Wednesday, February 25, 2015

ጀግናው አርበኛ በላይ ዘለቀ (አባ ኮስትር) ክፍል -1



በላይ ዘለቀና ወንድሞቹ
ዘለቀ ላቀው (የበላይ ዘለቀ አባት) የልጅ እያሱ አንጋች ነበሩ ልጅ እያሱ ሲገለበጡ ዘለቀ ላቀው ወደሚስታቸው አገር ወደ ጫቀታ ሄደው ልጆቻቸውን ይዘው ወደአገራቸው ወደ ለምጨን (ቢቸና ወረዳ ) ተሻገሩ (ቢቸና ጎጃም ውስጥ ጫቀታ ወሎ ውስጥ ከአባይ ወንዝ ማዶ ለማዶ ናቸው ይገበያያሉም ይጋባሉም
1916 .. ማለት በላይ ዘለቀ 14 አመት ልጅ ሳለ ፊታውራሪ እምቢ አለ የተባለ የራስ ሀይሉ ሌባ አዳኝ (ጸጥታ አስከባሪ ) ዘለቀ ላቀውን ከበባቸው ዘለቀ ላቀው እጄን አልሰጥም ስላሉ ተኩስ ተከፈተ ዘለቀ ላቀውና አብረዋቸው የነበረ አለሙ መርሻ የተባሉ ወንድማቸው ከአስ ሰው በላይ ገድለው ብዙ ሰው አቆሰሉ «እኛ ልጆች ተኩስ ካባራ በህዋላ ተየጫካው ስንመለስ ሁለቱም ሞተዋል የዘለቀ ላቀው ሬሳ እበቱ በራፍ ላይ ተሰቅሎዋል » አሉ ፊታውራሪ ተሻለ አለሙ እንግዲህ በላይ ዘለቀና ተሻለ አለሙ እኩል አባቶቻቸውን አጡ አብረው የሀዘንን ጽዋ ቀመሱ እኩል በቀልን እያሰላሰሉ አደጉ በሁዋላም አብረው ጠላትን ተዋጉ

ዘለቀ ላቀው ሲሞቱ ልጆቻቸው ወደእናታቸው አገር ወደ ጫቀታ ተመለሱ በላይ ዘለቀ ያባቱን ደም ለመመለስ ተኩስ እየተማረ አደገ አደገና ያባቱን «ናስ ማሰር» (ባለ ነሐስ ማሰርያ ) ውጅግራ ጠመንጃ ይዞ ወደ አባቱ አገር ወደ ለምጨን (ቢቸና )ተሻገረ ። አባቶቻቸው የተገደሉባቸው ጎረምሶች ዳኝነት እንዳይሹ ዳኛው ራስ ሀይሉ ሆኑባቸው የቀራቸው ምርጫ በቀል ነው ። መሳርያ እየገዙ እየተዘጋጁ ለምጨን ቀንጦ ማርያም እያረሱ ቀን ይጠብቁ ጀመር ...እንዲህ ሲል ጥልያን መጣ ...
በሚያዝያ 28 ቀን (1928 ..) ለቀኛዝማች መሸሻ ጥልያን መሳርያ በአየር አወረደላቸው (ለጥልያን ገቡ ) ካለው ሰበካ ያዙ በረንታ ወረዳ (ቢቸና አውራጃ ) ደረሱ የዱሀ ከተማ ሰፍረው ህዝቡን መሳርያ እየነጠቁ (ጥልያንን እንዳይወጋ ) ጥልያን ደግ መንግስት ነውና እንገዛለን እያሉ ይሰብካሉ (እንዲሾማቸው ) «ልጅ በላይ ዘለቀ ግን እዋጋለሁ እንዋጋ እያለ እኛን ወንድሞቹን አነሳሳን» አሉ ፊታውራሪ ተሻለ አለሙ «ቀሰቀሰን ከሰላሳ እስከ ሀብሳ ለምንደርስ ያንድ አያት ልጆች ...የገልገል ቂልጡ ልጆች ...ታጥቀን ተነሳን ከቀኛዝማች በላይ መሸሻ ሰዎች መሳርያ እየነጠቅን በረሀ ገባን »
«ጦር ሲያሳድደን ...ስንሸሽ ...ቤት ሲያቃጥልብን ...ከሁዋላው ወይም ከጎኑ በድንገት እየመታነው መሳርያ ነጥቀን ስናመልጥ .....እንዲህ ስንል አንድ ቀን የማናልፈው ጉዳይ መጣ ግንባር መግጠም ግድ ሆነ ጠላት መሸሻ አሳጣና »«የዛሬን ጦር ማን ይምራውአለን ልጅ በላይ «አንተን መርጠናል ...እስከ መጨረሻው» አልነው "ሁላችሁም ወንድማማች ናችሁ " ፊታውራሪ ተሻለን "በላይ ዘለቀን እርስዎ እንኩዋን 4 አመት እበልጠዋለሁ ብለዋል እንግዲያው በምኑ ነው አለቃችሁ እንዲሆን የመረጣችሁት ?" "እንዴ ! በደግነቱ በጀግንነቱ ! ጠባየ መልካም በመሆኑ ! እኔ ይቅርብኝ ብሎ ለሌላው ስለሚያዝን !" (ያን ጊዜ 1928 .. ልጅ በላይ 3 ወልደዋል ልጅ ተሻለ ግን ገና በታህሳስ ነው ያገቡ )


ወይዘሮ ድንቅነሽ ሀይሉ (የራስ ሀይሉ ልጅ ) ጥልያን ሾመዋቸው የለም ጨጉ ጉልተ ገዥ ሆነው ሄዱ ህዝቡን መሳርያ አግባ ብለው አሰባሰቡ በላይ ዘለቀና ወንድሞቹ በድንገት ገብተው መሳርያዎቹን ነትቀው ሴትየዋን ሳይጎዱ ሳያጎሳቁሉ ወደመጡበት መልሰው ላኩዋቸው የነጠቁዋቸውን መሳርያ 35 ያህል ጠመንጃ ዋሻ ደበቁት ለራሳቸው በቂ መሳርያ ይዘዋላ ። ከዚህ በሁዋላ ደብረ ማርቆስን ጥልያን እየያዘ በላይ ዘለቀን ያሳድነው ጀመር '28 .. ሚያዝያ እስከ ግንቦት 29 ቀን ድረስ ሁኔታው ተመሳሳይና ተደጋጋሚ ነበር ጦር ይመጣል ...ያስሳል .....እነ በላይ ዘለቀ ይሸሻሉ ...በሁዋላ ቀስ ብለው መጥተው ጥቂቱን ገድለው መሳርያ ነጥቀው ....እልም ! መሳርያ በየዋሸው ያከማቻሉ ። እንደዚህ ብዙ አሰሳ ተሞከረ ባንዱ አሰሳ የበላይ ዘለቀ በትና የለምጨን ቤቶች በሙሉ ተቃጠሉ ከብቱም ተዘረፈ ጠላት ለምጨን 3 ጊዘ ነው ያቃጠለ
"
እስከ ታህሳስ 29 ቀን ድረስ አሰሳው የሚካሄደው በባንዳ ነበር " በታህሳስ 8 ቀን 1929 ግብጣን ደቡብ የተባለ ጥልያን ቢቸና ገባ ቢሉን ከዱማ ገስግሰን ቢቸና አደጋ ልንጥል ስንል ካህናት ጽላት ይዘው ስእል መስቀል ይዘው "አገሩንና ታቦቱን ያቃጥልብናልና አትውጉት እሱን እኛ ተመለስ እንለዋለን " ብለው መለሱን   ግብጣን ደበቡም በላይ ዘለቀ መጣብህ ቢሉት ወደማርቆስ ተመለሰ "

በየካቲት 29 ጥልያን አገሩን አስነስቶ ወረረን ከያውራጃው ግብጣን ደበቡ አስከተተ ጦር ሲመጣባቸው እነ በላይ ዘለቀ ሸሹ አጥቷቸው ሲመለሱ እያደፈጠ በጎን አደጋ እየጣሉ ብዙ መሳርያ ነጠቁት
"
የግንቦት እርገት ለት ..29 ነበር የዋለ ..ጥልያን ራሱ መጣ" የበላይ ዘለቀን ዘመዶች ከለምጨን እየደበደቡ ወደ አርበኞቹ እንዲመሩዋቸው አስገደዱዋቸው "ጦሩ ሲመጣ አሳለፍነው ከጎን አደጋ ጣልንበት በላይ ዘለቀ አንዱን ትሊንቲ ገደለው ኩረኔሉን አቆሰለው ብዙ ባንዳዎች ሞቱ " ታስሮ እየተደበደበ ሲመራ የነበረው አዛዥ ቢያዝን ዱብዳ የተባለው የበላይ ዘለቀ ዘመድም ቆሰለ ። በሰኔ 29 (1929) ጠላት በቅምቧት በደጀን በገበያ በሽበል በበረንታ የነበረውን "ደንበኛ " በሙሉ አከተተው (ደንበኛ የሚባለው "የመንግስት " የደንብ ብረት የያዘ ነፍጠኛ ነው ) ቀኛዝማች ስማ ነገዎ አዝማች ሆኖ ይህን ሁሉ አስከትቶ አባይ ወረደና አባራ ጂወርጂስ ሰፈረ ሀሳቡ እነ በላይ ዘለቀ ወደ ጫቀታ እንዳይሻገሩ በር በሩን ለመዝጋት ነበር "እንውጋው " አለ በላይ ዘለቀ "ጦሩ በጣም ብዙ ነው አንችለውም " አሉት ሌሎቹ "ግድ የለም ።ጦሩ በየመንደሩ ይመራል አዝማቹ ላይ አደጋ እንጣልበት "
እነ በላይ ዘለቀ ቀኛዝማች ለማ ነገዎ ያደረበትን በለሊት ከበቡት ሲነጋ ለማ ነገኦን ከነወንድሞቹ ደመሰሱት ጦሩ በሙሉ እጁን ሰጠ መሳሪያውንና በቅሎውን ሁሉ አስረከበ ድል አድራጊዎቹ መሳርያውን ዋሻ ውስጥ ደበቁት በቅሎዎቹን ወደ ጫቀታ ልከው በጥይት ለወጡዋቸው " ይሄ የሆነው ሰኔ 10 ነበር ሰኔ 12 በአውሮፕላን ይደበድቡን ጀመር በረንታ ጎይ ጂወርጂስ ላይ 12 ሰው ሞተብን እኛም ተመልሰን ወደ በረሀችን ሸሸን " ፊታውራሪ ለማ ሞገስ የጣልያን የጦር እንደራሴ ሆኖ ከማርቆስ ተልኮ ወጥቶ ዲማ አጠገብ ገድ ወንዝ ዋሻ ውስጥ እንዳለ ከበባቸው ወጥተው ገጠሙ ድል ነሱት ። ብዙ ሰው ሞተበት እሱ ግን አመለጠ ። በላይ ዘለቀ 60 ያህል ምንሽርና አልቤን ማረከ ምንሽርና አልቤን ሲያገኙ የመጀመርያ ጊዜያቸው ነበር እስካሁን ግን ሲዋጉ በናስማስር በውጅግራ በለበን ብቻ ነበር "ድፍን ሀምሌን ተከበብን ለምጨን አንድ ዋሻ ገብተን ተደበቅን ኤኛን ሲያጣን ጊዜ የጎይ ጂወርጂስና ያካባቢውን ህዝብ ጎይ ላይ ሰብስቦ በላይ ዘለቀን ካላመጣችሁ ብሎ በመትረየስ ፈጃቸው " በላይ ዘለቀ የቶክሱ እለት
ሞቶ ተቀብሯል ተብሎ ለጥልያኖች ተነገራቸው ሰው ሰደው መቃብሩን ቢያስመረምሩት ሴት ሆና ተገኘች
አንዱ አሳባቂ በላይ ዘለቀ ወደ እነብሰ አውራጃ ነው የሄደው ብሎ ለጥልያኖች ጠቆማቸው የጥልያን ጦር ወደ እነብሴ ዘመተ የእነብሴና የጎንቻ ህዝብ ገጠመውና ጨረሰው አንድ ጥልያን ብቻ አመለጠ
በላይ ዘለቀና አገሬው እስከ ነሀሴ 1929 ድረስ የበላይ ዘለቀ ተከታዮች 30 እንከ 50 የሚደርሱ ወንድሞቹ ብቻ ነበሩ "ነሀሴ ጂወርጂስ በላይ ዘለቀ በረንታ ላይ አዋጅ አስነገረ ኤኛን ምሰሉ እርዱን አለዚያ ግን ይህ የጦር ሜዳ ነውና እንዳትጎዱ ሂዱ ልቀቁ " "እናርጅ እናውጋ (የደብረወርቅ ወረዳ ) በረንታና ሸበል ጉበያ (ደጀን አጠገብ ) እነማይ (ቢቸና አውራጃ ) ...ይሄ ሁሉ አመነ ተባበረን "ከህዳር ማርያም (1930) እስከ መጋቢት ውድማትን አዋባልን ቅምብዋትን ሊበንን ባስን አነድድን ደጀንን ...እነዚህን ያዝን "
"
በየካቲት ትሊንቲ ከጫቀታ ዘመተብን አባይ ደረሰ አገድነው ብዙ ውጊያ ተደረገ 80 ብረት (ከነሰው )  ማረክን መለስነው ወደደጀን ተመለስን " "ከሸዋ ሲዘምትብን አባይ ላይ አገድነው ወር ካስራምስት ቀን ተዋጋነው 3 መኪናዎች ሰበርን ውስጣቸው የነበሩ ጥልያኖች ሞቱ "ጥልያን ሀይሉን አጠናክሮ በደጀን በኩል ከሸዋ መጣብን 12 በጦለኔ በጀኔራል ማሊን አዝማችነት መጣ

"
መጋቢት 19 ቀን (1930) ውጊያው ማለዳ የጀመረ በአስራአንድ ተኩል አበቃ መትረየስና መድፍ ከታች ፈረሰኛ በሻምላ (በጎራዴ ) " ተጨምሮበት ከላይ አሮብላ ወንድሞቻችን አለቁ የጦር አዝማች የነበረው የበላይ ዘለቀ ወንድም ደጃዝማች ታደለ ላወቅ ወደቀ ተሰማ ላቀው ቆስሎ አመለጠ 300 ያህል አለቅን የተቀረውን ጨለማ ገላገለን "ጠላት ፆን ማርቆስ ገባ ::እኛ ወደ በረሀችን ገባን ::" "ሚያዝያ 4 (1930) እበረሀችን አፋፍ ላይ እንደሰፈርን ጠላት ባራት ረድፍ ቢቸና ገባ ሚያዝያ 6 ጦሩን ባራት ማእዘን አቀነባብሮ በረሀችንን በሙሉ ከበበው በመካከሉ ደግሞ በግንባር እልፍ አእላፋት ጦር ይዞ ተሰለፈ " "ባለው ሀይላችን ገጠምነው " "ሊያፍነን ሞከረ በብዛቱ " "የቆላ ጫካ ነው ....እሳት ለቀቅንበት " "ይገርማል እኮ የቀን ነገር !ልፋሱ እሳቱን እያንቦገቦገ ወደነሱ ወሰደው ብዙዎቹን እሳት በላቸው ብዙዎቹ አመለጡ "የበላይ ዘለቀ ሚስት ወይዘሮ ሸክሚቱ አለማየሁ በመትረየስ ሞቱ (እንደወንድ ለብሰው ነበር ) ልጅ የሻሸወርቅ በላይ ተማረከች የናትየዋ እናትም ተማረከች "ከዚህ በሁዋላ አባይን ተሻግረን ጫቀታ ገባን ያጌ ከተማ ግዛው ሰብስቤ የተባለው የጥልያን እንደራሴ ገድለን አገሩን አቃትለን የጎበዝ አለቃ ሾመን ... ፊታውራሪንና ቀኛዝማች እያሱ ልጅ በላይ ሾመው ...ተመልሰን ወደ ለምጨን በረሀ ገባን " "ክረምቱን ከረምን " (ያን ጊዜ ወንዞች ስለሚሞሉ እነ በላይ ዘለቀም ያርሳሉ ጥልያንም በየካምቦው ይከርማል )

በህዳር 27 / 1931 ጥልያን የዴንሳ አማኑኤልን ክልክል ሸንበቆ ሊቆርጥ (ሰፈር ሊሰራበት ) ይመጣል ማለትን ሰማን አርበኞቹ ደፈጣ አድርገው መሽገው አደሩ ማለዳ ሲመጣ ገጠሙት "ብዙ ባንዳ ገደልን ብዙ መሳርያ ማረክን ጥልያን ግን አመለጠ " በሶስተኛው ቀኑ ለምጨን ወዳዳ በሚባል ቀበሌ ኮረነል አጎረኔ አውግስቶ የተባለ ጥልያን ሁለት መድፍ ጠምዶ ገጠማቸው ሰቀላ ገብሬልን አቃጠለ ከሁለቱም በኩል ብዙ ሰው አለቀ በዘጠኝ ሰአት ኮረነሉ ድል ሆኖ ወደ ካምቦ ተመለሰ
"
ይህ ሁሉ ሲሆን ለምጨን ውስት ፈላው በሚባል ቦታ ላይ ከትመን ከዚያ እየወጣን ነው ጦርነት የምናደርገው ፈላው ነበር ዋናው ምሽጋችን 30 እስከ 1933 . ድል ሆነን አናውቅም "

ሰኔ 1931 እነ በላይ ዘለቀ ወደ ማርቆስ ልንዘምት ነው ክተት ብለው አወጁ ጦሩ ከተተ መነሻቸውን ወደደብረ ማርቆስ አስመስለው ለሊት አባይን ተሻግረው ወደ ጫቃታ ገቡ ሲነጋ ደጋው ደርሰዋል
"
ሀይለ ሮባ የተባለ የጥልያን እንደራሴ ያገ ላይ ገጠመን ተሸንፎ ሸሸ አመለጠ ከተማውን አቃጠልን  ሽቅብ ወደ ወጊዲ አፋፍ ቀጠልን "በማግስቱ ወጊዲ ላይ ያለውን ካምፕ (ምሽግ ) በቦምብና በእሳት አቃጠልነው ያልተተኮሰበት አዳዲስ አልቤንና ምንሽር በጭነት ወሰድን የኛ ሰው እየገባ አራት አምስት ምንሽር አንግቶ አንዱን የደስ ደስ ወደ ላይ እየተኮሰ ወጣ " አገሩን ሹም ሽር አድርገነው ወደ ፈላው ተመለስን " ይህን ጊዜ ባንዳዎች የነበላይ ዘለቀ ይዞታ የሆነውን አገር መልሰው ለማሳመን ጥረት ያደርጉ ጀመር በድለንታ መጀመራቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ለበላይ ዘለቀ ከታማኞቹ ደረሰው እነ በላይ ዘለቀም በፍጥነት ሄደው ባንዳዎቹን ከድለንታ አስወጡዋቸው እስከ ደብረ ማርቆስ ድረስ አባረሩዋቸው እከተማው ዳር ቤቶች ተቃጠሉ " ! ሮማ ተቃጠለች ! አለ ጥልያን ሲዘብት እነ በላይ ዘለቀ ይዞታቸውን ከባንዳ ለማጽዳት አገሩን እያሰሱ ደብረ ወርቅ አካባቢ ደረሱ "
ሰኔ 1ቀን /፲፱፻፴፪ዓ/ በዚህን ጊዜ እንደአጋጣሚ - ጥልያን ከደብረ ወርቅ ብዙ ጉዋዝና መሳርያ (ስንቅና ትጥቅ ) ይዞ ወደ ቢቸና ይጉዋዛል እነ በላይ ዘለቀ ይህን አላወቁም ማለዳ እንደተነሱ ጅብ ሲያዩ ጊዜ ብዙዎች ተኮሱበት ። የተኩሱን እሩምታ ወደ ቢቸና የሚጉዋዘው ጥልያን ሰማውና ቃፊር ቢልክ - እነ በላይ ዘለቀ ናቸው አዙር እንወጋቸዋለን አለ ጦር ወደአርበኞቹ በኩል ሲሄድ የአዛዥ በቅሎ ሶስት ጊዜ ጣለችው አጠገቡ ያሉት ባንዳዎች "ምልኪው መጥፎ ነውና ዛሬ ጦርነት ባናደርግ ይሻላል" አሉት እሱ ግን በቅሎይቱን ገረፋት ለቅጣት ጥይት ጫነባትና በለላ በቅሎ ተቀመጠ አርበኞቹን አያልፋሽ እተባለ ተራራ ላይ ገጠማቸው
ውጊያው ሲጀመር አርበኞቹ ከላይ በኩል ጠላት ከታች በኩል ናቸው በላይ ዘለቀ አርበኞቹን "ጎበዝ ጥልያን ጥይቱን የሚያመጣው ከፋብሪካ ነው እኛ ግን ገዝተን ነው ስለዚህ ጥይት መለዋወጥ አያዋጣምና በጨበጣ እንግባበት "አላቸውና በመጀመርያ ዘሎ እየጮኸ ከጠላት መሀል ገባ ። ይህ የደብረወርቁ ጦርነት ለኛ የመጨረሻው ትልቅ ውጊያ ነበር ድል አደረግን ዘጠኝ የውሀ መትረየስ (ከባድ በከብት የሚጫን ቁጥር የለለው ቀላል መትረየስ ጥይትና ጠመንጃ ለማንሳት እስኪያቅተን እና አስራ ሁለት ባንዲራዎች ማረክን አስራ አንዱን ባንዲራ በላይ ዘለቀ በሁዋላ ለንጉሱ አስረከበ አንዱ ባንዲራ አሁን የጎላ ጂወርጂስ (ደብረቀርቅ አጠገብ ) ይገኛል
"የደብረ ወርቁ ጦርነት የተደረገው ሰኔ 1/1932 .. ነበር በበነጋው አስራ ሁለት አሮብላ መጥቶ የተዋጋንበትን አካባቢ ደበደበው እኛ ግን ያን ጊዜ ፈላው ምሽጋችን ገብተናል በላያችን አልፎዋል እኮ ታድያ በላይ ዘለቀ "ጂወርጂስ ያውቃል አይዟችሁ" አለን "እንዳትነቃነቁ !" ሰውም በቅሎም ባለበት ቀጥ ብሎ ቆመ አሮብላን በሙሉ አልፎን ሄደ ክረምቱን አርበኞቹ በምችጋቸው ከረሙ ታህሳስ 1933 አርበኖቹ የቢቸናውን ካምቦ (ምሽግ ) ለመክበብ ሲዘጋጁ ራስ ሀይሉ በላይ ዘለቀን መጥቼ ላነጋግርኽ ብለው ላኩበት " እሺ ግን ከጠላት ጋር የነበረ ባንዳ እንዳይከተልዎ ፎቶ አንሺም እንዳይመጣ " ብሎ ላከባቸው ሰቀላ ገብሬል ድረስ መጥተው አነጋገሩት ::  "ከተዋጋችሁ አገሩም ይጠፋል ትልያንም እኔን ላያምነኝ ነው ካልወጋኸው ግን እራሱ አገሩን ይለቃል " "እሺ ይሁን " "ጃንሆይም መጥተዋል "አሉት "እንግዲያው እሱንም አፍነን እናስቀረው እሱስ ይዞት የመጣው እንግሊዝ ያው ነጭ አይደለምን ?" አላቸው
"
አይሆንም "አሉት ። ተቀየመ ግን መውጋቱን ተወ "ነጭ እዚህ ግድም እንዳላይ" አላቸው ራስ ሀይሉን "እርስዎንም እንዳልደፍርዎት ቶሎ ይዘውልኝ ይውጡ " ሌሊቱን ተነስተው ሄዱ ጥልያንም ቢቸናን ለቆ ሄደ (ራስ ሀይሉ ደብረወርቅ ሲደርሱ ራስ ተመስገን ፈንታ ወግቶ ጉዋዛቸውን ብዙ ጠገራም አገኘ እሳቸው ግን አመለጡ )
ዋቢ ጽሁፍ
^ ፊታውራሪ ተሻለ አለሙ 74 አመት አዛውንት ናቸው ::"እኔና በላይ ዘለቀ የወንድማማች ልጆች ነን "አሉኝ ::"በእድሜ 4 አመት እበልጠዋለሁ ::"እንግዲህ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ይኼን ጊዜ 70 አመታቸው ነበር ማለት ነው :: ፊታውራሪ ተሰማ ላቀው 67 አመታቸው ነው ::"የበላይ ዘለቀ ያባቱ ትንሽ ወንድም ነኝ ::አሉኝ ::ፊታውራሪ ቀለመወርቅ መዝጊያ 62 አመታቸው ነው ::የደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዋና ጸሀፊ ነበሩ ::የሚከተለውን ታሪክ የነገሩኝ እነዚህ 3 አዛውንቶች ናቸው :: የካቲት 3 አመት ቁጥር 7 ሀምሌ 1972 ,ስብሀት /እግዚአብሄር

No comments:

Post a Comment