Monday, October 19, 2015

ለምን አታገባም? (ክፍል-01)

ባለፉት ድፍን ሃያ አመታት በት/ቤት ህይወቴ ከተጠየቅኋቸው ጥያቄዎች ቀጥሎ በብዛት የተጠየቅሁት ጥያቄለምን አታገባም?” የሚለውን ጥያቄ ነው፡፡ ጎበዝ ማግባት ግንለምን አታገባም?” የሚለውን ጥያቄ እንደመጠየቅ ቀላል አይደለም፡፡ የሂሳብን፣ የፊዚክስን፣ የኬሚስትሪን ጥያቄ ፎርሙላውን በመጠቀም መፍትሔ መፈለግ ወይምፕሩፍማድረግ ይቻላል፡፡አግባየሚለውን ጥያቄ ግን ሚስት አግብቶ ለመመለስ ፎርሙላ አልባ የሆኑ ውስብስብ ጥያቄዎችን መመለስ ያስፈልጋል፡፡ ሰውአግባ አግባ…..” ብሎ መስመር ውሰጥ ያስገባህና ነገ ግራ ስትጋባአይዞህ ቻለውብሎህ የፌዝ ሳቅ እየሳቀ ይሸሽሃል፡፡ ምሽት ላይጉሮ ወሸባንአስጨፍሮ በነጋታው ጥዋት ጫጉላ ሳይፈርስ የነገር ጦር ከመማዘዝ ዝግ ብሎ አስቦ፣ አጥንቶ ማግባት ይሻላል፡፡ ስንቶች ናቸው ተጋብተው አመት ሳይደፍኑ የሚፋቱት፤ ስለዚህ እኔ ረጋ ብዬ፣ በደንብ አጥንቼ ነው የማገባ ብየ እከራከራለሁ፡፡

አንድኛው መጦ ደግሞየአዲስ አበባ ልጅ እንዳታገባአለኝ፡፡
ኮስተር ብዬ ምነው አልኩት?

አንተን ሳይሆን ኪስህን ነው የምታገባው፡፡ ያለችህ ሳንቲም ስታልቅ….”ከለለህ የለህም…” የሚለውን የዶ/ ጥላሁንን ዜማ ጋብዛህ እብስ ትላለች፡፡ ዱካዋን ተከትለህ ስትሄድ ከአንዱ አራት አግር ካለው ወጠምሻ ጎን ሂዳ ጋቢና ጉብ ትላለች፡፡ አንተም ሄድህ ከመዳፉ ለመቀማት ብታስብም የጎረምሳውን ጡንቻ ስታይ በርግገህ ወደኋላህ ትመለሳለህ፡፡ ከዚያም አስከመጨረሻው ድህነትህን  እየረገምህ የከተማ መነኩሴ ሁነህ ትቀራለህ፡፡ የአሁን ሴቶች ደግሞ ብልጣብልጥ ሁነዋል፣ ከታክሲ በላይ ቤት ኪራይ ስላማረራቸው ኮንደሚኔም ካለውመልኩን ወላድ አይየውየሚባል እንኳ ቢሆን የኔ ማር፣ የኔ ቆንጆ ብለው እንደ ምንጣፍ ይነጠፉለታል፡፡ ቤቱን በሁለታቸው ስም ካደረጉ በኋላ፣ ጨርቁ እንዳይከተለው አድርገው ይሰድቡታል፡፡ ከዚያ በኋላ ያለውን ተወው፡፡ ወይ ያብዳልወይ ደግሞ….ኤጪ ይበቃናል ባክህ ተወው፡፡
እሺ የት ሄጀ ላግባ? ነው እንደ ዕቃው ከቻይና ምናምን ላስመጣ….ብየ ጠየቅሁት፡፡
አይ ወንድሜ! ቢሆንማ ጥሩ ነበርሀብታም ታደርግህ ነበር፡፡
በልጅ ነው በገንዘብ?
በልጅም ቢሆን አንዴ ሰባቱን ወልደህ መገላገል ነዋ፡፡ በየጊዜው ሚስትህ ባረገዘች ቁጥር ለምን ትጨናነቃለህ፡፡ አማረኝ፣ ተገላበጠብኝ፣ ቼክ አፕ፣…..ስንት ጣጣ አለ መሰለህ፡፡ የቻይና ሚስት ችግሩ አርቲፍሻል ልጆችን ልትወልድብህ ትችላለች፡፡
እሺ ከየት ላምጣ፣ ከማርስ?
ከማርስ ያሉት እንኳ ለእኛ የሚደርሱ አይመስለኝም፤ባይሆን ለልጆቻቸን፡፡
ታሾፋለህ አልኩት በንዴት?
ከምሬ ነው፤ ለምን /ሃገር ሄደህ የገጠር ልጅ ፈልገህ አታገባምአለኝ
በዚን ጊዜ አንድ /ሃገር ያለ ጓደኛዬ በትዝታ ወሰደኝ፡፡ ይህ ጓደኛችን፤ ለምን አታገባም ብለን ስንጠይቀው፤ ማንን ላግባ ይለናል፡፡
ምን አይነት ሴት ነው የምትፈልገው? ብለን ጠየቅነው፡፡
እኔ ተቀምጣ ምትሸና ከሆነች ችግር የለብኝምአለን::
በእርግጥ የጓደኛዬ መልስ የቦሌ ሴቶች ቆመው ሲሸኑ የተነሱትን ፎቶ ላዬ ሰው ብዙ አያስገርምም፡፡ የትውልድ ዝቅጠት ይሏችኋል ይሄ ነው፡፡ ወንዱ የሴቱን፣ ሴቷ ደግሞ የወንዱን መመኘት፡፡ ባለን አለመደሰት፣ ተፈጥሮን መቃወም፡፡
ታዲያ ከዛሬ አራት አመት በፊት አንድ ቀን ለዚህ ጓደኛችን ተመካክረን አንዲት የመስከረም አበባ የምትመስል ቆንጆ ኮሌጅ ተማሪ አመጣንለት፡፡ በቡና ጠጭ ሰበብ እኛ ከምንቀርባት ከጓደኛዋ ቤት እንድትመጣ አደረግን፣ ቡናው ተፈልቶ እስኪያልቅ ቸከላት፡፡ ስስቅ፣ ስትሽኮረመም፣ ስጠጣ፣ ስታወራ…..አያት፡፡
ከዚያ ወጣ ስትሄድእህ እንዴት ናት ትሆንሃለችብለን ጠየቅነው፡፡
አልታየችኝምብሎን እርፍ አለ፡፡
በጣም ተናደድንከአቦል እስከ በረካ ጣራውን ነው እንዴ የኸውአልነው በደቦ፡፡ደግሞ ተቀምጣ ምሸና ምናምን እያልክ ትቀላምዳለህአለው አንደኛው፡፡ እውነት ለመናገር በሰዓቱ ያናደደን እሱ አትሆነኝም ማለቱ ሳይሆን ልጅቱ ቆንጆ ስለነበረች ከመካከላችን ለአንዳችን ትሆናለች ብለን ነበር፡፡ ሁሉም ልቡ አስቧታል፡፡ ግን እሱ ትልቃችን ስለሆነ ነው ቅድሚያ የተሰጠው፡፡ ለእሱ የታሰበች ደግሞ ከዚህ በኋላ ለእኛ መሆን አትችልም፡፡ የሷ ዶሴ በዚው ተዘጋ፡፡ ከአራት ወር በኋላ ያችን የመሰለች ለግላጋ ወጣት ለአንድ ሽማግሌ መምህር በቤተሰብ ታፍና ተዳረች፡፡
ከአንድ አመት በኋላ ጓደኛችንንአሁንስ ምን አይነት ሴት ነው የምትፈልገውብለን ጠየቅነው፡፡
እግሯ ጎንጎ ጫማ ያልለመደ የገጠር ልጅአለን፡፡
እንኳም የሸገር ልጆች አልሰሙህ፣ እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ የቁልቁሊት ይሰቅሉህ ነበርአለው አንዱ ጓደኛዬ::  ጓደኛችንን ንግግሩን ቀጠለ፤እኔ ምልህ እንደ ድሮ የገጠር ባሎች ገዝተሃት ልትኖር ነው ምትፈልገው፡፡ ታዲያ እዚ እኛ ጋር ምን ታደርጋለህ? ሂድ ገጠር ግባና እርፍ ጨብጠህ እረስ፡፡ ወይም ሰፊ መሬት ያለው ባላበት እንፈልግና ተከርቸም እናስገባህእያለ በስላቅ ሲያሾፍበት ክፉኛ ደሙ ፈላና የተናገረውን ልጅ ጉሮሮ ዘሎ አነቀው፡፡ ተረባርበን አላቀቅናቸው፡፡
በሌላ ጊዜ ደግሞ እንደ ቀልድ አንዷን ልጅላገባት እፈልጋለሁጠይቂልኝ ብሎ ለቅርብ ጓደኛዋ አስጠየቃት፡፡ የተጠየቀችቱም ልጅ ለደቂቃ እንኳ ሳትግደረደርየሚያምነኝ ከሆነማ እበል በይውብላ መለሰች፡፡ መልክተኛዋም እንደወረደ ነገረችው፡፡
እንዴት ነው ምን አለችህ አልኩት::
ሳትገደረደር እበል በይው አለችአለኝ፡፡
ታዲያ አሪፍ ነዋ፣አግባት አልኩት፡፡
"ተወው ባክህ ደበረኝ ትንሽ እንኳ መግደርደር አለባትአለኝ፡፡ ከዚያም ጓደኛዋን ጠርቶትቸዋለሁ በያትብሎ ነገራት፡፡
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ስለጋብቻ አንጠይቀውም፡፡ አስካሁንም አላገባም፡፡ ምን አልባት አንድ ቀን አንዷ ጠይቃ ታገባው ይሆናል፡፡ አይ ጓደኛዬ! ቁሞ ቀረ! እሱ ቁሞ እኛንም አስቆመን! ችግር የለም እኔ እንኳ እቀመጣለሁ፡፡
ወደ ቀደመ ነገሬ ልመለስና በአዲስ አበቤው መካሪያችን አነሳሽነት ባለፈው አመት ሶስት ሁነን ሚስት ፍለጋ ወደ /ሃገር ዘመትን፡፡ዘመቻ ሚሰት ፍለጋ፡፡ አንድ ሁለት ቀን ከተማ ቀመስ የሆኑ ሴቶችን አንዲት የጦጣ ግንባር የምታክል የወረዳ ከተማ ውስጥ ዞር ዞር እያልን መገራረፍ ጀመርን፡፡ ምንም እንኳ የገጠሩን ባህል ያልረሱ ብዙ ሴቶችን ብንመለከትም፣ ነቃ ብለው ሰማይ ሰማይ እያዩ በሚኒ እና በሱሪ በፊታችን የሚያልፉትን ሴቶች ሲያይ አንድኛው ጓደኛዬ እጢው ዱብ አለ፡፡ አልፎ አልፎ ሊፒስቲኩንም፣ የፀጉር ቀለሙንም የተጠቀሙትን ሲመለከት የባሰ ተናደደ፡፡ ብድግ ብሎእንሂድ አዲስ አበባ እዚያ ይሻለናልአለ፡፡
ምኑ ነው የሚሻለን?” ጠየቅነው፡፡
አያችሁ የአዲስ አበባ ችኮች ፈልተው ፈልተው ሰክነዋል፣ እነዚህ ገና እየፈሉ ነው እነሱን ለማስከንና ለማብረድ ማን ይሰቃያልአለንና ሁለታችን ከትከት ብለን ሳቅን፡
እዚህ አኮ ሁሉም አይደሉም አርቲፍሻል ውበት ያላቸውአልነው፡፡
እባክህ አዲስ አበባም ሁሉም አይደሉም፡፡ ቤተሰብ በስነ ምግባር ያሳደጋቸው ስንት ምርጥ ልጆች አሉ መሰለህ፣ ችግሩ እነሱን ለማግኝት ቁልቢ ሄደህ መሳል አለብህአለን ተስፋ በመቁረጥ መንፈስ፡፡
ከብዙ ክርክር በኋላ ትንሽ ቀን ቆይተን የድላችንን እንሞክር ብለን አንድ ሁለት ቀን አደርን፡፡ አነንድ ቀን ለመኪና በተሰራው ጥርጊያ መንገድ እየተጓዝን ሁለት ልጆች በእኛ ፊት ለፊት ከእርቀት እየመጡ ተመለከትን፡፡ አንደኛዋ መልኳና እርምጃዋ እምቢ ብሎ አይን ውስጥ ይገባል፡፡ ከዚያም አዲስ አበባ ይሻላል እያለ ሲከራከር የነበረው ጓደኛችን ቶሎ ብሎ ሳንቀድመው፣ያችን ቀይዋ ልጅ ለእኔ ናት እጠይቃታለሁአለ፡፡ መልስ አልሰጠነውም፡፡ ባንነጋገርም ሁለታችን እንደተናደድን አረማመዳችን ያሳውቃል፡፡ ፈጠን ፈጠን ብለን ስንራመድ ረጋ በሉ እንጂ አለን፡፡ ከዚያም ሁለቱ ልጆች እይታችን እነሱ ላይ መሆኑን ስለተረዱ አንገታቸውን ደፍተው አለፉን፡፡
ሂድ ቶሎ ጠይቃትአልነው፡፡
ኋላቸውን ተከትሎ ትንሽ ከሄደ በኋላአህት አህት…….” እያለ ይጣራ ጀመር፡፡
ሁለቱም በአንዴ ፊታቸውን ዞረው ማንን ነው አሉት፡፡አንቺን አንድ ጊዜ ላውራሽ?” አላት፡፡ ከዚያ በኋላ ተውት፣ ቀይ የነበረች ልጅ በአንዴ ጥቁር ሆነች፡፡ ከመንግስቱ /ማርያም ትንሽ ከፍ ባለ ቁጣ ቁም ስቅሉን አሳየችው፤የት አባህ ታውቀኛለህ፣ እዚያ በለመድኸው….” ምናምን ምናምን አለች እና ወደ እሷ ቀረብ ሲል ሁለቱም ወደል ድንጋይ ሲያነሱ እኛ ቶሎ ብለን ወደ እሱ ተስፈንጥረን ስንሄድ ድንጋዩን ጥለው ወደፊት ሸመጠጡ፡፡ በል እንሂድ ለጥያቄ ድንጋይ ያነሳች ነገ አግብተሃት ንብረቷን ብትጠይቅ በላውንቸር ነው ምታቀምስህብለን አረጋጋነውና በነጋታው አዲስ አበባን ሚያሞግሱ ሙዚቃዎችን እያዳመጥን ሸገር ገባን፡፡
ሌላኛው ጓደኛችንም ከዚህ በኋላ የሸገር ልጅ አገባለሁ አለ፡፡ በጓደኛችን የተዘረረው ድንጋይ ያስፈራው መሰለኝ፡፡
ለምን?” ብለን ጠየቅነው፡፡
ኧሯ ….የገጠር ልጅ አስቸጋሪ ናት፡፡
እንዴት?”
ምን እንዴት አለው፤ ለማውራት ተለምና፣ ለማግባት ተለምና፣ ከዚያ ደግሞ ነገ ሌላ ጣጣ፤ ልብስሽን አውልቂ ልመና፣ አብረን እንተኛ ልመና፣ ያን ነገር ስጭኝ ልመና…..ምን በወጣን ከዚህ ሁሉ መከራ ጣጣ የለላቸው የሸገር ልጆች አሉልን ባክህአለን፡፡
ግን ምን ዋጋ አለው፤ ይህን ባለ አፉ አነሆ እስካሁን አላገባም፡፡
ጋብቻ ትርጉሙም፣ ፎርሙላውም፣ መንገዱም ከባድ ነው፡፡ አንዳንድ ሰው ጋብቻ እንደ ጫማ ማሰሪያ በቀላሉ የሚታሰርና የሚፈታ አድርጎ ይቆጥረዋል፡፡
ወደሌላው መካሪዬ ልለፍ፡፡ 45 አመት ጎረምሳ ለማለት ይከብዳል፣ጎርማሳብንለው ይቀላል፡፡ጎርማሳየሚለው አዲስ ቃልጎረምሳእናጎልማሳየሚሉትን ሁለት ቃላት በማጣመር የተገኘ ነው፡፡ ይህ ጓደኛዬ አላገባም፡፡ እኔን ግን እንደ ቆላ ሞጀሌ ይነዘንዘኛል፡፡ ምክንያቱ በጣም ያስቃል፡፡የምትሆነኝ አጣሁይላል፡፡ ይገርማል ሰው 45 ዓመቱም ያማርጣል፡፡ እኔ ግን ምክንያቱ ስላልተዋጠልኝ ምነው ጋሼ ነገር እምቢ አለ እንዴ  አልኩት፡፡ ኧረ!…..አንተ!……እሱማ…………

              (((((((((((((((ይቀጥላል!!!)))))))))))))))))

1 comment:

  1. ዋው!...በዉኑ ወንድማችን(አባታችን) ይህን አይነት ነገር ምን ስትል አሰብከው?? በጣም ያስደስታል አይዞህ በርታልን....................እግዚአብሔር ያበርታህ....

    ReplyDelete