Wednesday, August 12, 2015

ዘሬ ከወዴት ነው?

ተጠየቅ ፈጣሪ ዘሬ ከወዴት ነው?
ትውልድን እንደዚህ የከፈለው ማነው?
ብዬ አንድ ቀን ሌሊት ጌታየን ጠየቅሁኝ
ንዴቴን አብርዶ እንዲህ ሲል አስረዳኝ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እኔ በአምላክ ጥበብ አንድ አዳም ስፈጥር
ሰይጣን በጎን ገብቶ ከፈላችሁ በዘር
አለና በሀዘን ትርጉሙን ነገረኝ
ዳግም ሁለተኛ ጥያቄ  ጠየቅሁኝ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
በነጭና ጥቁር ያቀለመን ማነው?
የቆዳ ልዩነት መሰረቱስ የት ነው?
አልሁና እግዜሩን በፍራት ብጠይቀው
የራሴን ጥያቄ ወደኔ መለሰው፡፡
መሬትን ከሞላው ከዓለም ህዝብ መሃል?
አንድ ፍጥረት አለ አንተን የሚመስል?
ይሄ ነው ትርጉሙ የቀለሙ ዝርዝር
ሀሌ ብለህ አድንቅ የስላሴን ምስጢር፤
አለና በቁጣ መልሱን መልሶልኝ
በእኩለ ሌሊት ሚስጢሩን አካፍሎኝ
እንዳመሰግነው ጊዜ እንኳ ሳይሰጠኝ
ከእንቅልፌ ስነቃ ከፊቴ ጠፋብኝ
"""""""""""""""""""""""""""""""""""""
      ሐምሌ 05 2007 .

No comments:

Post a Comment