Friday, March 3, 2017

♥ አድዋ ♥

ወይ አንቺ አድዋ! 
የጥቁር ህዝብ ትንሳኤዋ!
በኩረ ነፃነት ምሰሶዋ!
-------------
የደመና ጥግ~የሰማይ ክሳድ 
የሐበሻ ዘር~የወኔ ሞረድ
አፍሪካ ጭቁን~የነፃነት በር 
መክፈቻ ቁልፏ~ይቻላልድር
የማንዴላ ኃይል~የሉተር ህልም 
መነሻ ሃሳብ~ትንቢተ ዓለም
አድዋ አንቺ ነሽ!
የሐበሻ ዘር~በደም የፃፈሽ
አዎን አንቺ ነሽ አድዋ 
የጥቁር ህዝብ ትንሳኤዋ!
በኩረ ነፃነት ምሰሶዋ!
……..
ክብር ለጀግኖችሽ~ለሰማታቱ
ሀገር ፍቅር ብለው በክብር ለሞቱ
ክብር ለአባቶች~አፈር ለላሱ
ለእኛ ነፃነት~ሞት ለቀመሱ!
ክብር! ክብር! ክብር! ክብር!
ሞተው ላዳኑን~ከጥፋት ቀንበር!
~~~~~~~~~~~~~~~~~
© ዘላለም
[ተፃፈ፡ ጥር  25 2008 .ም፡ አድዋ ከተማ ]

No comments:

Post a Comment