Monday, April 24, 2017

ያዳኑሽ_የት_አሉ???

ቤተስኪያን ታዛ~ ካቡ ስር ቆሜ
እግዜሩ አስተብርኮ~ አንቺም ተሳልሜ
ስምሽን እጠራለሁ~ ዜማ ውዳሴ
ደም ስጋሽ ጋር~ተቆራኝታ ነፍሴ፤

እንደምን ዝም ልበል~እንዴት ብዬ ልሽሽ
ሰርክ ያባክነኛል፣ እናቴ ጡጦች ጋር~የጠባሁት ስምሽ
ግን ውዴ፡~
ገንቦሽ ሳልጠጣ~ ቅቤሽ ሳልወዛ
ምስለኔ ጅራፍ~ወገቤ ተይዛ
እንደ ሲኦል ግዞት~ነፍሴ ተገንዛ
ለምን ነው ዘወትር~ ስምሽ ምገዛ???
ይኸውልሽ ውዴ፡
ውበትሽ ጠቅሰው
ታሪክሽ ነቅሰው
ስለ ስምሽ ክብር~እልፎች ሲናገሩ
አርያም ዜማ~ሁሉም ሲዘምሩ
ሰገነት ግርማሽ~ሲታየኝ ስዕሉ
ገደሉሽ እንጂ~ያዳኑሽ የት አሉ???
........................................


((ዘላለም ጥላሁን-ሸገር-ኢትዮጵያ))
( አንቺ……© 2009 .ም)

No comments:

Post a Comment