Sunday, November 4, 2012

ትምህርታችን ይጕረፍ


ትምህርታችን፡ይጕረፍ፥ቋንቋችን፡ይፍሰስ፤
ጐርፉ፣ማዕበሉ፡አፍሪቃን፡ያልብስ፤
ኤውሮፓንም፡ያርካ፥እስያን፡ያርስ፤
ወዳሜሪካንም፡ይጋልብ ይገስግስ
እኛንም፡ያጥምቀን፡እንደ፡ዮርዳኖስ፤
ቀድሞ፡የተጣፈው፡በጥቍር፡ክርታስ፡
መጽሐፈ፡ዕዳችን፡እንዲደመሰስ።
በስመ፡አብ፡ወወልድ፡ወመንፈስ፡ቅዱስ።
(አሐዱ፡አምላክ፤አሜን።)"
አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ-መዝገበ ፊደል።ገጽ፡32

No comments:

Post a Comment