Friday, March 18, 2016

አድዋ


ወይ አንቺ አድዋ!
የጥቁር ህዝብ ትንሳኤዋ!
በኩረ ነፃነት ምሰሶዋ!

የደመና ጥግ የሰማይ ክሳድ
የሐበሻ ዘር የወኔ ሞረድ
አፍሪካ ጭቁን የነፃነት በር
መክፈቻ ቁልፏ ይቻላልድር
የማንዴላ ኃይል የሉተር ህልም
መነሻ ሃሳብ ትንቢተ ዓለም
አድዋ አንቺ ነሽ
የሐበሻ ዘር በደም የፃፈሽ


አዎን አንቺ ነሽ አድዋ
የጥቁር ህዝብ ትንሳኤዋ!
በኩረ ነፃነት ምሰሶዋ!

ክብር ለጀግኖች ለሰማታቱ
ለሀገር ፍቅር ብለው ለሞቱ
ክብር ለአባቶች አፈር ለላሱ
ለእኛ ነፃነት ሞት ለቀመሱ!
ክብር! ክብር! ክብር! ክብር!
ሞተው ለዳኑን ከጥፋት ቀንበር!!
©ዘላለም ጥላሁን
ጥር 25 2008 .ም፡ አድዋ ከተማ



No comments:

Post a Comment