Monday, March 28, 2016

በ እንተ “ማኅበረ ቅዱሳን”: ክፍል_1

(ትዝብትና ነፃ አስተያየት)
                  ( ዘላለም ጥላሁን_ zelatilahun@yahoo.com)
ማኅበረ ቅዱሳን ማን ነው? መች ተመሰረተ? ዓላማው ምንድን ነው? ቤተክርስቲያን ምን አበረከተ?   ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ለምን ጠሉት? የሁሉም ቀስትስ ለምን ወደ ማኅበረ ቅዱሳን አነጣጠረ? እውን ማኅበረ ቅዱሳን ለቤተክርሰቲያን ስጋት ወይስ አቃቤ?
(የውጭ አካላትን ጣልቃ ገብነት ለጊዜው ተወት አድርገን እስኪ መረጃ እያጣቀስን ወደ ውስጥ እንመልከት)
ቅድመ ታሪክ (ማኅበረ ቅዱሳን ማን ነው?): መተከልና ጋምቤላ መንደር ምስረታ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች የፅዋ ማኅበራትና የብላቴ ዘመቻ ማኅበረ ቅዱሳን መመስረት ትልቅ ድርሻ ቢኖራቸውም ብፁዕ አቡነ ጎርጎሪዎስ ካልዕ እና ብፁዕ / አቡነ ገብርኤል ወጣቶችን ሰብስቦ ከማስተማር ወደ አንድ የማኅበር ስያሜ እስከ ማምጣት ድረስ ያደረጉት ተጋድሎ ለማኅበሩ ቀጥ ብሎ መቆም መሰረት መሆኑን በጊዜው የነበሩ አባላት ሁሌም የሚናገሩት ሃቅ ነው1፡፡ በተለይ እምነቱን በእነ ሌሊንና እስታሊን ፍልስፍና ቀይሮ ሶሻሊስት አብዮት ጨርቁን ጥሎ በከነፈው ትውልድ መሃከል ስለ አብያተ እምነት የሚቆረቆር ትውልድ መኖሩ ነበር እኒህን አባቶች  “ ልጆቼ እኛ እናንተን መፈለግ ሲገባን እናንተ እኛን ፈልጋችሁ መጣችሁ፣ ንፍሮ ቀቅለን፣ አዳራሽ ባይኖረንም ድንኳን ጥለን እናስተምራችኋለን1,2,3,4 ብለው እንዲቀበሏቸው ያደረጋቸው፡፡ 

ማኅበረ ቅዱሳን ስያሜው እስከ ዓላማው በሰዓቱ በነበሩ ትጉሃን አባቶች የተቃኘ ነው፡፡ ስያሜውን በተመለከተ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል በተለያዩ የፅዋ ማኅበራት ይሳተፉ የነበሩ ወጣቶችን በአንድ ላይ በመሰብስብ እንዲህ ሲሉ ነበር የሰየሙት፡
  «………..ሁላችሁም የያዛችሁት አገልግሎት የቅዱሳን ክብር የሚገለጽበት ነው፡፡ ስለዚህ የማኅበራችሁም ስም 'ማኅበረ ቅዱሳን' ይባል፡፡»5  
እንግዲህ ይህ ክስተት ሐይማኖት አብዮት ጠንቅ ነው የሚል አዋጅ በወጣበት እምነት አልባውየኮሚኒዝም አብዮት ምሽት ላይ መፈጠሩ፤ ትውልድ ተቀደደው ቦይ ሰጥሞ እንዳይቀር፣ መጪውም ትውልድ በጥራዝ ነጠቅ ፍልስፍና ከመንገዱ እንዳይወጣ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደነበረው ማንም ንፁህ ህሊና ሁኖ ነገሮችን ማገናዘብ የሚችል ሰው የሚፈርደው ሃቅ ነው፡፡
በኋላም ይህ ማኅበር በቅዱስ ሲኖዶስ በተሰጠው አመራር መሰረት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ስለ ሃይማኖታቸውና ታሪካቸው ዓለማዊው ትምህርታቸው ጎን ለጎን እዲያስተምር፤ እንዲሁም ገዳማትና የአብነት /ቤቶች ትውፊታቸውን ጠብቀው ወደ መጪው ዘመን እዲሻገሩ እንዲያግዝ ተጨማሪ አደራ የተሰጠው ማኅበር ነው3,4፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያን ምን አበረከተ?  
ማኅበረ ቅዱሳን ከተመሰረተ ጀምሮ የሚታዩና የማይታዩ ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን ማበርከቱ ገበያ ሃቅ ነው፡፡ በእርግጥ ለመንፈሳዊ አገልግሎት የተደረገ ሱታፌ በፈጣሪ እንጂ በሰው የሚለካ ባይሆንም፤ ማኅበሩ በጥንት ዘመን ለኢትዮጵያ መካነ አእምሮ የነበሩ ጥንታዊ የአብነት /ቤቶችን በመደገፍና በማጠናከር፣ ገዳማትን በመደገፍና እራሳቸውን እንዲችሉ በማገዝ፣ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን  ስለ ነገረ ሃይማኖት በመሳተማርና በስነ ምግባር በማነፅ ያደረገውን ትልቅ አስተዋፅኦ የቀመሰ የሚያውቀው ሃቅ፣ ተመልካችም ህሊናው የማይክደው እውነታ ነው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ከሃይማኖታዊ አገልግሎቱ በተጨማሪ በስነምግባር የታነፀ፣ ፈሪሃ እግዚአብሔርና ፈሪሃ ህሊና ያለው ትውልድ ለሃገር ማበርከቱም አሌ የማይባል እውነት ነው፡፡ ሀገርን ከማህበረሰቡ ባህልና ሀይማኖት ለይቶ ማዬት ከባድ ነው፡፡ በማህበረሰብ ባህልና ሐይማኖት ያልተቃኘ ትውልድ ለምንም አይመለስም፡፡ ይህን ለማጠየቅ የምዕራባውያንና የሩቅ ምስራቅን ማህበረሰባዊ ቀውሶች አፍታ ማስታወስ በቂ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ማኅበሩ በቅርስ ጥበቃና በጥናትና ምርምር ዘርፍ ያደረገውን ጉልህ አስተዋፅኦ መጥቀስ ይቻላል፡፡
ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ማኅበሩን  ለምን ጠሉት?
የአሁኑ ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ማቲያስ የሰሜን አሜሪካ ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ በነቡሩበት ወቅት ማኅበረ ቅዱሳንን አገልግሎት ያሞገሱና ይደግፉ ነበር፡፡ በ ወቅቱ የሰጡት ምስክርነትም ቃል ቃል ይህንን ይመስል ነበር፡
በመጀመሪያ ማኅበሩ ቤተክርስቲያኗ አምናበት (የሲኖዶሱ ጉባኤ አምኖበት) በቤተክርሰቲያኑ ህግና ስርዓት የሚመራ ማኅበር ነው፡፡ በመቀጠል ማኅበሩ የተቸገሩ የገጠር አብያተ ክርስቲያናትንና ገዳማትን እንደሚረዳ አይቻለሁ፡፡ ይህ በጣም ትልቅ ነገር ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ቤተክርስቲያንን ሊውጡ የተነሱ ብዙ ድርጅቶች አሉ፡፡ በዚህ ክፉ ጊዜ ይህን የመሰለ ተከላካይ መንፈሳዊ ማኅበር መፈጠሩ ለቤተክርስቲያናችን ታላቅ ሃብት ነው፡፡ በመጀመሪያ እግዚአብሔርን  ልናመሰግን ይገባል፤ እንዲህ አይነት ለቤተክርስቲያን ህልውና የሚቆም ጠበቃ ማኅበር በመፈጠሩ፡፡  እውነት በጣም ነው እግዚአብሔርን የምናመስግነው!”6
በሌላ ጊዜም እንዲህ የሚል ተመሳሳይ የምስክርነት ቃልን ሰጥተው ነበር፡
“……ይህ ማኅበር መጠናከር አለበት፤ አገልግሎቱ መጠናከር አለበት፣ ጉባኤው መጠናከር አለበት፡፡ ሁላችሁም መደገፍ አለባችሁ፡፡ ብዙ ተጋድሎ የምታደርጉ ወጣቶች አላችሁ፤ በእውነት በጣም ነው የምኮራባችሁ፡፡7
ይህ የሚያሳው ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ስለ ማኅበሩ የሰፋ ግንዛቤና መልካም አመለካከት እንዳላቸው ነው፡፡ ይህን በተናገሩ አንደበታቸው ግን ሲመተ ፕትርክናቸው ማግስት ደግሞ የተናገሩትን ቃል ቃል እንመልከት፡
ቤተክርስቲያናችን በቅኝ ግዛት ተይዛለች፡፡ ቤተክርስቲያናችን በቅኝ ገዥዎች ተይዛለች፤ ማወቅ አለባችሁ፡፡ መረዳት አለባችሁ ይህን ጉዳይ፡፡ በኋላ አላየንም አልሰማንም እንዳትሉ፡፡ ማነው ቅኝ ገዢው? አንድ ማኅበር፣ ሁላችሁም የምታውቁት ማኅበር………..ገንዘብ የሚሰበስብ ማኅበር……”7,8
እንግዲህ እነዚህ ፍፁም ተቃራኒ የሆኑ አነጋገሮች አንድ ሰው አንደበት የወጡ ናቸው፡፡ ከዚህ ውስጥ እውነተኛው ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ቃል የቱ ነው? የትኛውን እውነት ነው ልባቸው አምኖ የተናገረው? ተቃራኒ የሆነ ነገር በመናገር ምዕመኑን ማወናበድስ ከአንድ አባት ይጠበቃል ወይ? ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ለምን ሁለት ምላስ ሆኑ? ሎቱ ስብሃት!
ስለ እውነት እና ውሸት በ አንድ ጉባኤ ላይ በ አንደበታቸው የተናገሩትን እናንሳ
ጵጵስና ማለት እኮ የቤተክርሰቲያኗ የመጨረሻ ቁንጮ ነው፡፡ ……….ጳጳሳት ከዋሹ ማን ነው እውነት የሚናገረው? ምኑን ነው የምናስተምረው? ውሸት ማስተማር ከ እኛ ይጠበቃል? ከእኛ!……አጅግ የሚያሳዝን  ነው7 በማለት እራሳቸውንም ሌሎችንም ወል ይተቻሉ፡፡
ፓትሪያርኩ ስለ ማኅበሩ የነበራቸው ትልቅ እምነት የት ገባ? ባለፉት ሁለት ሶስት ዓመታት ውስጥ ምን አዲስ ነገር መጣ? በእኔ እይታ አዲሱ ነገር የእሳቸው ፓትሪያርክ መሆን እንጂ ማኅበሩ በዓላማም በስምም የተቀየረ አይመስለኝም፡፡ ቅኝ ገዢ ያሉትን ማኅበርስ ማስረጃ አቅርበው በሲኖዶስ ማስመከርና እርምጃ ማስወሰድ እንዴት ተሳናቸው? የጥላቻቸው መሰረት ምን ይሆን? ልጅ ቢያጠፋ እንኳ ቆንጥጦ ከማስተካከል ባለፈሰድቦ ሰዳቢ” መስጠትስ አንድ ታላቅ አባት ይጠበቃል ወይ? ፍርዱን ለእራሳቸው፣ መላምቱን ለአንባብያን ትቼ ወደ ሚቀጥለው ጉዳይ ልለፍ፡፡  
የሁሉም ቀስትስ ለምን ወደ ማኅበረ ቅዱሳን አነጣጠረ?
ይህ የጽሁፌ ዋነኛ ዓላማ ባይሆንም ከውጭ ያሉ አካለትን ተፅዕኖ በጨረፍታም ቢሆን ማየቱ ክፋት የለውም፡፡ በየድህረ ገጾችና ማህበራዊ ሚዲያዎች በተናጠልና በቡድን ማኅበሩን መተቸትና ማጠልሸት የየእለት ስራቸው ያደረጉ ግለሰቦችና ቡድኖች ማየት የተለመደ ነው፡፡ እነሱን በመዘርዘር ጊዜዬን አላጠፋም፡፡ እንደ ማሳያ ግን የ “አባ ሰላማ” ና የ “ደጀ ብርሃን”ን ገፅ ማየት ይበቃል   9፡፡ የብዙዎች ዓላማ ወደ አንድ ነገር ያተኮረ ይመስላል፤ እሱም ማኅበሩን መሰረት አልባ በሆነ ትችትና ክስ አዳክሞ ከቤተክርስቲያኗ ገለል እንዲል ማድረግና የፈለጉትን አይነት አስተምህሮ ማራመድና እንደፈለጉ መጠምዘዝ፡፡
ለእነዚህ ቡድኖችና ግለሰቦች ዓላማ ማኅበሩ ደንቃራ በመሆኑ በተለያየ ጊዜ የስም ማጥፋት ውርጅብኝ ይደርስበታል፡፡ ይህ ደግሞ የሚጠበቅ ነው፡፡ ሲሰርቅ የተያዘ ውሻ ሲገስጡት ማንገራገሩ ከፍ ካለም መናከሱ አይቀርም፡፡ ማኅበሩ ግን የተነከሰውን አካል እያሻሸ ሌላውን አካል ላለማስነከስ እየጠነከረ የሄደ ይመስላል፡፡ ውሾች አሁንም ይጮሃሉ፣ ግመሎች ግን መሄዳቸውን ቀጥለዋል፡፡
በእኔ አቋም ማንኛውም እምነት ተቋም የሌሎችን አብያተ እምነቶች ሳይነካ የራሱን ሐይማኖት ማስፋፋት ክፋት ያለው አይመስለኝም፡፡ ከታሪክም የተቀበልነው  ጥሬ ሃቅ ይህ ነው፡፡ ነገር ግን የሌላውን አስተምህሮ ለመበረዝ ዘው ብሎ የሰው ቤት መግባት ሰብዓዊም ሞራላዊም ነው፡፡
አንድ ነገር ግን መናገር እችላለሁ፡፡ እውነት ባለበት ቦታ ሁሉ መከራና ጦርነት ይበዛል፡፡ ለዚህ ደግሞ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን ንግግር ማስታወስ ብቻ በቂ ነው፡፡ በወንጌል ፍሬአቸው ታውቋቸዋላችሁ እንደተባለው፣ እውነትና ንጋት እያደረ መገለጡ አይቀርም፡፡ በዚህ ሁሉ መሃል ግን ዝናሩ ያልቃል እንጂ፣ እውነት አትሞትም፣ ቤተክርስቲያኗም ትጠፋም፡፡ አሁን አሳሳቢው ነገር የውጭ አካላት ጉዳይ አይደለም፡፡ ይልቁንስ የውስጦቹ ለውጮቹ መጠቀሚያ እንዳይሆኑ ቤተክርስቲያኗ እንዴት ትጠንቀቅ የሚለው ጥያቄ ለ ለአመታት መልስ የሚሻ እንቆቅልሽ ይመስላል፡፡
ማኅበሩ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን: አስተምህሮዋን እንጠንቅቅ፤ ድርሻችንን እንወቅ”  በሚል ርዕስ 3.5 ሚሊዮን ብር በላይ አውጥቶ ያዘጋጀውና እንዳይታይ የታገደው ዐውደ ርዕይ ምን አልባት መልስ ይኖረው ከሆነ ወደፊት የምናየው ይሆናል፤ ሳይበሉ መመስከር ስለማይቻል፡፡ ማኅበሩ ያዘጋጀው ዐውደ ርእይ እንዳሰበው ባይሳካም፣ ዓላማውን የሚደግፉና በመልካም ስራው ተስበው መንፈሳዊ ትሩፋትን የሚሰሩ 3.5 ሚሊዮን ሰዎችን ማፍራት ከቻለ ይህ አሰበው በላይ የሆነ ታላቅ መንፈሳዊ ትርፍ ነው፡፡ እንግዲህ ጠላት ከሩቅ አይመጣምየምትለዋ ብሂል እውነትነት አላት፡፡ ይሄን ደግሞ ባለፉት አሰርትና ሃያ ዓመታት ውስጥ ብቻ በገሃድ ታይቷል፡፡ ሁሉም ነገር ገሃድ ስለሆነ ወደ ዝርዝሩ አልገባም፡፡
እውን ማኅበረ ቅዱሳን ለ ቤተክርስቲያን  ስጋት ወይስ አቃቤ?
ል……
ዋቢ ገጾች
1.     ማኅበረ ቅዱሳን ማን ነው?: https://www.youtube.com/watch?v=uSVQGR5swM4
2.    የማኅበረ ቅዱሳን አመሰራረት ታሪክ፡ ማኅበረ ቅዱሳን የህዝብ ግንኙነት፡ ነሃሴ 2002 .
3.    Short History of the Establishment of Mahibere Kidusan: http://www.eotcmk.org/site-en/index.php?option=com_content&task=view&id=109&Itemid=1
5.    የማህበረ ቅዱሳን አመሰራረት ታሪክ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል: https://www.youtube.com/watch?v=a5W3GrPstN4
6.    ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን የቀድሞ ምስክርነት፡ https://www.youtube.com/watch?v=5hrQIFtpTnM
7.    The trial of Mahibere Kidusan - The flip flapping of the Patriarch: https://www.youtube.com/watch?v=bsMUIiQ7m_U
8.    ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ንግግር ስለ ወቅታዊ የቤተክርስቲያ ጉዳይ፡ ጥቅምት 2007 .ም፡ https://www.youtube.com/watch?v=7jDn56OBipU

9.    አባ ሰላማ፡ http://www.abaselama.org/

1 comment:

  1. የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ስለ ነገረ ሃይማኖት በመሳተማርና በስነ ምግባር በማነፅ ያደረገውን ትልቅ አስተዋፅኦ የቀመሰ የሚያውቀው ሃቅ፣ ተመልካችም ህሊናው የማይክደው እውነታ ነው፡፡

    ReplyDelete