Tuesday, October 17, 2017

ይወለዳል ገና!

 ይሄ ወጣትነት
ከሱስ ላይ ተጥደን፥ ያልፋል እንደዘበት፤
ይሄ ወጣትነት
ያልፋል እንደ ዋዛ
ለሃብታም ስናረግድ፥ ለውሸት ስንገዛ
ይሄን ወጣትነት
የኔ ቢጤ ሁሉ፥ ይሰዋል በከንቱ
አሸሸገዳሜ፥ ለሚጠፋ አምሮቱ


ጀግናው ተሜ ግን፥ የሀገሬ እንቆቆ
ስለ መራራ እውነት፥ ጣፋጭ ዓለም ንቆ
ስለ ነፍሱ ህልው፥ በስጋው የሞተ
ሐር ፀጉሩን ነጭቶ፥ ፍትህ የሸበተ
በሀሰተኛ ዓለም፥ በእውነት የሰከረ
በአንዲት እስክርቢቶ፥ ሺዎች ያሸበረ
ኢትዮጵያዊ ባይሆን፥ ይቆጨኝ ነበረ!

ተሜ!
ግን ኢትዮጵያዊ ነህ፥ ያውም ትንታግ ጀግና
ትውልድ ከአብራክህ፥ ይወለዳል ገና
ይወለዳል ገና........
ይወለዳል ገና........
ይወለዳል ገና........
~~~~~~~~~~
©
. (2010
)

No comments:

Post a Comment