Thursday, August 16, 2018

ከነፃው ፕሬስ ፋና-ዎጊዎች


(በቅዱስ ሃብት በላቸው)
ነሃሴ 9 ቀን በኢትዮጵያ የነፃ ፕሬስ ታሪክ ፋና-ወጊ ተብለው በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱት ጋዜጠኞች መካከል አንዱ የሆነው የመብሩክ/መብረቅ ጋዜጣ አሳታሚና አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ ወርቁ ዓለማየሁ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየበት ዕለት ነው።ትንሿ ትግራይ!” በሚል ርዕስ በአንድ መንግስታዊ ተቋም ውስጥ ከላይ እስከታች የተሰገሰጉትን የአንድ ብሔር ሰዎች በማስረጃ ማጋለጡን ተከትሎ ድንገት ታፍኖ እስር ቤት ተጥሎ የነበረው ጋዜጠኛ ወርቁ፣ ከእስር ቤት እንደወጣ ነበር እስከወዲያኛው ከዚህ ዓለም በሞት የተለየን።
ጋዜጠኛ ወርቁ ከዚያም በፊት ቢሆን በአምባገነኑና ዘረኛው ሕወሃት አገዛዝ ያለአግባብ እየታፈነ በተደጋጋሚ ለእስርና እንግልት ሲዳረግ ነበር። በአንድ ወቅት የከፍተኛው /ቤት ሁለተኛ ወንጀል ችሎት ተከሶ ይቀርባል። የተከሰሰው ወያኔ የመጀመሪያዎቹንጄነራሎችከብዙኀኑ ህዝብ ደብቆ ሾሞ ወሬውን አፍኖት ስለነበር፤በረኸኞቹ ያለወታደራዊ ሣይንስ በከፍተኛ ማዕረግ ተንበሸበሹበሚል ርዕስ ባወጣው ዜና ነው። በዜናው የተሿሚዎቹን ዝርዝርና ያላቅማቸው የተጫነላቸውንማዕረግዘርዝሮ ለህዝብ አቀረበ። የቀረበው የነፃ ፕሬስ ጋዜጠኞችን፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ መሪዎችንና አባላትን እንዲሁም ሥርዓቱ ያሰጉኛል ያላቸውን በመቅጣት ከሚታወቁትዳኛተብዬዎች ዋነኛ ከሆነው ልዑል /ማርያም ያለበት ችሎት ነበር።
ጋዜጠኛው ዜናው እውነት መሆኑን ወንጀል አለመፈጸሙን ገለጸ። በዚሁ ዜና በምርመራ ስም በፓሊስ ጣቢያ ለረጅም ጊዜ ታስሮ መንገላታቱም አግባብ አለመሆኑን አስረዳ። በጊዜው መከላከያ ማስረጃ እንዳለው ይገልፃል። በዚህ ጊዜ በቁጣ ይህ ዳኛ ተብዬምንድነው መከላከያ ማስረጃህ?” ብሎ ይጮኻል። ተከሳሹመከላከያ ማስረጃዎቼ የተሾሙት ጄነራሎች ከየትኛው ወታደራዊ ሣይንስ ተመርቀው እንደወጡ ቀርበው ያስረዱልኛል …” በማለት፤ “… /ጄነራል ፃድቃን /ተንሳይ፣ …” እያለ መዘርዘር ሲጀምር ይህ ፍትህ ገዳይ አላስችል ብሎትዝምበል አንተ እነሱ እንዳንተ ሥራ ፈት አይደሉም። እዚህ ሊመጡልህ አይችሉምይልና በቁጣ ያቋርጠዋል።
የቀኝ ዳኛ የነበረችው ወጣት ጣልቃ ገብታመከላከያ ምስክር መጥራት መብቱ ነው። እነሱም ለምስክርነት ከተጠሩ ይቀርባሉ። ማንም ሰው ከሕግ በላይ አይደለምትላለች። ችሎቱ ፍጥጫ ነገሰበት። ልዑል የሚችለውን ተሳድቦ ሌላ ቀጠሮ ሰጠ። ዳኛዋ ከዚያ በኋላ በዚያ ችሎት አልታየችም። ወያኔ ዘግይቶ ሓየሎም ሲገደል ወያኔ ሹመቱን ሳይወድ ይፋ አድርጎ አወጣ። ጋዜጠኛው ቢቸግረውጄነራሎቹአይቀርቡም ከተባለ ወያኔ እራሱ ያወጣው ዝርዝር በማስረጃ ይቅረብ ሲልም ሊቀበለው አልፈቀደም። ለወያኔፍትህማለት ይህ ሲሆን፤ ለዳኛ ተብየው ልዑል /ማርያም ደግሞሕግየወያኔ ጠላቶች የተባሉትን ሁሉ ያለምህረት መቅጫ የበቀል መሣሪያ ነው።
ጋዜጠኛ ወርቁ ባለትዳርናየሶስት ልጆች አባት ነበር።


No comments:

Post a Comment