Saturday, August 11, 2018

የልጅነት ትዝታ


ይችን ልጅ ሳይ ልጅነቴ ትዝ አለኝ፡፡ ከልጅነቴ ውስጥ ደግሞ የአራተኛ ክፍል የሳይንስ መምህር ትዝ አሉኝ፡፡ አንድ ቀን የሳይንስ መምህር አዳፋ ካቦርታቸውን እና እንደ ምድር ወገብ መሃል ለመሃል የተሰነጠቀች ባርኔጣቸውን ለብሰው ወደ ክፍል ገቡ፡፡
እንደምን አደራችሁ ልጆች
ሁላችንም ተነስተንእንደምን አደሩ መምህር
ቁጭ በሉ
እሺብለን ቁጭ!
ምን አለበትእንደምን አደሩስንላቸውእግዚሃር ይመስገንወይምደህና ነኝቢሉን!...አላሉንም..... ቀጥታ ገጣባ አህያ ወደ ሚመስለው ብላክ ቦርድ ሄደውሳይንስብለው ጻፉ፡፡ ቀጥለውም የሰሌዳው ጠርዝ አካባቢ በዲያጎናል አስምረው ቀን ፃፉ፡፡ 
አሁን ሳስበው የሚገርመኝ አንድ ነገር አለ፡፡ አንድ መምህር የፃፈውን ቀን፣ ቀጥሎ ያለው መምህር ሲገባ አጥፍቶ እንደገና ይፅፈዋል፡፡ ሁሉም በራሱ ቀን ያምናል፡፡ ቢያምርም ባያምርም የራሱን ይፅፋል፡፡ አንድ በሆነ ሰለዴ፣ አንድ አይነት በሆነ ቀን ሁሉም በራሱ ቀን ይመካል፡፡ ሀገሬም ላይ የኖረው ሃቅ ይህ ነው፡፡ ወደ ቀደመ ነገራችን ስንመለስ መምህሩ ወደ ተማሪዎች ዞሩና የእለቱን ክፍለጊዜ አስተዋወቁ፡፡ 
;
ተማሪዎች ዛሬ ስለባለ አንድ ክክ እና ሁለት ክክ ዘር ስላላቸው አዝርዕቶች እንማራለንአሉና ኮፍያቸውን ከፍ እያደረጉአስኪ ከመካከላችሁ እጁን አውጥቶ ባለ ሁለት ክክ የሚያፈሩ አዝርዕቶችን የሚነግረኝ ተማሪ አለሲሉ ጠየቁ፡
#ተማሪ ጋሸ እኔ፣ ጋሸ እኔ
#መምህር እሺ አንተ ፊትህን ያልታጠብኸው፡፡....ግን አለመታጠብ ይነሰን፡፡በውሃ ላይ ቁማ ውሃ በተጠማች ሀገርጥፋቱ የማነው፡፡ ነገሩ ብንታጠብም መንገዱ አቧራ ስለሆነ /ቤት ስንደርስ ከአፈሩ ጋር እንመሳሰላለን፡፡ ግን በቆሸሸ ሰውነታችን ውስጥ ንፁህ ልብ፣ ደስ የሚል ፈገግታ፣ ተስፋ እና ፍቅር ነበር!
#ተማሪው #አተር ብሎ ሊናገር የነበረው ተማሪ ፊቱን ባለመታጠቡ ተሸማቆ #በቆሎ ብሎ መለሰ፡፡
#መምህር፡ አልመለስህም፡፡
መምህሩ ለሌሎች እድል መስጠት አልፈለጉም፡፡ ብዙ ተማሮችም ተሸማቀው እጃቸውን መሰብሰብ ጀመሩ፡፡ የተወሰኑት ንፍጣቸውን በሹራባቸው እየጠረጉ ጋሸ እኔ፣ ጋሸ እኔ…….ማለት ጀመሩ፡፡
#መምህር፡ፀጥታ ልጆች ይህ በቀላሉ አይመለስም፡፡ ሁላችሁም ነገ የባቄላ፣ የስንዴ፣ የገብስ፣ የአተር፣ የሽንብራና የበቆሎ እሸት ይዛችሁ ኑ፡፡ ያገኛችሁትን አምጡ፡፡ በደንብ ያመጣ አስሩ አስር ያገኛል፡፡ብለው አሰናበቱ፡፡
ተማሪዎች እንደተባሉት ወንዶች በፎጣቸው፣ ሴቶች በፀጉር መሸፈኛቸው የቻሉትንና ያገኙትን ይዘው መጡ፡፡
#መምህር፡ አመጣችሁ ልጆች፡፡ ጎበዞች፡፡ ይህ ባለ አንድ ነው፣ ይህ ደግሞ ባለሁት ነው፣ አሉ ሁለት በቆሎና ባቄላ ከአንዱ ልጅ ተቀብለው በጠፍራቸው ፈርቅተው እያሳዩ፡፡ < አሁን በድንብ ገባችሁ አይደል ልጆች> አሉ የፈረቁትን እሸት ለአነዱ ተማሪ እንዲበላው እየሰጡት
ተማሪዎች፡ አዎ መምህር፡፡ የተወሰኑ ልጆች ቀድሞም ገብቶናል ብለው አጉረመረሙ፡፡
#መምህር፡በሉ ተማሪዎች ያመጣችሁትን አሸት ማርክ ስላልሞላሁ፣ ተስልፋችሁ እያስመዘገባችሁ ቢሮየ አስቀምጣችሁ ትሄዳላችሁ፡፡ተማሪዎች በጣም ተናደዱ፡፡ እርቧቸዋል፡፡ ጎምዥተዋል፡፡ እንዳይበሉ፣ ማርክ ይቀንስባቸዋል፡፡ ከዚያም አንዳንዶች የጓደኞቻቸውን መብላት ጀመሩና ጠብ ተፈጠረ፡፡ መምህሩም የተጣሉትን ተቆጥተው፣ የመጣውን እሸት ተማሪዎች ለእጅ ስራ ትምህርት ብለው በሰሩት ቅርጫት ላይ ካስከመሯቸው በኋላማርኩን ሞልቸ ነገ አሳያችኋለሁብለው አሰናበቷቸው፡፡
ከዚያም መምህራን እሸቱን እየጠበሱና እየቆሉ ለአንድ ሳምንት እንትን በእንትን (ቃሉ አይነኬ ነው፣ ነቄ ያለ ይወቀው) ሁነው በድግስ ሰነበቱ፡፡ መምህሩም ማርኩን ከአምስት ብቻ ያዙት፡፡ የዛሬ ተማሪ አምጣ ቢባል ያመጣ ይሆን? ደግ ዘመን፡፡ ነገሩን እንጂ፣ ከተማሪው ተርፎ ለመምህሩ የሚሆንስ እሸትስ አለ ብላችሁ ነው?


1 comment: