮጵያ ብቸኛዋ ቅኝ ግዛት ያልተገዛች አፍሪካዊ ሃገር ሆና በታሪክ ቋት ላይ በደማቁ እንድትሰፍር አድርጓታል፡፡ 5 ዓመታትን በፈጀው በዚህ እልህ አስጨራሽ ተጋድሎ ተፈሪ መኮነን (የኋላው ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ) ከዲፕሎማሲ እስከ ፊት ለፊት የጨበጣ ውጊያ ለሃገር ነፃነት ዋጋ ከፍለዋል፡፡ ንጉሱ በማይጨው ጦርነት ባደረጉት የፊት ለፊት ውጊያ ብዙ የክቡር ዘበኛ አባላት ከፊት ለፊት በጣሊያን ከኋላ ደግሞ በባንዳዎች በተከፈተባቸው ጦር ሰለባ ሲሆኑ ንጉሱ በታምር የመትረፋቸው ታሪክ ብዙ ጊዜ ተዳፍኖ ይታለፋል፡፡ አንፃሩ ንጉሱ ሀገር ጥለው የኮበለሉ ከዳተኛ ናቸው የሚለው ጎልቶ ይነበባል፡፡ ከዚያም አልፎ ንጉሱ ነጮች ብቻ በተሰበሰቡበት በዓለም መድረክ የሰውን ልጅ እኩልነት በድፍረት የተናገሩ፣ ለአፍሪካውያን ነፃነት የተሟገቱ ብቸኛው አፍሪካዊ መሪ ነበሩ፡፡

ምንም እንኳ በሀገር ውስጥ በነበራቸው አገዛዝ እራሳቸውን ስዩመ እግዚአብሔር አድርገው መቁጠራቸውና ህዝብን ጭሰኛና ባላባት ብለው መክፈላቸው የኋላ ኋላ አስኳላ ቀመስ በሆነው ተራማጅ ሃይል ተቃውሞ ቢያስነሳባቸውም፣ 3 ዓመታት የቆየውን የሃገራቸውን ሃያልነትና ልዕልና ግን በዓለም መድረክ ያስከበሩ ሰው ነበሩ፡፡

ያን ሁሉ ቀይ ቀለም የተፃፈ የኢትዮጵያን ውብና ማራኪ ታሪክ ግን 1966 1977 . የደረሰው ድርቅና ረሃብ የኢትዮጵያን ስም በዓለም መድረክ ላይ ተሰርዞ በጥቁር ቀለም እንዲፃፍ አደረገው፡፡ ዝቅ ማለት የማይወደው የኢትዮጵያ ልጅም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በሄደበት ሁሉ ራሱን ዝቅ አድሮጎና ተሸማቆ እንዲኖር ምክንያት ከሆኑት ታሪኮች ዋነኛው ሆኖ አብሮ ይኖራል፡፡ ብዙዎች የረሃብ ሰለባ ሲሆኑ አንፃሩ ንጉሱ ለልደታቸው ያደርጉት የነበረው ቸበርቻቻ፣ በተማረው ሃይል በኩል ታላቅ ተቃውሞ አስነሳ፡፡
ለሀገር ሉዓላዊነት መስዋትነት የከፈሉ ጀግኖች አርበኞች ወደ ጎን ተገፍተው፣ አድርባይ ባንዳዎች ለሹመት ሲታጩ፤ ይበሳ ብሎ ለስልጣናቸው ስጋት ናቸው ብለው ያሰቧቸውን ሰዎች በግዞትና በእስራት ሲያሰቃዩ፣የ ህዝብ ልብ ውስጥ የከበሩ እንደ በላይ ዘለቀ ያሉ ጀግኖችን በስቅላት ሲቀጡ፣ መሻሻል አለብን ብለው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ያደረጉትን እነ ጄኔራል መንግስቱ ንዋይን አይቀጡት ቅጣት ሲቀጡ፣ የወጣቱ ትኩስ ሃይል መሪ የነበሩትን እነ ዋለልኝ መኮነንን ከምድረ ገፅ ሲያጠፉዝግ በዝግ ከህዝብ ልብ እየወጡ፣ በወታደሩም ዘንድ ቅሬታው እየበረታ ሄደ፡፡

ይህን እውነትና ግፍ በብእራቸው ያስወነጭፉ የነበሩ እነ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ፣ አቤ ጉቤኛና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሰሚ ጆሮ አጡ፡፡ ‹‹ጊዜው ሲደርስ አምባ ይፈርስ›› አንዲሉ፣ ጊዜው ሲደርስ ፅዋው ሞላ፡፡ የጎጃም ገበሬዎችን አመፅ ተከትሎ በጭሰኛውና በባላባቱ መካከል ውጥረቱ እየጨመረ ሄደ፡፡ በታራማጅ ሃይሎች የሚመራው ‹‹ መሬት ላራሹ›› መፈክር በገበሬው የተጀመረው አብዮት ላይ በሳት ላይ ነዳጅ አንደማርከፍከፍ ሆነና ውጥረቱን የበለጠ አጠነከረው፡፡
መስከረም 1 1967 . አዲስ ዓመት በሰላም ተከበረ፡፡ አዲስ ዓመት ማግስት መስከረም 2 1967 . ግን የኢትዮጵያ ህዝብ በተመሳሳይ ዘውዳዊ ስርዓት አልቀጠለም፣ አዲስ ዜናና በአዲስ የተስፋ ብስራት በጥዋቱ በኢትዮጵያ ሰማይ የወጣችዋን ፀሐይ ተመለከተ፡፡

በዚህ ቀን የወታደሩ ከፍተኛ ሹማምንት በድብቅ ያዘጋጁትን ፅሁፍ ይዘው ንጉሱ ፊት ቀረቡ፡፡ በሻለቃ ደበላ ዲንሳ ተነበበላቸው፡፡ ንጉሱ አላንገራገሩም፡፡ አንድ ቃላ ብቻ ተናገሩ፣ እንዲህ ሲሉ፡
‹‹
ያላችሁትን በጥሞና አዳምጠናችኋል። ለአገር በጎ አስባችሁ ከተነሳችሁ የአገርን ጥቅም ከራስ ጥቅም ማስቀደም አይቻልም። እኛ እስከዛሬ አገራችንንና ሕዝባችንን አቅማችን በፈቀደውና በምንችለው ሁሉ አገልግለናል። አሀን ተራው የኛ ነው ካላችሁ ኢትዮጵያን ጠብቁ። የአገሪቱን ነገር ግን አስቡበት>> ብለው ወደ ተዘጋጀላቸው ማረፊያ ቦታ ተወሰዱ፡፡

ኢትዮጵያም ከዚች ቀን ጀምሮ ‹‹ኢትዮጵያ ትቅደም ያለምንም ደም›› በሚለው መሪ መፈክር በወታደራዊው መንግስት እዝ ስር መተዳደር ጀመረች፡፡ ሌላ የደም ታሪክ እኪመጣ ድረስ በዚች ታሪካዊ ቀን ስልጣን በሰላም ተሸጋገረ፡፡
---------------------
©
. (2010 .)

(Photo; #ETHIOPIANFACTS:Debela Dinsa reading the final the dethronement words to the Emperor.)

No comments:

Post a Comment