Wednesday, July 19, 2017

የ ሲኦል ነፍሳት: ክፍል ፫

ማሪያና ትንሽ ሞቅ ብሏታል፡፡ ከለበሰችው ታኮ ጫማ ጋር ተዳምሮ ‹‹ደርደርደርደር›› ትላለች፡፡ ጠጋ ብዬ እጄ ጨበጥኋት፡፡ እጇ ያቃጥላል፡፡ አስፓልቱን ዳር ይዘን ባጃጅ መጠበቅ ጀመርን፡፡
ዝምታችንን ለመስበርይቅርታ ቅድም አስቀየምሁሽ አይደል አልኳት፡፡
‹‹ችግር የለም አንተ አልፈርድም፣ አልፏል እርሳው›› አለችኝ….ዝቅ ብላ መሬት መሬት እያየች፡፡
ማሪያና ወደ የት እንደምንሄድ እንኳን አልጠየቀችኝም፡፡ የምወስዳት ወደ ገነት እንዳልሆነ ልቧ ቢያውቅም፣ ሲኦል ወደ ባሰ ገሃነም ይሆን ብላ እንኳ አትጠይቅም….‹‹የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም›› ብላ ይሆን? አላውም ምን እያሰበች እንደሆነ ማወቅ ይከብዳል፡፡ 
ያለ ምንም ማጋነን መንገድ ብርሃኖች ፀዳል ሲያርፋባት ማሪያና እጅግ ውብ መሆኗ ቁልጭ ብሎ ይታያል፡፡
‹‹
የት ናችሁ››….የባጃጅ ሹፌር ነበር፡፡
‹‹
ኤክስኩቲቭ….›› አልሁትና ስንት ታደርሰናለህ ብዬ ጠየቅሁት
‹‹
የታወቀ ነው…200 ብር››
‹‹
እንዴ ወንድሜእኛን ለማድረስ ነውወይስ ተጨማሪ አገልግሎት አለው›› አልት ኮስተር ብዬ፡፡
‹‹
ቪአይፒ ነው….. ሰከሩ ደግፈን ወደ ሆቴላቸው እናስገባለን፡፡ ሁለት ደጋፊዎች አሉኝ፡፡ ልጥራቸው፡፡›› አለኝ፡፡ አነጋገሩ የቀልድ አይመስልም፡፡
‹‹
ወንድሜእኛ አልሰከርንም…..50 ብር ትወስደናለህ…..›› አልኩት፡፡
ትንሽ ካንገራገረ በኋላ 50 ብር ወደ ሆቴላችን ወሰደን፡፡
( ነገራችን ላይ አዳማ መሸ የባጃጅ ትራንስፖርት ዋጋ ብዙ እጥፍ እንደሚጨምር ባውቅም፣ ቀድሜ ካልተደራደርሁ እነሱ ያሉትን እንደሚቀፍሉኝ ቀደመ ስህተቴ ትምህርት ወስጃለሁ፡፡ ደጋፊዎቹ ስራም፣ ምን አልባት ብቻህን ሆንህ ወደ ሆቴል ሳይሆን ወደ ጫካ ማድረስ ሊሆን ይችላል፡፡ እርግጥ እኒህ ችግሮች አሁን አሁን ተሻሽለዋል፡፡)
ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስ! ወደ ማረፊያ ክፍሌ ከመግባታችን በፊት ‹‹…እራት በልተሻል ማሪያና›› ስል ጠየቅኋት…..
‹‹
›› አለችኝ አንጀትን በሚያባባ ቃና!
ከሆቴሉ ፊት ለፊት ወዳለ ሬስቶራንት ወስጄ እዘዥ አልኳት፡፡
ጥብስ ፍርፍር አዘዘች፡፡
ለምን እንደሆን አላውቅም ብዙ ጊዜ ሴቶች ጥብስ ፍርፍር ይወዳሉ፡፡ ብሶታቸውን በርበሬው እንዲያቃጥልላቸው ይሆን? (ሃሃሃሃሃሃ---- ሞኝ ትንተና……ሆድ የገባ ነገር እንዴት አእምሮን ብሶት ያስታግሳል)……ግምታዊ እንጂ ተጨባጭ መላምት መስጠት ስለማልችል ልለፈው፡፡
‹‹
ብላ እንጂ›› አለችኝ፡፡
አይ እኔ በልቻለሁ አልኳት፡፡
አበላሏ እህል ቀምሳ የምታውቅ አይመስልም፡፡ አልተገረምሁም፣ አሳዘነችኝ፡፡ በግድ ሁለት ጊዜ አጎረሰች……ጉርሻዋ ልክ እንደ እናት እጂ ይጣፍታል፡፡ ጨምሪኝ ልላት ነበር ግን በልቻለሁ ስላልሁ ይሉኝታ ቢጤ ያዘኝ፣ አንድ በኩልም እራቷን መጋፋት መስሎ ተሰማኝ፡፡
‹‹
ማሪያና›› አልኳት፡፡ አሁን አሁን ስሟን ደጋግሜ ስጠራው ደስ የሚል ስሜት ይሰማኝ ጅምሯል፡፡
‹‹
አቤት›› አለች፡፡
‹‹
ምግብ ሳትበይ ነው ቢራ የጠጣሽው›› አልኳት፡፡
‹‹
አዎ››
‹‹
ለምን ? ›› …..ቃሉ አፌ አምልጦኝ ከወጣ በኋላ ቆረቆረኝ፡፡ ሁሌም ‹‹ለምን›› ብሎ መጠየቅ ቀላል ነው፡፡ መልስ መስጠት ግን ይከብዳል……በዚሁ አንድ ወቅት የፃፍሁት ግጥም ትዝ አለኝ፡፡
‹‹ ለምን? ለምን?
የአንድ ቃል ሰመመን
ፊደሎች መክፋት
ደግሞ ከኋላው ላይ ጥያቄ ምልክት?
የአንድምታው ግዝፈት
እንደ ክፉ ደዌ አንጀት የሚጎትት
ለምን? ለምን?
ለምን? መጠየቅ አፍ ላይ ቢቀልም
ለምን? ስትባል ግን ምላሽ አታገኝም..… ›› እያለ ሚቀጥል ግጥም ነው፡፡
ማሪያና ግን መለሰችልኝ..
‹‹…
ጠዋት 4 ሰዓት አካባቢ ትንሽ ነገር ቀምሻለሁ….ትናንት ገባያ ጠርሮብኝ ነበር›› አለችኝ በተሰላቼ ድምፅ፡፡
አዝናለሁ አላልኋትም፡፡ ይህን ለማለት…….በወሲብ ንግዱ የሚደርስባትን ጉዳትና ርሃብ የሚደርስባትን ጉዳት የሚያመዛዝን ጭንቅላት ያስፈልጋል፡፡ እኔ ለጊዜው አእምሮዬ ይህን ማመዛዘን አይችልም፡፡ ሁሉም አእምሮዬ ክፍል በሌላ ሃሳቦች ተወጥሯል፡፡
ሂሳብ ስከፍልካልከፈልኩ ብላ አንገራገረች፡፡ በለጠ አዘንኩላት፣ አከበርኳትም፡፡ በዚህ ህይወትም ውስጥ ሁና ባህሏንና ወጓን ማክበሯ ገረመኝ፡፡ ችግር የለም ብዬ እኔ ከፈልኩና ወደ ማረፊያ ክፍላችን መጓዝ ጀምርን (አሁን እሷም ጊዜያዊ ማረፊያ ክፍል ነው)፡፡
‹‹አመሰግናለሁ›› አለችኝ የሆነ መግለፅ በማልችለው በሚያሳዝን ድምፅ፡፡
‹‹ለምኑ?›› አልኳት ( እንድታወራ ፈልጌ እንጂ ሳይገባኝ ቀርቶ አይደለም፡፡ ሀበሻ ሊያስለፈልፍህ ሲፈልግ ለምን፣ እንዴት፣ ከዚያስ፣ ከዚያ ቀጥሎስ……እያለ ደንቃራ ቃላትን ከወሬው መካከል ይዶላል፡፡)
‹‹ማንም እራት በልተሻል ብሎ ጠይቆኝ አያውቅም………እንኳንስ ሊጋብዘኝ›› አለችኝ፡፡
‹‹ምንም አይደል ማሪያና….እህቴ አይደለሽ››…….አልኳትና ከፊት ለፊት ቀድሜ የማረፊያ ክፍሉን ቁልፍ እንግዳ መቀበያ ክፍል ተቀብዬ ወደ ማረፊያ ክፍሉ አቀናን---3 ፎቅ-አልጋ ቁጥር 304፡፡
ግቢ ማሪያና›› እልኳት ቀድሜ ገብቼ፡፡
‹‹ እሺ…›› አለችና የመታረጃዋና ቦታ ጎሪጥ እያየች ፊት ለፊት ካገኘችው ወንበር ላይ ቁጭ አለች፡፡
መስኮቱን ከፍቼ አሻግሬ ወደ አስፓልቱ እየተመለከትሁ…..‹‹ሻወር መውሰድ ትፈልጊያለሽ›› አልኳት፡፡
‹‹አመሰግናለሁ…..ወስጄ ነው ወደ ስራ የገባሁት›› አለች፡፡
‹‹ስራ›› የምትለዋ ቃል ጭንቅላቴ ውስጥ ተንጠልጥላ ቀረች፡፡ ስራ ምንድን ነው?….ብር ያስገኘ ሁሉ ስራ ነው?……የስራ መመዘኛው ምንድን ነው? ….ለራሴ ጥያቄ ማዥጎድጎድ ጀመርሁ፡፡ እሷን ግን ዳግም የማይሆን ጥያቄ ጠይቄ ልጎዳት አልፈልግም፡፡
‹‹ምን እያሰብህ ነው›› አለችኝ፡፡
‹‹ምንም›› አልኳት፡፡
ወደ እሷ ዞር ስል….. ብርሃን መላክ መስላ አልጋው ዳር ቆማለች፡፡ (ውበቷን ለመግለፅ ያክል እንጂ መላክ በዚህ ሰዓት እዚህ ቦታ ምን ይሰራል)፡፡ አንዳች መገለፅ የማይቻል ልዩ ስሜት ሰውነቴን እግር ጥፍሬ እስከ እራስ ጠጉሬ እንደ ኤሌክትሪክ ሞገድ ሲነዝረኝ ተሰማኝ፡፡ ሳላውቀው ወደ እሷ እየተጓዝሁ ነው፡፡ የሆነ ኋይል ከኋላ ሁኖ ይገፋኛል፡፡ ሂድ ሂድ…..ይለኛል፡፡ ማን እንደሆነ ግን አላውቅም፡፡ ከፊል መቃብር ውስጥ የገቡት ጡቶቿ እንደ ተጠመደ መድፍ ወደ እኔ አፍጥጠዋል፡፡ ከንፈሯ እሳት መስሏል፡፡ ብቻ ….አሁን ያን ሁሉ ውበቷን መግለፅ ጊዜ የለኝም፡፡
ደንግጬ ይሁን ፈርቼ አልጋው ዳር ደርሼ ቀጥ አልሁኝ፡፡ እኔ ባለሁበት ስቆም ምትኩ እሷ ወደ እኔ መምጣት ጀመረች…. መሃከላችን ያለው እርቀት ቅጡ አንድ ክንድ እንኳን አይሆንም….ምንም ነገር ማሰብ አቁሜአለሁ፡፡ በጣም እየሞቀኝ ነው ግን ደግሞ ይበርደኛል፡፡ መላ ሰውነቴ እሳት መትፋት ጀምሯል….
;
ይቀጥላል!
(
በሉ ወደ ስራችሁ ተመለሱ……እና አብራችሁ ልትቀጥሉ ነው?)


No comments:

Post a Comment