Friday, March 20, 2015

ላልኖር እኖራለሁ

አንዴ በደስታ አንዴ በእንጉርጉሮ
ማታ በሳክስፎን ጥዋት በከበሮ
ሲጠፋ በቆሎ ሲገኝም በሽሮ
ደስ ሲለኝ በዘፈን ሲከፋኝ በሮሮ
አንዴ ተስፋ ሳጣ ሌላ ጊዜ ሳገኝ
ቀኖችን ስቆጥር ቀን ያልፋል እያልሁኝ፤
     ይሄ ብቻ አይደለም…..
በጋ ላይ ሲሞቀኝ ክረምት ላይ ሲበርደኝ
ቁልቁል ስበረታ ዳገት ላይ ሲደክመኝ
መባቻ ስጠግብ የገብርኤል ሲርበኝ
ማታ ላይ ስባንን ቀን እንቅልፍ ሲጥለኝ
ላልኖር እኖራለሁ ግዴታ ሁኖብኝ
የጫንቃዬ ሸክም ከእኔ እስኪርቅልኝ
              ጥር 2004 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ

No comments:

Post a Comment