Wednesday, July 4, 2018

ሻምበል አስረስ ገላነህ ብዙነህ [ጎጃሜው]

                                          (የግፍ ጥግ የተፈፀመበት የጦር መኮንን)
ለመጀመሪያ ጊዜ በአማራ ህዝብ ላይ እየተሰራ ያለውን አሻጥር ፊት ለፊት የተጋፈጠ የጦር መኮንን ይህ ሰው ይመስለኛል፡፡ ‹‹ሳሞራ››ን ፊት ለፊት የተጋፈጠ፣ ባህርዳር በተደረገው ስብሰባ ከእነ በረከት እና ህላዌ ጋር ‹‹በአማራ ስም አትነግዱ›› ብሎ ፊት ለፊት የተፋጠጠ የመጀመሪያው ሰው ይህ ይመስለኛል፡፡ በዚህም ድርጊቱ ‹‹ ጎጃሜው›› የሚል ቅፅል ስም እንደተሰጠው ባለታሪኩ ይገልጻል፡፡ በዝሆኖች ጥርስ የተነከሰበት ይህ ቆፍጣና የጦር መኮንን የማታ ማታ ‹‹ የአልጋ ቁራኛ›› የሚያደርገው ግፍ፣ እላዩ ላይ ነዳጅ አርከፍክፎ ፓርላማ ፊት ለፊት እራሱን እንዲያቃጥል ያስወሰነው መከራ ተፈፀመበት፡፡  ይህ ሰው ‹‹የካድሬው ማስታወሻ›› የተሰኘ ግለ ታሪክ 2005 ዓ.ም አካባቢ ለንባብ አብቅቷል፡፡ መፅሃፍ አንብቤ ያለቀስኩበትን፣ ከመጠን በላይ ልቤ የተነካበትን ጊዜ አላስታውስም፡፡ የዚህን ጀግና ግለታሪክ ሳነብ ግን አልቅሻለሁ፡፡ በማልቀስ ብቻ አላለፈም፣ ከውስጥ የሆነ ተስፋ ሲሰበር ይታወቀኝ ነበር፡፡ የጭካኔን ጥግ ያየሁበት ትርክት ስለሆነ!

ታሪኩን በወፍ በረር እንመልከት፡፡ በደርግ ዘመን የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት አባል ነበር፡፡ የሻንበልነት ማዕረግ የደረሰው ይህ ሰው በአቋሙ ምክንያት ከመንጌ በትርም ሸሽቶ እንደተረፈ ይናገራል፡፡ ኢህዲግ ስልጣን ሲይዝ ከተሸኙት ውስጥ አንዱ ነው፡፡ እንደገና ወደ ጦር ሰራዊት በመመለስ ከተራ ወታደርነት ተነስቶ የሻንበልነት ማዕረግ ደረሰ፡፡ ከዝሆኖች ጋር በፈጠረው መላተም የተነሳ ጥርስ የተነከሰበት ጎጃሜው፣ የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት የሎጂስቲክስ አስተባባሪ ሆኖ ወደ ባድመ ተላከ፡፡ ከታቀደለት ድርጊት ቀድሞ፣ በሻቢያ ጦር ቆስሎ ሆስፒታል ገባ፡፡ ከዚያ በኋላ የሆነውን ፈረንጆቹ <<from the horse mouth>> እንዲሉ በአንደበቱ ግለታሪኩ ላይ ያሰፈረው እውነት ይህን ይመስላል፡፡ ሁለት ደቂቃ ሰውታችሁ አንብቡት!
 ‹‹በጠቅላላው የኢህአዴግ የመከላከያ ሠራዊት ቤት ጥቅምና የተሟላ ኑሮ ወደ አንድ ወገን እያደላ ሲሄድ በጣም አዝን ነበር። እኔ መፍትሄ አመጣ ይመስል አላስችል እያለኝ ፊት ለፊት ከማይነቃነቅ ድንጋይ ጋር በተደጋጋሚ ተጋጭቻለሁ። ለእውነት መቆሜ ብዙ አስከፍሎኛል። ይሄው ባህሪዬ በመንግስቱ ኃይለማርያም መዳፍ ውስጥ ሊያስጨፈልቀኝ ነበር። ደግነቱ ቀድሜ ሸሽቻለሁ። ምን ያደርጋል፣ እድሜ ልኩን በቁም መግደል ከሚችልበት የህወሓት/ኢህአዴግ መዳፍ ውስጥ ወድቄያለሁ። ከአፋር ወደ ሽራሮና ወደ ሌሎች ግምባሮች በመጓዝ ብዙ ውጤታማ ስራዎችን ሰርቻለሁ። 1992 ዓም ከሻዕቢያ በተተኮሰ የከባድ መሳርያ ፍንጣሪ ቆሰልኩ። አብረውኝ የሚሰሩት አብዛኛዎቹ ሲቪሎች ስለነበሩ ደንግጠው ይመስለኛል፣ በወቅቱ እርዳታ አላደረጉልኝም። ደሜ ፈሶ አልቆ መናገር አልችልም ነበር። ራሴን ስቼ ነበር በፊልድ ሐኪሞች የተነሳሁት። ሐኪሞች አንስተው ወስደው ፊልድ ሆስፒታል ድንኳን ውስጥ አስተኙኝ። ጨካኝ ካድሬዎች ቆስዬ ሆስፒታል ተኝቼ ሳለ፣ በተፈጠረ አጋጣሚ በየጊዜው እየተሟገተች የተዳፈረቻቸውን ምላሴን ፀጥ ለማድረግ፣ በበሽታ እንድመረዝ አደረጉ። ዘመኑ እጅግ በተራቀቀበት ወቅት አንድ በኤች አይ ታሞ አጠገቤ ከተኛ የአስር አለቃ (የአድዋ ልጅ ነው) የደህንነት ሰራተኛ የተወጋበትን መርፌ እንስት ሀኪም ተብየዋ ረዳት ተጋደልቲ ወጋችኝ። በወቅቱ መንቀሳቀስ አልችልምና እዚያው በተኛሁበትእሪብዬ ጮህኩ። ወዲያውኑ የዋርዱ ኃላፊ ዶክተር ሳምሶን የሚባል ሲቪል ወጣት መጥቶምን ሆንክ?” ብሎ ሲጠይቀኝ፣እንዴት በሌላ ሰው መርፌ ትወጋኛለች? መርፌ ደግሞ እየቀቀሉ መጠቀም እንኳ ድሮ ቀርቷል……” እያልኩ ጮህኩ።
ይች ተጋደልቲ ሐኪም በድንገት የተሳሳተች ለመምሰል ከወዲያ ወዲህ ትሯሯጣለች አንባቢያን ሊረዳልኝ የምፈልገው በመጀመሪያ እኔ መኮንን ነኝ። አጠገቤ የተኛው ደግሞ አስር አለቃ ነው። በወታደራዊ ህግ በኩል አስር አለቃው መኮንኖች ዋርድ የመተኛት መብት የለውም። ሆን ተብሎ በእቅድ የተሰራ ነበር።
ዶክተር እንዴት እንዲህ ይደረጋል?” ብየ አለቀስኩበት። ዶክተሩ የታዘዘውን መስራት እንጅ ምንም ሥልጣን እንደሌለው እናውቃለን። በተራ ተጋዳልቲ እየታዘዘ ነው የሚሰራው። እናም የተወጋሁትን ታፋዬን በአልኮል እያጠበአይዞህ ምንም አይደል!” እያለ ሊያፅናናኝ ሞከረ። በጣም ማዘኑ ከፊቱ ያስታውቃል። ከዶክተሩ ጋር የምትሰራዋ ሌላኛዋ ሲቪል ነርስም በጣም እያዘነች ነበር። እራሷን እያረጋጋችለማንኛውም ከወር በኋላ ቸክ አድርግ!”አለችኝ። ይህች ነርስ ዛሬም በህይወት አለች። ዶክተሩን ግን ከዚያች ጊዜ በኋላ አላየሁትም። የት እንዳለም አላውቅም።
አጠገቤ ተኝቶ የነበረው አስር አለቃ ደህንነት አይኔ እያየ አጠገቤ ሞተ። ከዚህ በኋላማ ለደቂቃም አእምሮዬ ሊያርፍ አልቻለም። ውስጤ በፍርሃት እየራደ አለቀ። ነርሷ እንደመከረችኝ በወሩ ስመረመርያጠራጥራልተባለ። ቁስሌ ሲያገግም ከትግራይ ወደ አዲስ አበባ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል ተላኩ። በሁለተኛው ወር አዲስ አበባ ስመረመርፖዘቲቭመሆኔ ተነገረኝ። ይህ ውጤት ሲነገረኝ አራት ቀን ምግብ አልበላሁም። እንቅልፍ የሚባል በአይኔ አልዞር አለ። ኒሞኒያው፣ቲቪው፣ አልማዝ ባለጭራው፣ ጉንፋኑምኑን ልንገራችሁ? በሽታ ሁሉ እንደ ንብ መንጋ የሰፈረብኝ መሰለኝ። ከሆስፒታል ወጥቼ ቤቴን ትቼ ጃንሜዳ ሜዳው ላይ 3 ቀን ዋልኩ። አደርኩ። 3ኛው ቀን ቤተሰብ ፈልጎ አገኘኝና በስንት ልመና ወደ ቤቴ ገባሁ።
ከመስርያ ቤት የስራ ስንብት ጠየኩ። ማመልከቻዬ ታይቶ ሳይፈቀድልኝ ቀረ። ያልተፈቀደልኝ ደግሞ ለኔ ታስቦ ወይም ስለምጠቅማቸው አይደለም። ከእነሱ ስላልመጣ ነው። እናም በህክምና ምክንያት ብዙ ጉዳት ደረሶብኝ ይኸው ከሞትኩ ቆየሁ።››

በዚህ አላበቃም፡፡  ጎጃሜው ከጦርነቱ በኋላ ‹‹በክብር›› ተብሎ ከተሰናበቱት ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ከተባረረ በኋላ በኤች.አይ.ቪ ላይ የሚያተኩር ግብረ ሰናይ ደርጅት መሰረተ፡፡ ድርጅቱም በጠራራ ፀሐይ በግለሰቦች ተወረሰ፡፡ ከዚህ በኋላ ነው ነዳጅ አርከፍክፎ እራሱን ለማቃጠል ያስጨከነውን ውሳኔ  የወሰነው፡፡ ሆኖም ግን በተኣምር ተርፎ ግለታሪኩን ለመፃፍ በቅቷል፡፡ አሁን በህይወት ይኑር አይኑር አላውቅም፡፡ ይህን የምፅፈው ቂምን ለማውሳት ሳይሆን ‹‹ በአማራ ስም በየጥሻው እየተደራጁ ያሉ ሰዎች ይህን ጀግና የማሰብ፣ በህይወት ካለም የማገዝ የሞራል ግዴታ እንዳለባቸው ለመጠቆም ነው፡፡››



No comments:

Post a Comment