Saturday, February 25, 2017

መ  ነ  መ  ነ  ች   እ  ው  ነ  ት
ብርሀን ደበዘዘ~ጨለማ ደመቀ
ሰው ከሰው ሲቀርብ~ሰው ከእራሱ ራቀ
ማመን መተማመን~ጥለው ተሰደዱ
ፍርሃት ጥርጣሬ~ ልብ ተዋሃዱ፤
አይንና አፍንጫ~ጉርብትና እረሱ
መተዛዘን ቀርቶ~ይሙት ሆነ ክሱ፤
ቅትሎ…. ስቅሎ
ቅትሎ….ስቅሎ
ይላል ግብረ ቃኤል~ክፋት ጀርባ አዝሎ፤

እም አልቦ ደመና~ዶፍ እየወረደ
አፍላጋት እምብርት ላይ~ሳት እየነደደ
ሳይዘራ ታጭዶ~ህል እየተቦካ
ወረቀት ጥቅል~ልብ እየተመካ፤
አንዳውላ ምርኩዝ~እየተደገፈ
ሰው እንደ ሰው ኖሮ~ማለፍ ተጠየፈ፤
ንዋይ ብቻ ሆነ~የሰውነት ማሳ
ህሊናም ተከዳ~እግዜሩም ተረሳ

----------------------------------------

  © ዘላለም; የካቲት 2009

3 comments:

  1. ንዋይ ብቻ ሆነ~የሰውነት ማሳ
    ህሊናም ተከዳ~እግዜሩም ተረሳ

    ReplyDelete
  2. ቅትሎ…. ስቅሎ
    ቅትሎ….ስቅሎ
    ይላል ግብረ ቃኤል~ክፋት በ ጀርባ አዝሎ፤

    ReplyDelete
  3. ማመን መተማመን~ጥለው ተሰደዱ
    ፍርሃት ጥርጣሬ~ከ ልብ ተዋሃዱ፤

    ReplyDelete